ጋጃ

ከውክፔዲያ
ጋጃ

ጋጃ (Andropogon gayanus) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ሣር ተክል ነው።

እንግሊዝኛ ሣሩ በሐውዛኛ ስሙ «ጋምባ»፣ ወይም «ጋምባ ሣር» (ጋምባ-ግራስ) በመባል ይታወቃል።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በወፍራም እጅብታ እስከ 4 ሜትር ድረስ ይበቅላል። እጅብታው ባጋማሽ 70 ሰንቲ ሜትር ይደርሳል። ቅጠሎች 30-60 ሳንቲ ሜትር ረጅም፣ እስከ 3 ሳንቲ ሜትር ሰፊ፣ በለስላሳ ጽጉር ተሸፍነው፣ ባለ ልዩ ነጭ መሃል ጎድን ናቸው። አገዳዎችም ጉልበታም፣ በለስላሳ ጽጉር ተሸፈኑ። ሥሮቹ ከአፈር ገጽታ ሳይጠልቁ ከእጅብታው እስከ አንድ ሜትር ይርቃሉ። ዘሮቹ በጥጣማ V-ቅርጽ ባለ ጫፍ ይገኛሉ

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዝናባማ ወቅት ያድጋል፤ ዘሮቹን ያደርጋል። አንድ ተክል በአመት 244,000 ዘሮች ያስገኛል፣ 65% በህያዊነት። በንፋስ በቀላል ይበተናሉ፤ ሆኖም 90% ከተክሉ ከ5 ሜትር ርቀት በላይ አይወድቁም። በውሃ ወይም በመኪና ላይ ጭቃ ሊስፋፉም ይቻላል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ ዝርያ በተለይ ለአፍሪካ ገሞጂማ ሣርማ ቦታዎች ኗሪ ነው። በአውስትራሊያ ግን እንደ አስቸጋሪ ወራሪ አረም ይቆጠራል። ኗሪ ሣሮቹን በብዛት ከመተካቱ በላይ፣ በቀላሉ ስለሚቃጠል የእሳት አደጋ ይታስባል።

የሚገኙባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ከ980 ሜትር ከፍታ በታች፣ ከ400-1500 ሚሊሜትር ዝናብ በያመቱ የሚቀበሉ ቦታዎች ናቸው።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከብት ይሰማሩበታል።

በአንዳንድ ምዕራብ አፍሪካ ባህላዊ መድሃኒት ይጠቀማል። በማሊ ለድህረ-ወሊድ ሕማም፣ በናይጄሪያ ልጡም ለተቅማጥ መጠቀሙ ተዘገበ። የቅጠል ውጥ ግን ለሰውም ሆነ ለ ውሻ ለሚያስቀመጥ መድሃኒት ይሰጣል። በሞሪታንያ፣ ማሊ፣ ሴኔጋል ጠረፍ ለላሞች ለወተት ጉድለት ችግር ለማከም ይሰጣል። ከሌሎችም አትክልት ጋር የሚቀላቀልባቸው ዝግጅቶችም አሉ።[1]

የውጭ መያያዦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ «ፕሬሉድ» የምዕራብ አፍሪካ ባህላዊ መድሃኒቶች ዳታቤስ