ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 19
Appearance
- ፲፰፻፶፮ ዓ.ም. - ጀኔቭ ላይ የተሰበሰቡ የአሥራ ስድስት አገሮች ልዑካን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ለመመሥረት ተስማሙ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ተመሥርቶ በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. የዓለም አቀፋዊው ማኅበር አባል ሆነ።
- ፲፱፲፭ ዓ.ም. - የኢጣልያው ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሦሥተኛ ለፋሽሽት መሪው ለቤኒቶ ሙሶሊኒ የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ሥልጣን ሰጡ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም - በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሸነፈውና የተሠባበረው የኦቶማን ግዛት አክትሞ በቦታው የቱርክ ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሱዳን መሪ ጄኔራል ሞሐመድ አቡድ በኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ጉብኝታቸውን ጀመሩ። በዚህ ጉብኝትም በንጉሠ ነገሥቱ ፴ኛ የዘውድ በዐል አከባበር ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. - በምሥራቅ አፍሪቃ ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው የታንዛኒያ ሕብረት ሪፑብሊክን መሠረቱ።