የዝባድ በሬ
Appearance
?የዝባድ በሬ | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
| ||||||||||||||
የዝባድ በሬ በተፈጥሮ (ቀይ) እና
ሰዎች አስገብተው (ሰማያዊ) የሚገኝባቸው ቦታዎች |
የዝባድ በሬ (ሮማይስጥ፦ Ovibos moschatus) በአርክቲክ ዙሪያ የሚገኝ የቶራ አስተኔ አባል ነው።
የዝባድ በሬ ወንድ ብርቱ ጠረን የሚሰጡ እጢዎች አሉት። ይህ ሴቶችን ለማዳራት ነው። ወንዶችም ሴቶችም ሁለት ረጅም፣ ጥምዝ ቀንዶች በራሳቸው ላይ አሏቸው። ወንዶችም ከደመነፍስ የተነሣ እርስ በርስ ለሴቶችም ሆነ ለሣር ቡጢ ያደርጋሉ።
የዝባድ በሬ የሚበላው ሣር፣ በለሴት፣ ሳርንስት፣ የአርክቲክ አኻያ ቊጥቋጥ፣ ወዘተ. ነው።
ዝባድ በሬን የሚበላው ነጣቂ በተለይ የአርክቲክ ተኲላ ነው። አልፎ አልፎ የዋልታ ድብ ወይም ቡናማ ድብ ድካሙን ይነጥቃል። በሚበዙበት ጊዜ፣ የሰው ልጅ ደግሞ ለሥጋው ያድናቸዋል።
በመንጋው ምናልባት 8-24 በሬዎች ይሆናሉ። ጥቃት ቢደርስባቸው፣ ለመከላከያ ፊታቸውን ወደ ውጭ አድርገው በክብ ነገር ቁመው የቀለበት ቅርጽ ይሠራሉ።
የተፈጥሮ መኖሪያቸው በስሜን ግሪንላንድና በስሜን ካናዳ ሲሆን፣ ከዚህ በላይ የሰው ልጆች ወደ አላስካ፣ ስካንዲናቪያና ሳይቤሪያ አስገብተዋቸዋል። አንዳንዴ ይህ የሚደረግ ለማደኑ እንዲበዙ ነው። በመላው ዓለም በጠቅላላ አሁን ምናልባት 125 ሺህ ያህል ዝባድ በሬዎች ይኖራሉ።
«ቂቪዩት» የተባለ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ሱፍ ይሰጣሉ። አልፎ አልፎ ብቻ የዝባድ በሬዎች ለሱፍ፣ ለወተትና ለሥጋ ለማዳ እንስሶች ተደርገዋል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |