የሰበክ-ሁ ጽላት

ከውክፔዲያ
የሰበክ-ኹ ጽላት

የሰበክ-ኹ ጽላትጥንታዊ ግብጽ መካከለኛው መንግሥት3 ሰኑስረት ዘመን በ1893 ዓ.ም. የተገኘ ቅርስ ነው አሁን የሚታየው በማንቸስትር ሙዚየም በኢንግላንድ ነው።

ሰበክ-ኹ (ወይንም ኹ-ሰበክ) ከሰኑስረት ሥራዊት አንዱ መኮንን ወይም መቶ አለቃ እንደ ነበር ይገልጻል። ጽሑፉ ከሰበክ-ኹ መቃብር በአቢዶስ ነው የተገኘው። በጽሑፉ ውስጥ በከነዓን እና በኩሽ መንግሥት ላይ ስለ ተሳተፉባቸው ዘመቻዎች ይገልጻል።

ጥቅሶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«ግርማዊነቱ [ኻኻውሬ፣ ፫ ሰኑስረት] የሴተት ብሄር የመንቱ ሕዝብ ለመገልበጥ ወደ ወንዙ ወረደ። ግርማዊነቱ «ሰክመም» በተባለ ሥፍራ ደረሰ።... ከዚያስ እኔ ኋላውን ጎን ስጠብቅ፡ ሴኬም፣ ከርኩሱ ምድረ ረጨኑ ጋራ፣ ወደቁ።... እኔ በላይኛና ታችኛ ግብጽ ንጉሥ በኑብካውሬ (2 አመነምሃት) ፳፯ኛው ዓመት (= 1912 ዓክልበ. ግ.) ተወለድኩ...»

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]