Jump to content

ቶኪዳይደስ

ከውክፔዲያ
የቶኪዳይደስ ሃውልት፣ በቶሮንቶ ካናዳ

ቶኪዳደስ (452 – 387 ዓክልበ.) (ግሪክኛ፦ Θουκυδίδης /ቱኩዲዴስ/) የጥንታዊት ግሪክ ታሪክ ፀሐፊ ነበር። ቶኪዳደስ በተለይ የሚታወቀው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛው ክፍለዘመን ተደርጎ የነበረውን የስፓርታ እና አቴና ጦርነት ታሪክ ዘግቦ በማቆየቱ ነው። የፔሎፖኔዥያን ጦርነት ባለው በዚህ የታሪክ ዘገባ፣ የጦርነቱን መንስኤ እና ውጤት እስከ 411 ዓ.ም. በመከታተል ያቀርባል። ይህ የታሪክ ዘገባ ከአማልክትና ሌሎች ዝባ-ዝንኬዎች የጸዳና በጠራ ሁኔታ ከመንሴ-እና-ውጤትን ብቻ የሚተረትር የታሪክ ስራ ስለነበር የሳይንሳዊ ታሪክ አባት እንዲባል አስችሎታል።

በሌላ ጎን የአገሮች ግንኙነት በሃይል እንጂ በመብት ላይ የተመሰረተ እንዳልሆነ ስላስረዳ የእውን ፖለቲካ (ሪል ፖሊቲክ) አባት የሚባል ስም እንዲያገኝ አብቅቶታል። የቶክዲደስ ጽሑፎች አሁን ድረስ በከፍተኛ የውትድርና ተቋማት የሚጠና ሲሆን፣ የሜሊያን ወግ ብሎ የደረሰው ጽሑፉ እስካሁን ድረስ የአለም አቀፍ ግንኙነት ኅልዮት ውስጥ እንደ ቁልፍ ጽሑፍ ይወሰዳል።

በአጠቃላይ መልኩ፣ በቸነፈር፣ በእልቂት፣ እና በርስ በርስ ጦርነት ጊዜ የሚታዩት የሰው ልጅ ባህርያት መነሻቸው የሰው ልጅ ተፈጥሮ እንደሆነ ለማሳየት ሞክሯል። ታሪክን ከሥነ ምግባር ነጥሎ ከፖለቲካ አንጻር ብቻ ለማሳየት በመሞከሩ ከ ማካቬሊ እና ቶማስ ሆብስ ተርታ እንደ የእውን ፖለቲካ መስራች ይመደባል። በዚህ ተቃራኒ፣ ሄሮዶቶስ፣ ታሪክን ከአንድ መጥፎ ስራና ያንን ስራ ለመበቀል ከሚነሳ የምያባራ የበቀል ዑደት አንጻር ለማሳየት ሞክሯል። ይሄውም ታሪክንና ሥነ ምግባርን ያቆራኘ የትንታኔ አይነት ነበር።


ተጨማሪ ንባብ (እንግሊዝኛ)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የውጭ ድረ ገጾች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]