ሐመልማል አባተ
Appearance
ሐመልማል አባተ የኢትዮጵያ ታዋቂ ድምፃዊ ስትሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ትታወቃለች።
ሐመልማል ያደገችው አሰበ ተፈሪ ሲሆን ሙያዋን የጀመረችው በቤተ ክርስትያን ዘማሪ ሆና ነው።[1] የመጀመሪያው አልበሟ የወጣው በ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. ነው።[1]
ሐመልማል አባተ የሁለት ሴት ልጆች እናት ናት።[2][3]
ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በመካኒሳ መንገድ አቦ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ሐመልማል ቪላ ቤት በእሳት ቃጠሎ የወደመ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ ወደ ቤቱ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ መዋዠቅ እንደሆነ ይጠቀሳል።[4]
ከድምፃዊነትም አልፎ ሐመልማል የራሷን የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት አመል ፕሮዳክሽንስ በሚል ስም አቋቁማለች።[2] ከሙዚቃ ሥራ በተጨማሪም ሐመልማል በንግድ ዘርፍ በግንባታ ስራ እንዲሁም አመል ካፌ ተሞክሮ አላት። [3]
- ^ ሀ ለ Jossy In Z House
- ^ ሀ ለ አዲስ አድማስ፣ ድምፃዊ ሐመልማል አልበም አሳተመች የሞሃ ፔፕሲ ለአልበሙ ከግማሽ ሚ. ብር በላይ አውጥቷል
- ^ ሀ ለ ኢ.ቢ.ኤስ. ቴሌቪዥን «እንጫወት» ዝግጅት፣ ሐመልማል አባተ ቃለ መጠይቅ
- ^ Awramba Times፣ የአርቲስት ሐመልማል አባተ ቪላ በእሳት ቃጠሎ ወደመ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |