Jump to content

ደብረ ፀሐይ ቍስቋም

ከውክፔዲያ
(ከደብረ ፀሐይ የተዛወረ)
የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም

ቁስቋም እልፍኝ - 1876 ዓ.ም. እንደተሳለ
ቁስቋም እልፍኝ - 1876 ዓ.ም.
አገር ኢትዮጵያ
ዓይነት ባሕላዊ
መመዘኛ c(ii)(iii)
የውጭ ማጣቀሻ 19
አካባቢ** አፍሪካ
የቅርስነት ታሪክ
ቅርስ የሆነበት ጊዜ 1971  (3ኛ ጉባኤ)
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም በኢትዮጵያ ካርታ
* በዩ.ኔ.ስ.ኮ ስሙ እንደሰፈረ።
** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል

ደብረ ፀሐይ ቍስቋምጎንደር ከተማ በስተ ስሜን ምዕራብ ወጣ ብሎ በሚገኘው ደብረ ፀሐይ የተባለ ተራራ ላይ የተሰራ የቤተክርስቲያንና ቤተመንግስት ግቢ ነው። ደብረ ፀሓይ ቁስቋም በእቴጌ ምንትዋብ፣ ከ1725 ዓ.ም. እስከ በ1738 ዓ.ም. ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ዙሪያው በግምብ የታጠረና በ8 እንቁላል ግንቦች የተከበበ ነው[1]። ግቢውን ሰንጥቆ የሚያልፍ ግምብ ደብሩን ለሁለት ሲከፍል አንዱ ጎን ቁስቋም ማርያም የተባለውን ቤተክርስቲያን ሲይዝ ሌላው ጎን ደግሞ የብርሃን ሞገሴን (ምንትዋብን) ቤተመንግስት፣ ስዕል ቤት የተባለውን የምትጸልይበትን ክብ ጸሎት ቤት፣ እንግዶች መጋበዣ ዕልፍኝ፣ ሰፊ የሰራተኞች ግምብ፣ የጄምስ ብሩስቤተመጻሕፍት ተብሎ የሚታወቀው ግምብና ለልዩ ልዩ ግልጋሎት የተመደቡ እንቁላል ግንቦችን ይይዛል። ደብረ ፀሐይ በተመሰረተበት ዘመን የራሱ ጉልት የነበረው ሲሆን ይኼውም በእብናትበለሳ እና አርማጭሆ ተሰባጥሮ ይገኝ ነበር፤ ስለሆነም 260 ቀሳውስትን በስሩ ያስተዳድር ነበር[2]፡፡

ግቢው ሦስት ጊዜ ጉዳት ደርሶበታል። በመጀመሪያ በ1858፣ ዓፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ሊያሰሩት ላሰቡት ቤተ ክርስቲያን ከቤተክርስቲያኑ የተለያዩ ንዋያትን መውሰዳቸው ነበር። ሁለተኛው ጉዳት የደረሰው በ1870ወች፣ የሱዳን ደርቡሾች ግቢውን በእሳት በማጋየት ያደረሱት ዋናው ጉዳት ነበር። በዚህ ቃጠሎ ቁስቋም ማርያም እንዳለ ሊቃጠል ችሏል። በ1932ዓ.ም. የእንግሊዝ ጦር በአውሮፕላን ቦምብ ስለጣለበት፣ እንዲሁ ተጨማሪ አደጋ ደረሰበት። ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ብዙ ጉዳት ሳይደርስበት ከሞላ ጎደል ተርፎ የሚገኘው አጥሩና እልፍኙ ነው[3]

-1px

1.ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም 2.የቤተክርስቲያን አለቃ መኖሪያ 3.ቁስቋም ዕቃ ቤት 4.ዋናው በር 5.ቤተ ላሕም 6.ስዕል ቤት 7.የምንትዋብ መኖሪያ 8.የምንትዋብ እልፍኝ 9.እልፍኝ በር 11.የቁስቋም ሰገነቶች

የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ግቢ ማውጫ
የቁስቋም እልፍኝ በአሁኑ ጊዜ
በወር አበባ ጊዜ ሴቶች ወደ ቤ/ክርስቲያን መከልከላቸውን ለማምለጥ እቴጌ ምንትዋብ ያሰራችው ስዕል ቤት ፍርስራሽ።
  1. ^ Stuart C. Munro-Hay, Ethiopia, the unknown land: a cultural and historical guide,I.B.Tauris, London, 2002 Page 156
  2. ^ Donald Crummey, Land and society in the Christian Kingdom of Ethiopia: from the thirteenth, page 168
  3. ^ Briggs, Philip, Blatt, Brian, Ethiopia, Legoprints SPA, Italy, 2009
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Category:Kuskwam የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።