Jump to content

ሃቢሩ

ከውክፔዲያ
የ16:14, 30 ዲሴምበር 2018 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ሃቢሩ የተጠቀሱባቸው አማርና ደብዳቤዎች (1369-1339 ዓክልበ.) ሁላቸው ከከነዓን ምድር ደርሱ።

ሃቢሩ ወይም አፒሩ ከ1600-1150 ዓክልበ. መካከል በከነዓን ዙሪያ የተገኘ በብዙ አገራት መዝገቦች የተጠቀሱት ብሔር ናቸው። ብዙ ጊዜ እንደ ቅጥረኞች ወይም ወታደሮች ይገለጻሉ።

  • 1587 ዓክልበ. ግ. - የሃቢሩ አለቃ ሰሙመ ከያምኻድ ንጉሥ እርካብቱም ጋራ ስምምነት አደረገ።
  • 1550 ዓክልበ. ግ. - የሶርያ ሑራውያን ቲኩናኒ ከተማ ንጉሥ ቱኒፕ-ተሹፕ በሥራዊቱ የተገኙት ሃቢሩ ስሞች በቲኩናኒ ፕሪዝም ላይ ሲዘረዝር፣ ብዙዎቹ ሑርኛ፣ የተረፉትም ሴማዊ ስሞች ነበሩዋቸው። (አንድ ስም ብቻ ካሥኛ ይታስባል)
  • 1500 ዓክልበ. ግ. - የሚታኒ መሥራች ኪርታ ዘመን ያሕል፤ የኡጋሪትኛ ጽሑፍ የከረት ትውፊት (1350 ዓክልበ.ግ. ተጽፎ) ኪርታን «የሐበር ንጉሥ» ይለዋል።
  • 1480 ዓክልበ. ግ. - ሐለብሚታኒ መንግስት ወድቆ አልጋ ወራሹ ኢድሪሚ ወደ ኤማርና ወደ ሃቢሩ ወገን ሸሸ።
  • 1473 ዓክልበ. ግ. - ሃቢሩ ከኢድሪሚ ጋር ተባብረው አላላኽን ለመያዝ እንደ ረዱት ይታወቃል።
  • 1465 ዓክልበ. ግ. - ፈርዖኑ 3 ቱትሞስ ሦስት ከተሞች በደቡብ ሊባኖስ ይዞ የሐቢሩ ዕደ-ጥበቦች እንዳገኘ ተዘገበ።
  • 1459 ዓክልበ. ግ. - 3 ቱትሞስ የፊንቄ ኡላዛ ወደብ ይዞ የሐቢሩ ወገን ሰዎች በዚያ እንዳገኘ ተዘገበ።
  • 1428 ዓክልበ. ግ. - 2 አመንሆተፕ ከሶርያ ዘመቻው በ89,600 ምርከኞቹ መካከል 3,600 ሃቢሩ ይቆጥራል።
  • 1369-1339 ዓክልበ. - የአማርና ደብዳቤዎች፦ በስሜኑ፣ አንዳንድ ሃቢሩ ከአሞራውያን አለቆች አብዲ-አሺርታና ልጁ አዙሩ ጋር ተባብረው የሊባኖስን ጠረፍ ከኡጋሪት ወደ ደቡብ እስከ ሲዶና ድረስ እየቃሙ ነበር። ወደ ደቡብም፣ ሃቢሩ ወገኖች ከሴኬም ንጉስ ላባያ ጋር ተባብረው ለጊዜው ሐጾርን ይዘው ብዙ ከነዓናዊ ከተሞች ከነመጊዶኢየሩሳሌም ለፈርዖን እርዳታ ይለምኑ ነበር።
  • 1360 ዓክልበ. ግ. - የኬጥያውያን ንጉሥ 1 ሱፒሉሊዩማ በጽላት ከጎረቤት አገራት አማልክት መካከል «የሃቢሩ አማልክት» እርዳታን ይለምናል።
  • 1320 ዓክልበ. ግ. - የኬጥያውያን ንጉሥ 2 ሙርሲሊ ባስታረቀ ስምምነት፦ «በባርጋ ምድር ሑራውያን ጃሩዋታን ከተማ ይዘው ለቴቴ አያት ለሃቢሩ ሰው ሰጡት፤ እኔ ግን ንጉሡን አቢራዳን ወደ ዙፋኑ መለስኩት።»
  • 1298 ዓክልበ. ግ. - የደብረ ያርሙታ አቢሩ በአንዱ መንደር ጥቃት ስላደረጉ ፈርዖኑ 1 ሴቲ ሥራዊቱን ልኮ ብዙ ተማረኩ።
  • 1282 ዓክልበ. ግ. - የቃዴስ ውግያ2 ራምሴስ በሥራዊቱ የሃቢሩ ፍላጻ ወርዋሪዎች ነበሩት።
  • 1188 ዓክልበ. ግ. - ኡጋሪት ከተማ በ«ባሕር ሕዝቦች» ወረራ ሲጠፋ፣ «ሃቢሩ» የጠቀሰ ሸክላ በእሳት እየተጋገረ ነበር። በሐላብ የተገኘ ወገን ነበሩ።
  • 1168 ዓክልበ. ግ. - 3 ራምሴስ ሃቢሩ ባርዮችና ሌሎች እንግዶች ለግብፅ ቤተ መቅደሶች ያከፋፈላል።
  • 1163 ዓክልበ. ግ. - 4 ራምሴስ 5000 ወታደሮች፣ 2000 የመቅደስ አገልጋዮችና 800 ሃቢሩ ወደ ዋዲ ሐማማት ድንጋይ መፍለጫ ላከ።

ሥነ ቅርስ የተረጋገጡት ብሔር በስማቸው «ሃቢሩ / አቢሩ» እና ዕብራውያንመጽሐፍ ቅዱስ ቢመሳሰሉም፣ ይህ ሀሣብ በመጽሐፍ ቅዱስ ከሃዲነት በተከተሉ ምዕራባውያንና አይሁዳውያን መምህሮች ዕጅግ ተከራካሪ ሆኗል።