ጥር ፲፫

ከውክፔዲያ
(ከጥር 13 የተዛወረ)

ጥር ፲፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፴፫ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፪፻፴፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፪፻፴፪ ዕለታት ይቀራሉ።

ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፰፻፷፬ ዓ.ም.፣ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ (አባ በዝብዝ) በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስመ መንግሥታቸው "ዮሐንስ ራብዓዊ" (ዮሐንስ ፬ኛ) ተብሎ፣ በጳጳሱ በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እጅ ተቀብተው በሥርዓተ መንግሥት ንጉሠ ጽዮን፣ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ። በታሪክ እንደተመዘገበው በዚሁ ንግሥ ምክንያት ሦስት ቀን በዓል ሆኖ፣ ለግብር ፬ ሺህ ሰንጋ ታርዶ፣ ፶ ጉንዶ ማር የፈጀ፣ ፻፶ ሺህ ገንቦ ጠጅ ቀርቦ፣ በደስታ ሲበላ ሲጠጣ ሰንብቷል።
  • ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪቃ እግር ኳስ ውድድር የግብፅን ቡድን አራት ለ ሁለት አሸንፋ ዋንጫውን ተሸለመች። ለኢትዮጵያ ቀዳሚውን ግብ ያስቆጠረው የቴሌው ግርማ ዘለቀ ሲኾን፣ የጊዮርጊሱ መንግሥቱ ወርቁ በ፹፬ኛውና በ፻፲፯ኛው ደቂቃ ሁለተኛና አራተኛውን፣ ኢታሎ ቫሳሎ በ፻፩ኛው ደቂቃ ሦስተኛውን ለማስገባት ችለዋል። ያልተደገመውንና ሕዝቡም እየናፈቀ ያለው የአፍሪቃ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ያስገኙት ፩. ጊላ ሚካኤል ተስፋ ማርያም ፪. ክፍሎም አርአያ ፫. አስመላሽ በርሔ ፬. በርሔ ጎይቶም ፭. አዋድ መሐመድ ፮. ተስፋዬ ገብረ መድኅን ፯. ግርማ ዘለቀ/ተክሌ ኪዳኔ ፰. መንግሥቱ ወርቁ ፱. ሉቻኖ ቫሳሎ (አምበል) ፲. ኢታሎ ቫሳሎ ፲፩. ጌታቸው ወልዴ ሲሆኑ ተጠባባቂዎች ደግሞ ጌታቸው መኩሪያ፣ እስማኤል ጊሪሌ፣ ብርሃኔ አስፋው፣ ኃይሌ ተስፋ ጋብር፣ ነፀረ ወልደሥላሴ ነበሩ። አሰልጣኞች ይድነቃቸው ተሰማ፣ ፀሐየ ባሕረና አዳሙ ዓለሙ፣ ወጌሻው ጥላሁን እሸቴ ነበሩ፡፡

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ሪፖርተር፣ ኪንና ባህል - “ሳምንቱ በታሪክ”