Jump to content

ደብረ ዳሞ

ከውክፔዲያ

ደብረ ዳሞ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው ። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል።

ከአለት የተፈለፈለ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ደብረ ዳሞ


ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ
አገር ኢትዮጵያ
ዓይነት አራት መዐዘን
አካባቢ** አዲግራት ፣ ትግራይ
የቅርስነት ታሪክ
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን ፮ኛው ክፍለዘመን 
ደብረ ዳሞ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ደብረ ዳሞ
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ
* የአለበት ቦታ
** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል

ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገምድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይዞ ይገኛል ። የተሰራውም በአቡነ አረጋዊ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ ወህኒአምባ ግሸን ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል። [1] የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የኖራ ድንጋይንና የጥድ እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በስነ ህንጻ ጥበበ አክሱማዊ ዘዴ አሰራር ይባላል።[2]

እዚህ አምባ ላይ የሰውም ሆነ የእንስሳ ሴቶች መውጣት አጥብቆ የተከለከለ ነው። ሆኖም ግን በግራኝ አህመድ ወረራ ወቅት ንግስት ሰብለ ወንጌል እና ደንገጡሮቻ እዚህ አምባ ላይ በመጠለል ከሞት ድነዋል። ተራራው ላይ ምንጭና እህል የሚዘራበት ሰፊ መሬት ስለነበር ፖርቱጋሎቹ እነ ክሪስታቮ ደጋማ ከአምባው ደርሰው ንግስቲቱ እንድትወርድ እስከአሳመኗት ድረስ የግራኝን ሰራዊት ከዚህ አምባ ላይ ሆና መከላከል ችላለች።



  1. ^ Thomas Pakenham, The Mountains of Rasselas (New York: Reynal & Co., 1959), pp. 79-86
  2. ^ Pakenham, p. 85