Jump to content

ነፈርካሬ ቀቲ

ከውክፔዲያ
የ19:47, 29 ጁላይ 2018 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ነፈርካሬ ቀቲ ቶሪኖ ቀኖና በተባለው ጥንታዊ ፈርዖን ዝርዝር ዘንድ የግብፅ (ሄራክሌውፖሊስ) ፈርዖን ነበረ። ዘመኑ ምናልባት 2236-2232 ዓክልበ. ግድም ነበረ። ነገር ግን በዚህ መጀመርያ ጨለማ ዘመንሥነ ቅርስ ጉድለት ስላለ፣ ኅልውናውን የሚያረጋገጥ ቅርስ ገና አልተገኘም። ሌሎቹ ጥንታዊ ፈርዖን ዝርዝሮች የአቢዶስ ፈርዖን ዝርዝርና የሳቃራ ፈርዖን ዝርዝር አይጠቅሱትም።

በዚሁ 9ኛው-10ኛው ሥርወ መንግሥታት ከመሪብታዊ ቀቲ ቀጥሎ እና ከመሪካሬ አስቀድሞ ስንት ያሕል ነገስታት መቼ እንደ ገዙ በትክክል ለማወቅ አይቻልም። የቶሪኖ ቀኖና ለዚህ ጨለማ ዘመን ዋናው ምንጭ ሲሆን ሰነዱ ግን ፍርስራሽ ሆኖ ብዙ ቀዳዳዎች አሉበት። ከቶሪኖ ቀኖና ለዚህ ዘመን ሊነብ የሚችሉት ስሞች እንዲህ ናቸው፦ «ነፈርካሬ፣ ቀቲ...፣ ሰነን-...፣ ...ነፈርካሬ፣ መሪ-...-ቀቲ፣ ሸድ-...፣ ሕ...።» ከዚህ በላይ ብዙ ሌሎች ስሞች ከሰነዱ ጠፍተዋል። ነፈርካሬ በዚህ ሁለት ጊዜ አላለ፣ ምናልባት ሁለት ነፈርካሬ ቀቲዎች በዚህ ሥርወ መንግስት ነበሩ። ነገር ግን ምንም በእርግጥኝነት ሊባል አይችልም።

የነፈርካሬ ስም ትርጉም «መልካም (ነፈር) ነፍሰ (ካ) ፀሐይ (ሬ)» ነው።

በጨለማ ዘመን የተቀበረው የሄራኮንፖሊስ (3ኛው) እና ኤድፉ (2ኛው) ኖሞች ገዢ አንቅቲፊ በመቃብሩ ጽሑፍ አንድ የድሮ ንጉሥ «ካ-ነፈር-ሬ» ይጠቅሳል። ስለዚህ በአንዳንድ መምህር አስተሳሰብ፣ ይህ ካ-ነፈር-ሬ መታወቂያ ከቶሪኖ ቀኖና ነፈር-ካ-ሬ ጋር አንድላይ ሆኖ ለታሪካዊነቱ ማረጋገጫ ይበቃል።

ቀዳሚው
ሳ-... ቀቲ ?
ግብፅ ፈርዖን ተከታይ
?