ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 24
Appearance
- ፲፬፻፹፮ ዓ.ም - የጄኖአው ተወላጅ ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ (Christopher Colombus) የአትላንቲክ ውቅያኖስን ከአውሮፓ ወደምዕራብ የማቋረጥ ሁለተኛው ጉዞው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሚኒካ ደሴትን አገኘ።
- ፲፰፻፹፮ ዓ.ም. -ፓናማ በአሜሪካ ማበረታታት ተነስታ ከኮሎምቢያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን አወጀች። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቴዎድሮስ ሩዝቬልት የፓናማ ቦይን ለመቅደድ ፈልገው ኮሎምቢያ ለዚሁ ሥራ መከፈል የፈለገችውን ዋጋ ስላልተስማሙበት ፓናማ ነጻ አገር እንድትሆን ጥረታቸው ተሳካ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ.ም - የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ አገርን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከያዙ በኋላ ራሳቸውን በዘውድ ያነገሡት ዣን ቢዴል ቦካሳ በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ወከር ቡሽ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ተመረጡ።