Jump to content

ደምሳቸው ፈንታ

ከውክፔዲያ
(ከDemisachew Fenta የተዛወረ)

ደምሳቸው ፈንታ መንግስት / Demisachew Fenta Mengistአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ ወጀል በተባለች አነስተኛ ከተማ ሚያዚያ 23 ቀን 1977 ዓ.ም ተወለደ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን የጀመረው በደብረ ማርቆስ ከተማ ተክለሃይማኖት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። የ1ኛ እና 2ኛ ክፍል ትምህርቱን ተክለ ሃይማኖት ከተከታተለ በኋላ 3ኛ ክፍል ሲሆን ወጀል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ እስከ 8ኛ ክፍል ተማረ። በወቅቱ ማለትም በ1993 ዓ.ም በወጀል ከተማ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያልነበረ በመሆኑ ምክንያት 9ኛ እና 10ኛ ክፍልን ደጀን ከተማ በመሄድ "ጎጃም በር" አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። 11ኛ እና 12ኛ /የመሰናዶ/ ትምህርቱን ደግሞ ቢቸና ከተማ "በላይ ዘለቀ" አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል። በወቅቱም ዩኒቨርሲቲ የሚያሰገባ ውጤት ማምጣት በመቻሉ በ1997 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀላቀለ።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1999 ዓ.ም በትያትር አርትስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በአዋበል ወረዳ ማስታወቂያ ጽ/ቤት /በአሁኑ አጠራር "የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት"/ በፕሬስና ኢንፎርሜሽን ዴስክ ሃላፊነት ሠርቷል። በኋላም መንግስት በ2001 ዓ.ም ስራን መልሶ የማደራጀት /BPR/ ተግባር ሲያካሂድ በፕሬስ ዜናና ፕሮግራም የስራ ሂደት አስተባባሪነት ተመድቦ አገልግሏል።

ደምሳቸው መጋቢት 2001 ዓ.ም የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንን በጋዜጠኝነት የተቀላቀለ ሲሆን ከጀማሪ እስከ ከከፍተኛ ሪፖርተርነት አገልግሏል። በአሁኑ ወቅትም የአማራ ቴሌቪዥን የምርመራ ዘገባዎች አርታኢ/Editor በመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ በድርጅቱ ቆይታው፡-

  • በአማራ ራዲዮ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ የፕሮግራም ሪፖርተር
  • በበኩር ጋዜጣ የዜናና መጣጥፍ ከፍተኛ ሪፖርተር
  • በአማራ ቴሌቪዥን ትህምርታዊ ፕሮግራሞች ከፍተኛ ሪፖርተር
  • በአማራ ቴሌቪዥን የዶክመንታሪ ፕሮግራሞች ከፍተኛ ሪፖርተር
  • በአማራ ራዲዮ፤ ኤፍኤም ባህርዳር፤ ደሴና ደብረ ብርሃን ዜና አቅራቢነት
  • 2007 ዓ/ም ጀምሮ በአማራ ቴሌቪዥን በአዘጋጅነት (አርታዒነት)
  • ከሀምሌ 2008 ዓ/ም እስከ መስከረም 30/2010 ዓ.ም የአማራ ቴሌቪዥን ምክትል ዋና አዘጋጅ (Deputy Editor-in-Chief)
  • ከጥቅምት 1/2010 ዓ.ም እስከ ህዳር 30/2011 ዓ.ም የድርጅቱ የፕሮሞሽንና ገበያ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዲሁም
  • ከታህሳስ 1/2011 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ የአማራ ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ዋና አዘጋጅ
  • ከጥቅምት/2013 ዓም ጀምሮ ደግሞ በአማራ ቴሌቪዥን የምርመራ ዘገባዎች አርታኢ/Editor ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በ2005 ዓ.ም አዲስ ያሰራውን የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሲያስመርቅ በድርጅቱ የስራ ቆይታዉ ባሳየው የላቀ የስራ አፈጻጸም ከተሸለሙ የድርጅቱ ሰራተኞች አንዱ መሆን ችሏል። በዚህም ከምክትል ጠ/ሚንስትር ደመቀ መኮንን እጅ የምስጋና የምስክር ወረቀትና የማበረታቻ ሽልማት ተቀብሏል። በተጨማሪም የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በሰጠው ነፃ የትምህርት እድል አማካኝነት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ 2ኛ ዲግሪውን አግኝቷል።

ደምሳቸው በ2002 ዓ.ም ከወ/ሮ ሙሉእመቤት መልኬ ጋር ትዳር የመሰረተ ሲሆን መባ የተባለች ሴት ልጅ በጥር 16/2005 ዓ.ም ፤ ሮቤል የተባለ ወንድ ልጅ በጥር 09/ 2008 ዓ.ም እንዲሁም በነሃሴ 15/2012 ደግሞ ኪሩቤል የተባለ ወንድ ልጅ ወልደዋል፡፡