ሐምሌ ፲፰
Appearance
(ከሐምሌ 18 የተዛወረ)
ሐምሌ ፲፰
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፲፰ኛው እና የክረምት ፳፫ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፵፰ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፵፯ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በልዑል ራስ አስራተ ካሳ የሚመራ የኢትዮጵያ የፓርላማ ቡድን ከዩናይተድ ስቴትስ ፕረዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጋር በ ዋይት ሃውስ ተገናኝቶ ስለ ኢትዮጵያ ልማት፤ የኢትዮጵያና የሶማልያ ግጭት እንዲሁም በአፍሪቃ የፖርቱጋል ቅኝ ግዛቶችና ስለ ደቡብ አፍሪቃ ሁኔታ ተወያየ።[1]
- ፲፱፻፸ ዓ/ም - የመጀመሪያዋ የቤተ-ሙከራ-ጠርሙስ ጽንስ፣ ሉዊዝ ብራውን በዚህ ዕለት ተወለደች።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - ከፓሪስ ሻርል ደጎል ጥያራ ጣቢያ ለበረራ የተነሳው የፈረንሳይ 'ኮንኮርድ' ጥያራ (በረራ ቁጥር ፵፭፻፺) ከጥቂት የበረራ ጊዜ በኋላ ሲከሰከስ ተሣፋሪዎቹን በሙሉ እና አራት መሬት ላይ የነበሩ ሰዎችን፤ በጠቅላላው የ፻፲፫ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።
- (እንግሊዝኛ)