Jump to content

ዳግዳ

ከውክፔዲያ
የ17:41, 5 ሴፕቴምበር 2015 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ዳግዳ፣ ትክክለኛ ስሙ «ዮካይድ ኦላጣይር» በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቱዋጣ ዴ ዳናን ወገን የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። የፎሞራውያን ንጉሥ ኤላጣ ልጅና የብሬስ ወንድም ነበር። በሁለተኛው የማግ ትዊረድ ውግያ (1474 ዓክልበ. ግድም) ሴቲቱ ኬጥለን በመርዝ ቆሰለው። መርዙ ግን እጅግ ቀስ የሚል አይነት ነበር።

ሉግ በቱዋጣ ዴ ላይ ለ፵ ዓመታት ገዝቶ በ1434 ዓክልበ. የዳግዳ ልጅ ኬርማይት ከሉግ ሚስት ጋር ካመነዘረ በኋላ ሉግ ኬርማይትን ገደለው። የኬርማይትም ልጅ ማክ ኲል ቂሙን በቅሎ ሉግን ገደለው። በሉግም ፋንታ የማክ ኲል አያት ዳግዳ በዙፋኑ ተከተለው። ዳግዳ በኋላ እንደ አምላክ በመቆጠሩ በሥነ ጽሑፍ ስለርሱ ብዙ ሌሎች ትውፊቶች ይገኛሉ።

፹ ዓመታት ከገዛ በኋላ፤ የኬጥለን መርዝ ከ120 ዓመታት በኋላ በመጨረሻ ተከናወነና ገደለው ይባላል። በፈንታው የልጁ ኦግማ ልጅ ደልበህ በከፍተኛ ንጉሥነት ተከተለው።

ቀዳሚው
ሉግ
አይርላንድ (ባንባ) ከፍተኛ ንጉሥ
1434-1354 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ደልበህ