ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 2
Appearance
- ፲፩፻፹፬ ዓ/ም- በመስቀል ጦርነት የእንግሊዝ ንጉሥ ቀዳማዊ ሪቻርድ በሳላዲን ላይ በአርሱፍ ውግያ አሸነፈ።
- ፲፬፻፵፪ ዓ/ም - በቱሙ ምሽግ ውግያ የሞንጎል ሃያላት የቻይናን ንጉስ ማረኩ።
- ፲፭፻፮ ዓ/ም - የስኮትላንድ ንጉሥ ጄምስ ፬ኛ እንግሊዝን ወርሮ በፍሎደን ሜዳ ውግያ ተሸንፎ ሞተ።
- ፲፭፻፴፭ ዓ/ም - አምባ ሰሜን በተባለ ሥፍራ ላይ በቡርቱጋል ሠራዊት እና በአህመድ ግራኝ መኻከል በተካሄደው ጦርነት ላይ ዶም ክርስቶፍ ዳጋማ በጥይት ቆስሎ በግራኝ ወታደሮች ተማረከ።
- ፲፰፻፺ ዓ/ም - የዳግማዊ ምኒልክ የጦር አበጋዞች የከፋውን ንጉሥ ጋኪ ሸሮቾ በመማረክ ያንን መንግሥት ጨረሱ።
- ፲፱፻፴፭ ዓ/ም - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪቃን ስትቀርብ በጀርመኖች ተኩስ ሰመጠች።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ከ ፶፰ ዓመታት በሥልጣን፣ መጀመሪያ በአልጋ ወራሽነትና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነት፣ ከ መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በንጉሠ ነገሥትነት ኢትዮጵያን የመሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በደርግ የአብዮት ሥርዓት ተሽረው ከሥልጣን ወረዱ።
- ፲፱፻፸ ዓ/ም -የጸረ-አፓርታይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
- ፲፱፻፹፭ ዓ/ም - መይ ካሮል ጀሚሶን በጠፈር የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊት ሆነች።