ጠላ

ከውክፔዲያ

ጠላየኢትዮጵያ ባህላዊ መጠጥ ነው። ይህ መጠጥ ከገብስና ከጌሾ ተጠንስሶ የማሽላ፣ ዘንጋዳ፣ የጤፍ፣ የሰንዴ ወይም የዳጉሣ ቂጣ (እንኩሮ)በመጨመር የሚሠራ ሲሆን ከ2%-4% አልኮሆል ይዘት አው። ጠላ ከተጠመቀ በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ለመጠጣት ይደርሳል። ሆኖም ተደፍድፎ በቆየ ቁጥር እየበሰለና እየበረታ ስለሚሄድ ማቆየቱ ይመረጣል። በዚህም ምክንያት አፍለኛና ጥሩ የሚባሉ ደረጃዎች አሉት። ከዋናው የጠላ አይነት በተጨማሪ ሌሎች ሁለት አይነት ጠላዎች አሉ፣ እነርሱም

አስፈላጊ ነገሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

3 ፓውንድ ጌሾ 1 ½ ጋሎን ውሃ 3 ፓውንድ ገብስ 1 ፓውንድ ስንዴ

ጠላ ጠመቃ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጌሾውን ቅጠል ከግንዱ ይለያል። ጌሾው ከተፈጨ በኋላ ከ1 ጋሎን ውሃ ጋር ይደባለቃል። ቅይጡ 3 ጋሎን በሚይዝ በርሜል ወይንም ጋን ውስጥ ተከድኖ ይቀመጣል (የእንጨት በርሜል ይመረጣል)። ጋኑ ወይም እንስራው ለግማሽ ሰዓት በጥንጁት ይታጠናል።

ብቅል፡ ከስንዴ እንዲህ ይሰራል፦ ስንዴው ውሃ ውስጥ ለሶስት ቀን ይነገከራል። ስንዴው መብቀል ሲጀምር በጥብቅ የተከደነ እቃ ውስጥ ለ3 ቀን ይቀመጣል። በ3ኛው ቀን ስንዴው ይወጣና ፀሐይ ላይ ይደርቃል። ፀሐይ ካልወጣ ቀስ ብሎ በሚግል ምድጃ ላይ ተደርጎ እንዲደርቅ ይደረጋል። ከደረቀ በኋላ በደምብ እስኪልም ይፈጫል። ከላመ በኋላ እንጨቱ በርሜል ውስጥ ከጌሾው ጋር ይደባለቃል።

አሻሮ፡ ከገብስ ይሰራል። ገብሱ ጠቆር ያለ ቡኒ እስኪሆን ይቆላል። ከዚያ ሽፋኑን ለማስወገድ ይሸከሸካል። ሽፋኑ ከተወገደ በኋላ ገብሱ በደምብ እስኪልም ይፈጫል።

አነኩሮ (አንኩሮ)፦ የላመው አሻሮ ላይ ያልበዛ ውሃ ይደረግና ለስላሳ ሊጥ እንዲፈጥር ይደረጋል። ሊጡ ለ5-7 ደቂቃ በአንስተኛ ሙቀት ይጋገራል። ከዚያ እንዲቀዘቅዝ ይደረጋል። ይህ አንኩሮ የሚባለው ቂጣ ነው። ቂጣ በትናንሹ ይበጣጠስና ከእንጨቱ በርሜል ውስጥ አብሮ ይደባለቃል። ተጨማሪ የላመ ጌሾ በዚሁ ጊዜ ይገባል። ከዚያ በርሜሉ ይገጠማል። ለ8 ሰዓት ድብልቁ እንዲረጋጋ ይተውና በ8ኛው ሰዓት ግጣሙ ተከፍቶ ቀሪው ውሃ ይጨመርና ለ7-9 ቀናት ተከድኖ እንዲብላላ ይሆናል። ከዚህ በኋላ በጨርቅ (ሸማ) እየተጠለለ ጠላው መቀዳት ይጀምራል።

ቀሪውን ጠላ ቀዝቃዛ ስፍራ ውስጥ ወይም ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ ጥሩ ምክር ነው።[1]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ መስፍን፣ የኢትዮጵያ ልዩ አበሳሰል፡ ህዝብ፣ ባህል፣ እንግዳ ተቀባይነት