ናራም-ሲን (አሦር)
Appearance
ናራም-ሲን የአሹር ንጉሥ ነበር። ምናልባት 1782-1730 ዓክልበ. አካባቢ ገዛ። የ2 ፑዙር-አሹር ልጅና ተከታይ ይባላል።
በሃቲ የነበሩት ካሩም (የንግድ ጣቢያዎች) አስቀጠለ። ወደ ዘመኑ መጨረሻ ግን (ምናልባት 1745 ዓክልበ. አካባቢ) የካሩም ንግድ ለ30 ዓመት ያህል እስከ ሻምሺ-አዳድ ዘመን ድረስ ተቋረጠ።
የናራም-ሲን ልጅ 2 ኤሪሹም ተከተለው።
የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።[1]
«የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» የተባለው ሰነድ ከዚህ ዘመን ጀምሮ የሊሙ ስምና ተጨማሪ የዓመት ድርጊቶች ይሰጣል።[2] እነዚህ የጎረቤቱ ነገሥታት አሚኑም (የኡኒና ንጉሥ)፣ 2 ኢፒቅ-አዳድ (የኤሽኑና ንጉሥ)፣ 1 ሻምሺ-አዳድ፣ እና የሌሎች ዘመቻዎች ይዘግባሉ። ይህም በታች ይመለከታል።
የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ደግሞ በዚህ ናራም-ሲን ዘመን የኢላ-ካብካቡ ልጅ ፩ ሻምሺ-አዳድ ወደ «ካርዱኒያሽ» (ባቢሎን) እንደ ሄደ፤ በኋላም በ1723 ዓክልበ. ከባቢሎን ወጥቶ ኤካላቱምን እንደ ያዘ፣ በ1720 ዓክልበ. አሹርንም ይዞ የአሦር ንጉሥ እንደ ሆነ ይዘግባል።
- 1782 ዓክልበ. - ኢናያ፣ አሙራያ ልጅ
- 1781 ዓክልበ. - ሹ-ሲን፣ ባቢሉም ልጅ
- 1780 ዓክልበ. - አሹር-ማሊክ፣ አላሁም ልጅ
- 1779 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ፣ ኢሊባኒ ልጅ
- 1778 ዓክልበ. - ኤና-ሲን፣ ሹ-አሹር ልጅ
- 1777 ዓክልበ. - አኩቱም፣ አላሁም ልጅ - «<...> ያዘ።»
- 1776 ዓክልበ. - ማጺሊ፣ ኢሪሹም ልጅ
- 1775 ዓክልበ. - ኢዲን-አሁም፣ ኩዳኑም ልጅ
- 1774 ዓክልበ. - ሳማያ፣ ሹበሉም ልጅ - «አሚኑም ሻዱፑምን ያዘ።»
- 1773 ዓክልበ. - ኢሊ-አሉም፣ ሱካሊያ ልጅ - «ሲን-አቡም ሲትን ምድር ያዘ።»
- 1772 ዓክልበ. - ኤናማኑም፣ አሹር-ማሊክ ልጅ
- 1771 ዓክልበ. - ኤናም-አሹር፣ ዱነያ ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ።»
- 1770 ዓክልበ. -ኤና-ሲን፣ ሹ-እሽታር ልጅ
- 1769 ዓክልበ. - ሃናናሩም - «አሚኑም ኢፒቅ-አዳድን ድል አደረገው።»
- 1768 ዓክልበ. - ዳዲያ / ካፓቲያ - «ኢፒቅ-አዳድ አሚኑምን ድል አደረገው።»
- 1767 ዓክልበ. - እሽመ-አሹር፣ ኤያዳን ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ ዚቁራቱምን ያዘ።»
- 1766 ዓክልበ. - አሹር-ሙታቢል፣ አዚዙም ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ <...> ።»
- 1765 ዓክልበ. - ሹ-ኒራሕ፣ አዙዛያ ልጅ
- 1764 ዓክልበ. - ኢዲን-አቡም - «ሲን-አቡም <...> ።»
- 1763 ዓክልበ. - ኢሊ-ዳን፣ አዙዋ ልጅ
- 1762 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ፣ ኢዲን-ኢሽታር ልጅ
- 1761 ዓክልበ. - ቡዚያ፣ አቢያ ልጅ
- 1760 ዓክልበ. - ዳዲያ፣ ሹ-ኢላብራት ልጅ - «የ1 ሻምሺ-አዳድ ልደት።»
- 1759 ዓክልበ. - ፑዙር-እሽታር፣ ኑር-ኢሊሹ ልጅ - «የጸሐይ ግርዶሽ ሆነ፤ አሚኑም ዓረፈ።»
- 1758 ዓክልበ. - ኢሳያ፣ ዳጋን-ማልኩም ልጅ
- 1757 ዓክልበ. - አቡ-ሻሊም፣ ኢሉ-አሉም ልጅ
- 1756 ዓክልበ. - አሹር-ረዒ፣ ኢሊ-ኤሙቂ ልጅ
- 1755 ዓክልበ. - ጣብ-አሹር፣ ኡዙዋ ልጅ
- 1754 ዓክልበ. - ሹ-ራማ፣ ኡዙዋ ልጅ
- 1753 ዓክልበ. - ሲን-እሽመአኒ
- 1752 ዓክልበ. - አሹር-ማሊክ፣ ሹ-ሃኒሽ ልጅ
- 1751 ዓክልበ. - ዳን-ኤያ፣ አቡ-ዋቃር ልጅ - «የሑፕሹም መያዝ»
- 1750 ዓክልበ. - ኤና-ሲን፣ ኢዲን-አቡም ልጅ - «ጐርፍ በሩቅ አገር»
- 1749 ዓክልበ. - አሹር-በላጢ
- 1748 ዓክልበ. - ኤና-ሲን
- 1747 ዓክልበ. - ኢቱር-አሹር
- 1746 ዓክልበ. - ሹ-በሉም - «ኢላ-ካብካቡ ሱፕሩምን ያዘ።»
- 1745 ዓክልበ. - ሻሩም-አዳድ፣ ቡዛዙ ልጅ - «የኤላም ሰው (ኩዱር-ማቡግ) ኢፒቅ-አዳድን አሸነፈ፤ ሻምሺ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ።»
- 1744 ዓክልበ. - ሹ-ላባን
- 1743 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ - «ሉሉ ንጉሡን በላዛፓቱም አሸነፉት።»
- 1742 ዓክልበ. - ዳዳያ - «ሙት-አቢህ <...>፤ ኢፒቅ-አዳድ አራጳን ያዘ።»
- 1741 ዓክልበ. - አህ-ሻሊም - «የጋሱር (ኑዚ) መያዝ»
- 1740 ዓክልበ. - ኡጹር-ሺ-እሽታር
- 1739 ዓክልበ. - ካታያ
- 1738 ዓክልበ. - ሹ-ሲን
- 1737 ዓክልበ. - አቡ-ሻሊም - «የሲን-አቡሱም ከነረብቱም መያዝ።»
- 1736 ዓክልበ. - ሹዳያ
- 1735 ዓክልበ. - ሹ-ዳዱም - «የነ<...> መያዝ።»
- 1734 ዓክልበ. - አሹር-ዱጉል - «ሻምሺ-አዳድ የኡኒኒ ሰው አሸነፈ፤ ሙት-ያ<...> አሸነፈ።»
- 1733 ዓክልበ. - ፑዙር-እሽታር - «ሻምሺ-አዳድ <...>።»
- 1732 ዓክልበ. - አታናህ - «ኢፒቅ-አዳድ <...> አሸነፈ፤ <...> ምድርን ያዘ።»
- 1731 ዓክልበ. - ኢሪሹም - «ሻምሺ-አዳድ <...>ን በዱር-<...> አሸነፈ።»
- 1730 ዓክልበ. - አሹር-ኤናም
ቀዳሚው 2 ፑዙር-አሹር |
የአሹር ገዥ 1782-1730 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 2 ኤሪሹም |
- ^ የመስጴጦምያ ነገሥታት (ፈረንሳይኛ)
- ^ የሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል