የሰበክ-ሁ ጽላት
Appearance
የሰበክ-ኹ ጽላት ከጥንታዊ ግብጽ መካከለኛው መንግሥት ከ3 ሰኑስረት ዘመን በ1893 ዓ.ም. የተገኘ ቅርስ ነው አሁን የሚታየው በማንቸስትር ሙዚየም በኢንግላንድ ነው።
ሰበክ-ኹ (ወይንም ኹ-ሰበክ) ከሰኑስረት ሥራዊት አንዱ መኮንን ወይም መቶ አለቃ እንደ ነበር ይገልጻል። ጽሑፉ ከሰበክ-ኹ መቃብር በአቢዶስ ነው የተገኘው። በጽሑፉ ውስጥ በከነዓን እና በኩሽ መንግሥት ላይ ስለ ተሳተፉባቸው ዘመቻዎች ይገልጻል።