ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 21
Appearance
- ፲፱፻፮ ዓ/ም - የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽ፣ አውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድ በዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው።የአውስትሪያው ልዑል ‘ፍራንዝ ፈርዲናንድ’ እና ባለቤታቸው የሳራዬቮን ከተማ በመጎብኘት ላይ ሳሉ በነፍሰ ገዳይ እጅ ሕይወታቸውን አጡ። ይኼ ድርጊት የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መንስዔ እንደነበር በታሪክ ተዘግቧል።
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተቀናቃኞች፤ በአንድ በኩል አለማኝያ እና በሌላው ወገን የቃል ኪዳን አገራት የጦርነቱን ፍጻሜ ስምምነት የቨርሳይ ውል በዚህ ዕለት ተፈራረሙ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ካይሮ ላይ በተካሄደ ሥርዓተ-ሢመት በቅብጡ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ ተቅብተው የፓትርያርክነቱን ዘውድ ደፉ።