ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ

ከውክፔዲያ
ቅዱስ ባስሊዮስ
ከሦስቱ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባቶች አንዱ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ
የቄሣርያው ኤጲስ ቆጶስ
ስም ባስሊዮስ ዘቄሣርያ
የአባት ስም ቀዳማዊ ባስልዮስ
የእናት ስም ኤሚልያ
የተወለደው ፫፻፳፩ ወይም ፫፻፳፪ዓ.ም.
ያረፈበት ቀን ጥር ፮ ቀን ፫፻፸፩ ዓ.ም. በቀጰዶቂያ ሥንክሳር
የሚከበረው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

በኦርየንታል ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
በኮፕት ቤተክርስቲያን
በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
በአንግሊካን ኮሚዩነን ሉተራኒዝም
የንግሥ በዓል ጥር ፮ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ጄኑዋሪ ፩ና ፴ በቤዛንቲን ክርስቲያን
ጄኑዋሪ ፲፬ በሰርቢያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን
ጄንዋሪ ፪ በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
ታውት ፮ በኮፕት ቤተክርስቲያን


ባስሊዮስ ዘቄሣርያ በሌላ አጠራሩ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ (በግሪክ: Ἅγιος Βασίλειος ὁ Μέγας, Ágios Basíleios o Mégas) (በእንግሊዘኛ Basil of Ceasarea ሲነበብ ባዚል ኦፍ ሢዛሪያ)በቀጰዶቂያ የቄሣርያ ኤጲስ ቆጶስ ነበር ። የንቂያን የሊቃውንት ጉባዔ የሚደግፍና አርያኒዝምንና የአፖሊናረስን ተከታዮችን የክርስትና አመለካከት ተቃውሞ ትክክለኛውን መንገድ ያስተማረ ታላቅ አሳማኝ የሃይማኖት ፈላስፋና መሪ ነበር ።

ቅዱስ ባስሊዮስ ከሃይማኖት ፈላስፋነቱ ሌላ ድሆችንና ኑሮን ማሸነፍ ያቃታቸውን በመንከባከብ ይታወቃል ። በተጨማሪም የማኅበራዊ ኑሮ ፣ የሥርዐተ ጸሎትና የጉልበት ሥራ ለገዳማዊ ኑሮ መመሪያን መሥርቷል ። ባስሊዮስ ከቅዱስ ጳኩሚስ ጋር የማኅበራዊ ገዳማዊነት አባት ተብሎ በምሥራቃዊ ክርስትና ይታሰባል ። ዳሮግን በምሥራቅም በምዕራብም በቅዱስ ደረጃ ነው የሚከበረው ። እነዚህ ሁለት ጎራዎች ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት የሚለውን ስያሜ ከዮሐንስ አፍወርቅና ከግሬጎሪዮ ናዚያንዘስ ጋር ሰተውታል ።

የቀደመ የሕይወት ታሪኩና ትምህርቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባስሊዮስ ከቀዳማዊ ባስሊዮስና ከኤሚልያ የቄሣሪያዋ[1] በ፫፻፳ ዓም አካባቢ በቀጰዶቂያ ተወለደ[2] ። እናትና አባቱ እግዚአአብሔርን በጣም የሚወዱና ጸሎተኞች የነበሩ ሰዎች ነበሩ[3] ። የእናቱ አባት ከቆስጠጢኖስ ፩ኛ በክርስትና ማመን በፊት ሰማዕት ሆኖ ያለፈ ሰው ነበረ[4][5] ። ጸሎተኛ ባልቴቱ ማክሪናም የጎርጎርዮስ ታውማታርገስ (የኒዎ ቄሣርያን ቤተክርስቲያን በአቅራቢያው የመሠረተ)[6] ተከታይ የነበረች ባስሊዎስንና አራቱን ወንድሞቹንና እህቱን ፣ ወጣትዋ ማክሪናናውክራቲየስጴጥሮስ የሰባስቴውንናጎርጎርዮስ የኒሳውን (ወደፊት ታላቅና የተከበሩ ቅዱሳን የሚሆኑ) በክርስትና ሃይማኖት ሥርዐት አሳደገች ።

ባስሊዮስ በቄሣርያ ማዛካ ቀጰዶቂያ በአሁኑ ዘመን አጠራር ካይዜሪ (ቱርክ) ትምህርት ቤት በ፫፻፵፪ ፵፫ ዓ.ም.አካባቢ ተምሩዋል[7] ። እዛም ጎርጎርዮስ ናዚያንዘስን የረጅም ጊዜ ጉዋደኛ የሚሆነውን ተዋውቋል[8] ። ባስሊዮስና ጎርጎርዮስ አንድላይ በመሆን ለከፍተኛ ትምህርትና በተጨማሪ የሊባኒየስን ትምህርታዊ ንግግር ለማጥናት ወደ ቁስጥጥኒያ አምርተዋል ። ሁለቱ በአቴንስ በ፫፵፪ ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ ለስድስት ዓመት ተቀምጠዋል ። በዛም ቆይታቸው ጁሊያን ዘአፖስቴት ወደፊት ንጉሥ የሚሆን ተማሪ ተዋውቀዋል[9][10] ። ባስሊዮስ አቴንስን በ፫፵፰ ለቆ ወደ ግብፅና ሶርያ ከተጉዋዘ በኋላ አገሩ ቄሣርያ የሕግ ሥራ በመለማመድና የንግግር ችሎታ ሲያስተምር ቆየ[11]

የባስሊዮስ ሕይወት ኢውስታቲየስ የሴባስትን ኃይለኛ የማሳማን ችሎታና ጥሩ ግብረገብ ያለው[12]የተዋወቀ ጊዜ ሕይወቱ ሙሉበሙ ተቀይሩዋል ። ከዚህም የተነሳ ሕጋዊ የማስተማር ሥራውን ትቶ ሕይወቱን ለእግዚአብሔር ሰጠ ። ይህንንም የመንፈሳዊ ሕይወቱን መነቃቃት የሚያሳይ ጽሑፍ እንደሚከተለው አስቀምጦታል ፡

ብዙውን ጊዜዬን በማይረቡ ነገሮች አሳለፍኩ የወጣትነት ዕድሜዬንም በከንቱ ልፋትና እግዚአብሔር ሞኝነት ላደረገው ጥበብ ። በቅጽበት ከኃይለኛ እንቅልፍ ነቃሁ የወንጌልንም እውነተኛ ብርሃን አጥብቄ ያዝኩ የዚህንም ዓለም ንጉሦች ጥበብ ባዶነት ተረዳሁ [13]

ባስሊዮስ በአኔዚ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አኔዚ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የባስሊዮስ ዘቄሣርያ የሩሲያ ምስል

ከተጠመቀ በኋላ ባስሊዮስ በ፫፻፵፱ ዓ ም ወደ ፍልስጤምግብፅሶርያ እንዲሁም መስጴጦምያ የመመንኮስንና የገዳማዊነት ትምህርት ለማጥናት ሄደ ።[14][15] ያለውን ሐብት በሙሉ ለድሆች አድሎ እንደጨረሰ ወደ ምነና በፖንተስ ኒዎሢዛርያ (በዘመኑ አጠራር ኒክሳር ቱርክ) ቤተክርስቲያን ገባ ።[14] ባስልዮስ ይህን የገዳማዊ ኑሮ ቢያከብረውም ለሱ እንዳልተጠራ ተረዳ ።[16] የሴባስቴው እዩስታቴየስ እጅግ የታወቀ መኖክሴ በፖንተስ አካባቢ ባስሊዮስን ያስተምረው ነበር ። በዶግማ ላይ ግን ይለያዩ ነበር ።[17]

ይልቁን ባስሊዮስ በመንፈሳዊ ማኅበራዊ ኑሮ ተሳበና በ፫፻፶ በአስተሳሰብ ከእሱ ጋር የሚመሳሰሉትን የክርስትና ደቀመዝሙሮች ወንድሙን ጴጥሮስን ጨምሮ ማሰባሰብ ጀመረ ። አንድላይ ሆነው በቤተሰቡ ርስት ላይ አኔዚ አጠገብ ገዳም መሠረቱ ።[18] በጣም ግልፅ ለማረግ (በዘመኑ አጠራር ሶኑዛ ወይም ኡሉኮይ የዬሲሊርማክ ባሕርና የኬልኪት ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ማለት ነው ።)[19]. ባልተቤትዋ እናቱ ኤሚልያ ፣ እህቱ ማክሪናና ሌሎች ሴቶችም ራሳቸውን ለቅዱስ ተግባር መጽዋት በማድረግ ከባስሊዮስ ጋር ተባበሩ ። (ይህን ማኅበረሰብ የመሠረተችው እህቱ ማክሪና ናት የሚሉም አሉ) ። [20]

ቅዱስ ባስሊዮስ እዚህ ባታ ላይ ስለ ገዳማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ጽፎ ነበር ። ጽሁፉ ግን ለምሥራቃዊ ክርስትና ዕድገት ከፍተኛ ምክኒያት ሆንዋል.[21] በ፫፻፶ዓ ም ባስሊዮስ ጉዋደኛውን ጎርጎሪ (ግሬጎሪ) የናዚያነስን በአኔዚ እዲቀላቀል ጋበዘው። [22] ጎርጎሪዮም (ግሬጎሪ) እንደመጣ በኦሪጄን ፊሎካሊያ የኦሪጄን ሥራዎች ስብስብ ላይ ጥናት ማድረግ ጀመሩ ። [23] ከዚህም በኋላ ግሬጎሪ ወደ ናዚያነስ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ ወሰነ ።

ባስሊዮስ የቁንስጥጢናውን የሊቃውንት ጉባዔን ፫፻፶፪ ዓ ም ተሳተፈ ። በመጀመሪ ከኤዩስታቲየስና ከሆሞወሲያንስ ወገነ ፣ ግማሽ አራዊያን የሆነ የመናፍቅ ቡድን ፣ ወልድ ከአብ ጋር ተመሳሳይ እንጂ አንድ ባሕርዪ ወይም አካል አይደለም ብለው ከሚያስተምሩ ጋር ማለት ነው። [24] ሆሞወሲየንስ የአውኖሚየስን አርያኒዝም ይቃወማሉ ግን ደግሞ ከኒቂያ ጉባዔ ተከታዮች ጋር የሥላሴን አንድነት "ሆሞወሲዮስ" ከሚያስተምሩት ጋር መተባበር አይፈቅዱም ። በዚህም ቢሆን በዚያ የባስሊዮስ ጳጳስ ዲያኒየስ የቄሣሪያው የሚከተሉት የቀድሞውን ንቂያ ስምምነት ነበረ ። ባስሊዮስም ወዲያውኑ ሆሞወሲያንስን ጥሎ እንዲየውም ጠንካራ የኒቂያ ጉባዔ ውሳኔን ተከታይ ሆነ ። [24]

ባስሊዮስ በቄሣሪያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቄሣሪያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሦስቱ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባቶች ምስል: ታላቁ ባስሊዮስ (በግራ) ዮሐንስ አፈወርቅ (በመሐል) እና ግሬጎሪ ቴዎሎጂያኑ (በቀኝ)—ከሊፒ ታሪካዊ ሚይዚየም ሳኖክ ፖላንድ

በ፫፻፶፬ ዓ ም ጳጳሱ ሜለቲየስ የአንጾኪያው ባስሊዮስን ዲያቆን አድርጎ ሾመው ። አውሰቢየስ ደሞ በቄሣሪያ ቤተክርስቲያን በ፫፶፯ ዓ ም ፕሬስቢተር እንዲሆን ሾመው ። እኒህ የቤተክህነት ጥያቄዎች የባስሊዮስን ምርጫ የማይመጣጠኑ ስለሆኑ የሥራውን አቅጣጫ እንዲቀየር አድርገዋል ።[14]

ባስሊዮስና ግሬጎሪ ናዚያነስ ለጥቂት ዓመት የአርያኒዝም መናፍቅ ትምህርት የቀጰዶቂያን ክርስቲያኖች ይከፋፍላል ተብሎ ስለሚያሰጋ ሲታገሉ ቆዩ ። በኋላም የማሳመኛ ንግግር በትልቅ ደረጃ ውድድር (ክርክር) ከታዋቂ አርያውያን ቴዎሎጂየንና ተናጋሪዎች ጋር ለማድረግ ስምምነት አደረጉ ።[25]በንጉሥ ቫሌንስ ተወካዮች መሪነት ከተደረገው ክርክር በኋላም ግሬጎሪና ባስሊዮስ አሸናፊዎች ሆነው ወጡ ። ይህ መሳካት ለግሬጎሪና ለባስሊዮስ የወደፊት ሥራቸው በቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት መሆኑን አረጋገጠላቸው ።[25] ቀጥሎም ባስሊዮስ የቄሣሪያን ከተማ አስተዳደር ወሰደ ።[21] አውሰቢየስ ግን በባስሊዮስ ፈጣን እድገትና በማኅበረሰቡ ባገኘው ተቀባይነት በመቅናት ወደ ነበረበት የገዳም ብቸኝነት ኑሮ እንዲመለስ ፈቀደለት ። ቆይቶ ግሬጎሪ በዚም በዚያም ብሎ ባስሊዮስን እንዲመለስ አሳመነው ። ባስሊዮስም እንዳለው አደረገ በዚያችም ከተማ ለበርካታ ዓመት ውጤታማ አስተዳዳሪ ሆነ የተደነቀበትን ሥራ ሁሉ ለአውሰቢየስ ተወለት ።

በ፫፻፷፪ ዓ ም አውስቢየስም ሞተ ባስሊዮስም እንዲተካው ተመረጠ በዛውም ዓመት የቄሣሪያ ጳጳስ ሆነ ።[26] አዲሱ የቄሣርያ ጳጳስ ሹመቱ በተጨማሪ የፖንተስ ኤክስአርክና የሜትሮፖሊታን ጳጳስ (አምስት ጳጳሳትን የሚያካትት) ሲያስሰጠው ከአምስቱ አብዛኞቹ የአውስቢየስን ቦታ እንዲይዝ የማይፈልጉ ነበሩ ። ይህን ጊዜ ነው የሹመቱን ኃይል ለመጠቀም ያስፈለገው ።

ባስሊዮስ ለሃይማኖቱ የጋለ ስሜት ያለው ፣ ትዛዝ ሰጪ ደግና ለሰው አዛኝ ነበረ ። በዛም ወቅት ድርቅ ባስከተለው ረሐብ ምክኒያት በግሉ ምግብና መጠጥ በማዘጋጀት ለድሆች አድልዋል ፣ ያገኘውን የቤተሰብ ውርሱንም እንደዚሁ ድሆች እንዲጠቀሙ በነበረበት ቤተክርስቲያን አካባቢ አድልዋል ።

ባስሊዮስ ከብዙ የሃይማኖት መሪዎችና ቅዱሳን ጋር ደብዳቤ ተጻጽፍዋል ። ከ ደብዳቤዎቹም መካከል ያለማቋረጥ ሌቦችንና ሴቲኛአዳሪዎችን ለማዳን እንደሠራ የሚያሳዩ ይገኙበታል ። ከሱም ጋር የሚሠሩትን የቤተክህነት አገልጋዮች በሀብት ፍለጋ እንዳይፈተኑ በቀላል የካህን ኑሮ እንዲወሰኑና ብቁ የሆኑ የቤተክህነት ሠራተኞች ለቅዱስ ሥራ እራሱ ይመርጥ እንደነበር ያሳዩ ነበር ። ባለሥልጣኖችንም ፍትሕ ባጉዋደሉ ጊዜ ወይም ግዴታቸውን ባልተወጡ ጊዜ ከመተቸት ወደኋላ አይልም ነበር ። ይህን ሁሉ እያካሄደ በራሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሰፊ ማኅበረሰብ ምዕመናን ጠዋትና ማታ ያስተምርና ይሰብክ ነበር ። ከዚህ በላይ ከተባሉት በተጨማሪ ለብዙ ዓይነት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሆን በቄሣሪያ ባዚሊያድ (Basiliad)[27] የሚባል ሕንፃ ገንብቱዋል ። የሚያካትተውም ለምስኪኖች መኖሪያ ቤት ፣ ወደ መጨረሻ ዕድሜያቸው የደረሱ ሰዎች እንክብካቤ የሚደረግላቸው ቤትና የነዳያን ሐኪም ቤት ናቸው ። ግሬጎሪ ናዚያንዘስ አስተያየት ሲሰጥ የዓለም አስደናቂ ሥራዎች ብሎታል ። [28]

ስለ ሃይማኖቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ስለ እውነት ያለው ኃይለኛ አቋም በተቀናቃኙ ውስጥ ያለውን ጥሩ ነገር እንዳይታየው አልጋረደውም ፣ ስለሰላምና መታደግ ሲል መስማማት ያለእውነት መስዋትነት የሚገኝ ከሆነ የእውነት መለኪያውን ደስ እያለው አይጠቀምበትም ነበር ። በአንድ ወቅት ንጉሡ ቫሌንስ የአርያን ፍልስፍና ተከታይ የነበረ የመንግሥቱን ተወካይ ሞደስተስን ቢቻል በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከቀሪዎቹ የአርያን ቡድኖች ጋር እንዲስማሙ መልክተኛ አርጎ ወደ ባስሊዮስ ላከው ። የባስሊዮስ ግትር እምቢተኛነት ሞደስተስን "በዚህ ሁኔታ ማንም አናግሮኝ አያውቅም" ብሎ እዲናገር አረገው ። ባስሊዮስም ሲመልስ "ከጳጳስ ጋር ተደራድረህ አታውቅ ይሆናል" ብሎ መለሰለት ። ሞደስተስም ለአለቃው ለንጉሡ "ባስሊዮስ ኃይል እንጂ ሌላ ምንም አይመልሰውም" ብሎ ልኮለታል ። በወቅቱ ቫሌንስ ጦርነት እንደማይፈልግ ማንም ያውቅ ነበር ። ታዲያ በተደጋጋሚ ያልተሳካ ባስሊዮስን ከሥራው የማፈናቀል ሙከራዎች አደረገ ። ከዛም ራሱ ቫሌንስ ወደ ባስሊዮስ ቅዱሱን የጥምቀት በዓል በሚያከብርበት ዕለት መጣ ። በዛም ወቅት በባስሊዮስ በጣም ስለተደነቀ ለባዚሊያዱ ሕንፃ መሥሪያ መሬት ሰጠው ። ይህም መንግሥት በቤተክርስቲያን ላይ ያለውን ኃይል ወሰነው[29]

ይህም ደግሞ እያደገ በመስፋፋት ላይ ያለውን አርያኒዝምን እንዲጋፈጥ አስገደደው ። ይህ አርያኒዝም ክርስቶስን በተወሰኑ መልክ ከአባቱ ጋር አንድ መሆኑን የሚያስክድ ፍልስፍና እየሰፋ በብዙ አካባቢ ተቀባይነት ሲያገኝ በተለይ በአሌክሳንድሪያ ብዙዎች ስለሚያውቁት ለቤተክርስቲያን አንድነት በጣም አስጊ ምክኒያት ሆኖ ተገኘ[30] ። ባስሊዮስ በአትናቲዮስ እርዳታና ከምዕራብ ቤተክርስቲያን ግንኙነት በማድረግ ይህን የሆሞውሲያነስ ስሕተተኛነትና ያለመቀበል ያለውን ስሜት እውነት ለማረግ ብዙ ሞክሩዋል ። ችግሩ የመንፈስ ቅዱስን ማንነት ጥያቄ በመጣበት ጊዜ ተባብስዋል ። ባስሊዮስ ግን የመንፈስ ቅዱስን ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል መሆኑን በማስረጃ አጥብቆ ያስተምርና ይሰብክ ነበር ሆሞዋሲዮስንም ከሱ አስተምሮ ጋር አያስተካክላቸውም ነበር ። ለዚህ በመጀመሪያዎቹ ፫፻፷፫ ዓም በኦርቶዶክስ አክራሪ አባቶች ይነቀፍ ነበረ ። አትናሲዮስ ግን ይደግፈው ነበር ። ከዶግማቲክ ልዩነት በስተቀረም ከሴባስቴው እዩስታቲየስ ጋር ያለውን ጉዋደኝነት ጠብቋል ።

ባስሊዮስ ከጳጳሱ ዳማሰስ ጋር የጽሁፍ ልውውጥ በማድረግ ጳጳሱ መናፍቃን በምሥራቅም በምዕራብም እንዲወገዙ ተስፋ አድርጎ ነበር ነገር ግን የጳጳሱ ወላዋይ አቋም የባስሊዮስን ቆራጥነት አሳዝኖት ተስፋውን አድብዝዞበታል ።

ከሥራዎቹ በጥቂቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አባቶቻችን እንዳስተማሩን ቅዱሱ ሊቅ ከሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት አንዱ ነው ። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊንም ያስተማረው እርሱ ነው ። ነገር ግን ቅርብ ጊዜ ከድረ ገጾች ታሪክ እየገለበጡ የሚጽፉ አንዳንድ ወንድሞች ይህንን የሚያፋልስ ነገር ጽፈው ተመልክተናል ። ቅዱስ ባስልዮስ ገዳማዊ ጻድቅ፣ ባለ ብዙ ምሥጢር ሊቅ ፣ የብዙ ምዕመናን አባት፣ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት፣ ባለ ብዙ ተአምራትና ከከዊነ እሳት (ከፍጹምነት) የደረሰ አባት ነው ። ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳያንን ሆስፒታል በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያስገነባ እርሱ ነው። እጅግ ብዙ ድርሰቶች አሉት ። መጽሐፈ ቅዳሴውንም ዛሬ በምናውቀው መንገድ ያሰናሰለው እርሱ ነው። ለምዕመናን የሚጠቅሙ ብዙ ሥርዓቶችን ሠርቶ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተርጉሟል ፣ በየዕለቱም የሚጸለዩትን "ውዳሴ አምላክ" "የኪዳን ጸሎት" "ሊጦን" የተባሉትን መጸሐፍት የሚያካትት መጽሐፈ ጸሎትን ያዘጋጀ እሱ ነው ። እሱ በጻፋቸው መጸሐፍት ላይ ተመርኩዘው ብዙ አባቶች ጽፈዋል ። በመጽሐፈ ስንክሳር ጥር ፮ ቀን በሚነበበው የቅዱሳን ገድል ላይም የሠራው ታላቅ ተአምር ተጽፎ ይገኛል ። ታዲያ ይህ ሊቅ ቅዱስና ጻድቅ ሰው ብዙ ድንቆችን ሠርቷል ።

እረፍቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባሰሊዮሰ የፊት ገጽታ መዛባቱ ከመጠናቀቁ በፊት ሞተ።በጉበት በሽታ ተሠቃይቷል።ከልክ ያለፈ እርባናዊ ድርጊቶችም ለቀድሞ ሕይወቱ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።የታሪክ ምሁራን ባሰሊዮሰል በትክክል ስለሞተበት ቀን አይስማሙም።የቂሳርያ፣የፓቶኮፕተሪዮስ ወይም “ባዚሊያድ”፣እንደ ድሃ ቤት፣ ሆስፒታል እና ሆስፒታሎች ፊት ለፊት የነበረው ታላቁ ተቋም ለድሆች የባሰሊዮሰ ተከታታይ የምጽዓት መታሰቢያ ሆነ።ብዙዎቹ የቅዱስ ባሰሊዮሰል ጽሑፎች እና ስብከቶች በተለይም በገንዘብ እና በንብረት ላይ በተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ያሉትን ክርስቲያኖችን መፍታተናቸውን ቀጥለዋል።

ሰነ ጽሑፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፍሬስኮ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ ለቤተክርስቲያን የመጽዋት ድርሻውን ሲያቀርብ

የባስሊዮስ ዋና ሥነ-መለኮታዊ ጽሑፎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን በቀደመ የክርስትና ባህል (የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት ለማረጋገጥ) እና የእግዚአብሔር ፍራቻ ለሌለው ለኤውኖሚየስ የነቀፋ መጻሕፍት በ፫፻፶፮ ዓ.ም. ፣ የአኒሞኒያን የአሪያኒዝም ዋና ተዋናይ የሳይዛይከሱ ኤውኖሚየስን የሚቃወም ሦስት መጻሕፍት ። የመጀመሪያዎቹ ሦስት የማመሳከሪያ መጻሕፍት የእርሱ ሥራ ናቸው ፡፡ የአራተኛውና አምስተኛው መፅሃፍ ደራሲው ግን እንደ ተጠራጠረ ያስመስለዋል ። [31]

ባሲሊ ማኒ ኦፔራ ፩ሺ፭፳፫)

ባስሊዮስ ዝነኛ ሰባኪ ነበር ፣ ባብዛኛዎቹ ሰበካዎቹና የጾም ጊዜ ትምህርቶቹ በሄክሰሮንሮን (ማለት ፡ ሄክሳምሮስ ፣ “የፍጥረት ስድስት ቀናት”) ፣ በላቲን: (ሄክሳሮን) ላይ ያተኩሩ ነበር በተጨማሪም ለጸሎት የተጻፉ የዳዊት መዝሙሮች ከላይ እንደጠቀስናቸው ውዳሴ አምላክን የመሳሰሉ ጨምሮ በርካታ መጻሕፍት ይቀርባሉ ፡፡ አንዳንዶቹ በ፫፻፷ዎቹ ረሃብ ላይ ለሥነ ምግባር ታሪክ ዋጋ የሚሰጡ ናቸው ፣ ሌሎች ለሰማዕታት እና ለጽሑፍ ቅርሶች የተከፈለውን ክብር ያሳያሉ ። የጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ ጥናት ላይ ለወጣቶች የተላለፈው መልዕክት የሚያሳስበው ባስሊዮስ በመጨረሻ የራሱ አስተምህሮ በራሱ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረበት ያሳያል ፣ ይህም የጥንታዊ ሥነ-ጽሑፋዊ ጠቀሜታ አድናቆት እንዲያድርበት አድርጎታል።

በትርጓሜው ውስጥ ባሰሊዮሰ ለኦሪጀን እና ለቅዱሳት መጻሕፍት መንፈሳዊ ትርጓሜ አስፈላጊነት ከፍተኛ አድናቆት ነበረው ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሥራው ላይ “ቀጥተኛውን ቃል ወስዶ እዚያ ለማቆም ፣ በአይሁዲዝም ሥነ-ጽሑፍ መሸፈኛ ልብ መሸፈን ነው” የሚል ማረጋገጫ ሰጥቷል ፡፡ መብራቶች ፀሐይ በምትበራበት ጊዜ ከንቱዎች ናቸው ፡፡ እርሱ በመሠረተ ትምህርት እና በቅዱስ ቁርባን ጉዳዮች ውስጥ የመጠባበቂያ አስፈላጊነት ደጋግሞ አበክሮ ገልጽዋል ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ የአንዳንድ ዘመናትን የዱር ቅኝቶች ይቃወም ነበር። ይህን በተመለከተ ፣ እንዲህ ሲል ጽፍዋል :

እኔ በሌላው ሥራ በበለጠ በእኔ ሥራ ያነሰ በሚሆን የተዘበራረቀ የምሳሌ ህጎችን አውቃለሁ ፣ በርግጥም አሉ የቅዱሳት መጻሕፍትን የጋራ ስሜት የማይቀበሉ ፣ ውሃን ውሃ አይደለም የሚሉ ፣ በአንድ ተክል ውስጥ ወይም ዓሳ ውስጥ የራሳቸውን የደስታ ምኞቶች የሚያዩ ፣ የእንስሳዎችን እና የዱር አራዊትን ተፈጥሮ ለምሳሌዎቻቸው እንዲስማሙ አድርገው ለውጠው ከግምትዎቻቸው ጋር እያስማሙ ምሳሌዎች የሚጽፉ ፣ እንደ ሕልም አስተርጓሚዎች ሕልሞችን የራሳቸውን መጨረሻ እንዲያገለግሉ የሚያደርጉ ።[32]

የእሱ የመራባት ዝንባሌ በሞራሊያ እና በደኢታካ (አንዳንዴም የቅዱስ ባሰሊዮሰ ህጎች በተተረጎመው) እና በሥርዓት በዓለም ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ የሥነ-ምግባር መመሪያዎች ይታያሉ ፡፡ የታላቁ አስኬቲከን እና አናሳ አስኬቲከን የተባሉትን የሁለቱ ሥራዎች ትክክለኛነት በተመለከተ ጥሩ ውይይት ተደርጓል ፡፡ [17]

የእሱ ሥነ-መለኮታዊ ተግባራዊ ገጽታዎች የተገለፀው በሥነ-ጽሑፍ ጽሑፎች እና በሞራል ስብከቶች ውስጥ ነው ፡፡ ስለዚህ ፣ ለምሳሌ ፣ የጎረቤቶቻችንን ተፈጥሯዊ ፍላጎቶች (ለምሳሌ ፣ ረሀብ ፣ ጥማትን) እንደራሳችን አድርገን እንድንመለከት የሚረዳን የጋራ ተፈጥሮአዊ ተፈጥሮአችን እንደሆነ ያስረዳናል ። ምንም እንኳን ሌላ ግለሰብ ቢሆን

ሦስት መቶ ደብዳቤዎች ፣ በሽታ እና ቤተክርስቲያናዊ አለመረጋጋት ችግሮች ቢኖሩም ተስፋ ሰጭ ፣ ርህራሄም እና ተጫዋች የነበረ ፣ ሀብታም እና ታዛቢ ተፈጥሮውን ያሳያሉ። እንደ አንድ የማሻሻል እርምጃ ዋና ተግባሩ የሕግ ሥነ-ሥርዓቱን ማደስ እና የምስራቅ ገዳማትን ተቋማት ለውጥ ለማምጣት ነበር ፡፡

አብዛኛዎቹ የእሱ ሥራዎች እና ለእሱ በጥቂቶች የተጻፉ ናቸው የተባሉት የተለያዩ ጥራት ያላቸው የላቲን ትርጉሞችን በሚያካትተው ፓትሎሎጂ ግሪካ ውስጥ ይገኛሉ። በርከት ያሉ የቅዱስ ባሰሊዮሰ ሥራዎች በሃያኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በእነ ሶርስ ክሪኔኔስ ክምችት ውስጥ ይታያሉ ፡፡

የባሰሊዮሰ ሃውልት, በምራባውያን አለባበስ ፡ በኒኮለሰ ቤተክርስቲያን ፤ ማላ ስትራናፕራግቼክ ሪፓብሊክ.

ሥነ-ምግባራዊ አስተዋፅዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በስደት ዘመን ማብቂያ ላይ እንደመጣ ፣ የቂሳርያ ባስሊዮስል በክርስቲያናዊ ሥነ-ስርዓት ታሪክ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ቦታን ይይዛል ፡፡ የባስሊዮስል ሥነ ምግባራዊ ተጽዕኖ በቀደሙት ምንጮች ውስጥ በሚገባ ተረጋግጥዋል ፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ስሙን የሚሸከሙት መለኮታዊ ሥነ- ሥርዓት የትኞቹ ክፍሎች በትክክል እንደሆኑ ማወቅ ከባድ ቢሆንም በብዙዎች የምሥራቅ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የተመዘገቡት የጸሎት አካላት እጅግ ፀንተዋል ፡፡

የባሲል ስም የሚሸከሙት አብዛኞቹ [ሥነ ስርዓት | ሥነ-ሥርዓቶች] አሁን ባሁኑ መልኩ ሙሉ ሥራቸው አይደሉም ፣ ሆኖም ግን በዚህ መስክ ውስጥ የ ባስሊዮስል ሥነ ሥርዓቶችን በማዘጋጀት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝማሬዎችን በማስተዋወቅ ረገድ የተከናወኑትን ሥራዎች ለማስታወስ ይረዳሉ ፡፡ የክርስትና ሃይማኖት አዋቂዎች ፣ የቅዱስ ባስሊዮስል ሥነ ሥርዓት “የታላቁ የቅዱስ ባሲል የግል እጅ ፣ ብዕር ፣ አዕምሮ እና ልብ” ያለአንዳች ስሕተት ያሳያል ።[33]

ለእሱ ሊባል የሚችል ሥነ-ስርዓት" የቅዱስ ባስሊዮስል ሥነ-መለኮታዊ ሥነ-ስርዓት)"፣ ብዙ ጊዜ ከተለመዱት ከቅዱስ ዮሐንስ አፍወርቅአገልግሎት የሚረዝም ሥነ-ስርዓት ነው ። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ዋናነት ካህኑ በሚያደርገው በጸጥታ ፀሎቱ ላይና ለ ቴዎቶኮስየሚያደርገው ዜማና ቃላት ነው ፣ ‹ፍጥረት ሁሉ› በሚለው ምትክ ፣ ኤክስዮን ኤንቲን የሚለውን የዮሐንስ አፍወርቅን ሥነ-ሥረት ይጠቀማል ። የዮሐንስ አፍወርቅ ሥነ ስርዓት በአብዛኛዎቹ ምስራቃዊው ኦርቶዶክስ እና የባዛንታይን ካቶሊክ ሥነ ሥርዓታዊ ባህሎች ውስጥ የባስሊዮስን ለመተካት መጥቷል ፡፡ ሆኖም ፣ አሁንም በተወሰኑ የበዓላት ቀናት ላይ የባሲል ሥነ-ስርዓት ይጠቀማሉ ፥ የመጀመሪያዎቹ የዐብይ ፆም አምስት እሑዶች ፣ የ ልደት ዋዜማ እና ቴዎናን ፣ በፀሎተ ሐሙስ እና ቅድስት ቅዳሜ እና በጃንዋሪ ፩ የባስሊዮስ ቀን (በ ጁሊያን የቀን መቁጠሪያ የሚከተሉ አብያተ ክርስቲያናት ጄንዋሪ ፲፬ በ የግሪጎሪያን የቀን መቁጠሪያ ላይ ይወድቃል]])።

በሞናስቲዝም(ገዳማዊ ኑሮ) ላይ ያለው ተጽዕኖ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በእሱ ምሳሌዎች እና ትምህርቶች መሠረት ባስሊዮስል ከዚህ በፊት በምነና ሕግ ማለትም የገዳም ኑሮ ባሕርዪ አመለካከት የነበሩትን ልዩነት ማንንም በማያስቀይም ደረጃ አሻሽሎ አሳይቷል ፡፡ ሁለቱን አጣምሮ የሚይዝ የ ሥራና ፀሎት ቅንጅት ያለው አሠራር በመፍጠሩ ይታወቃል ። [34]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Quasten(1986), p. 204.
  2. ^ Bowersock et al. (1999), p.336
  3. ^ Oratio 43.4, PG 36. 500B, tr. p.30, as presented in Rousseau (1994), p.4.
  4. ^ Davies (1991), p. 12.
  5. ^ Rousseau (1994), p. 4.
  6. ^ Rousseau (1994), p. 12 & p. 4 respectivel
  7. ^ Hildebrand (2007), p. 19.
  8. ^ Norris, Frederick (1997). "Basil of Caesarea". in Ferguson, Everett. The Encyclopedia of Early Christianity (second edition). New York: Garland Press 
  9. ^ Ruether (1969), pp. 19, 25.
  10. ^ Rousseau (1994), pp. 32–40.
  11. ^ Rousseau (1994), p. 1.
  12. ^ Hildebrand (2007), pp. 19–20.
  13. ^ Basil, Ep. 223, 2, as quoted in Quasten (1986), p. 205.
  14. ^ Quasten (1986), p. 205.
  15. ^ Encyclopædia Britannica (15th ed.) vol. 1, p. 938.
  16. ^ Merredith (1995), p. 21.
  17. ^ McSorley, Joseph. "St. Basil the Great." The Catholic Encyclopedia Vol. 2. New York: Robert Appleton Company, 1907. 31 May 2016
  18. ^ Encyclopædia Britannica (15th ed.) vol. 1, p. 938.
  19. ^ mod. Yeşilırmak and Kelkit Çayi rivers, see Rousseau (1994), p. 62.
  20. ^ The New Westminster Dictionary of Church History: The Early, Medieval, and Reformation Eras, vol.1, Westminster John Knox Press, 2008, መለጠፊያ:ISBN, p. 75.
  21. ^ Attwater, Donald and Catherine Rachel John. The Penguin Dictionary of Saints. 3rd edition. New York: Penguin Books, 1993. መለጠፊያ:ISBN.
  22. ^ Rousseau (1994), p. 66.
  23. ^ Merredith (1995), pp. 21–22.
  24. ^ Meredith (1995), p. 22.
  25. ^ McGuckin (2001), p. 143.
  26. ^ Meredith (1995), p. 23
  27. ^ The Living Age. 48. Littell, Son and Company. 1856. p. 326. https://books.google.com/?id=cxAuAAAAYAAJ&lpg=PA326&dq=%22Basiliad%22&pg=PA326#v=onepage&q=%22Basiliad%22&f=false. 
  28. ^ Gregory of Nazianzus. Oration 43: Funeral Oration on the Great S. Basil, Bishop of Cæsarea in Cappadocia. p. 63. http://www.newadvent.org/fathers/310243.htm በ20 February 2016 የተቃኘ. 
  29. ^ Alban Butler; Paul Burns (1995). Butler's Lives of the Saints. 1. A&C Black. p. 14. ISBN 9780860122500. https://books.google.com/?id=XIEAD2MC1YkC&lpg=PA14&dq=%22Basiliad%22%20%22Valens%22%20%22modestus%22&pg=PA14#v=onepage&q=%22Basiliad%22%20%22Valens%22%20%22modestus%22&f=false. 
  30. ^ Foley, O.F.M., Leonard (2003). "St. Basil the Great (329–379)". in McCloskey, O.F.M., Pat (rev.). Saint of the Day: Lives, Lessons and Feasts (5th Revised Edition). Cincinnati, Ohio: St. Anthony Messenger Press. ISBN 978-0-86716-535-7. http://www.americancatholic.org/Features/SaintOfDay/default.asp?id=1248 በ2007-12-15 የተቃኘ. 
  31. ^ Jackson, Blomfield. "Basil: Letters and Select Works", Nicene and Post-Nicene Fathers, (Philip Schaff and Henry Wace, eds.) .T&T Clark, Edinburgh
  32. ^ Basil. "Hexameron, 9.1". in Schaff, Philip. Nicene and Post-Nicene Fathers (2nd Series). 8 Basil: Letters and Select Works. Edinburgh: T&T Clark (1895). p. 102. http://www.ccel.org/ccel/schaff/npnf208.viii.x.html በ2007-12-15 የተቃኘ . Cf. Hexameron, 3.9 (Ibid., pp. 70–71).
  33. ^ Bebis (1997), p. 283
  34. ^ Murphy (1930), p. 95.