Jump to content

በርበር ማርያም

ከውክፔዲያ
{{{ስም}}}
በርበር ማርያም በአሁኑ ቅርጹ
ከፍታ 2750 ሜ
በርበር ማርያም is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}

6°19′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

በርበር ማርያም በጥንቱ የጋሞ ግዛት ውስጥ ይገኝ የነበር ቤተክርስቲያንና ተራራ ስም ነው። በቀዳማዊ አፄ ምኒሊክ ከክርስቶስ ልደት በፍት በ960ዎቹ ሙኩራበ አይሁድ ሆና እንደተቆረቆረች፣በ328ዓ.ም በሮም ንጉሥ ቆስጢንጢኖስ እና የኢትዮጵያ ንጉሥ አፃ እዛና ዘመን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት ተቀበለች፣በ526ዓ.ም በአቡነ አረጋዊ በቅዱስ ያሬድ ክርስትና እንደገና አጠናከሩ፡፡በ1522ዓ.ም በአፄ ልብነ ድንግል እንደተገደመች የተመዘገበው [1]ይህ ቤተክርስቲያን ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከጥቅም ውጭ ሆን ሳለ በ1886 ዓ.ም. ራስ ወልደ ጊዮርጊስ አክባቢውን ሲቆጣጠሩ እንደገና ሊያንሰራራ ችሏል[2]

ቤተ ክርስቲያኑ የሚገኝበት በርበር ማርያም ተራራ 2750 ሜተር ክፍታ ሲኖረው፣ ከአባያ ሐይቅ በስተምዕራብ ይገኛል[3]። የፈረንሳዩ ቅርስ ተማሪ ቻቆት እንደዘገበ፣ የጥንቱ ቤተክርስቲያን በ1530ዓ.ም. በግራኙ መሪ ሙጃሂድ/ግራኝ መሐመድ የተቃጠለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የጥንቱ ቤተክርስቲያን ቅሪት በቦታው አይገኝም ብሏል። አባ ባሕርይ የተሰኙት የኦሮሞን ታሪክ የጻፉ መነኩሴ፣ ወደ ዓፄ ሠርፀ ድንግል አገልግሎት የገቡት ከዚሁ ቦታ መወረርና መሰደድ በኋላ ነበር[4]

በዚህ ሁኔታ አካባቢው ለ239 ዓመት ከቆየ በኋላ፣ የአካባቢው ሰዎች በአቅራቢያ በሚገኙ ዋሻወች ውስጥ የደበቋቸው የቤተክርስቲያን መገልገያ እቃዎች፣ ታቦታት፣ ጥንታዊ መጽሐፎች በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደገና ሊገኙ ችለዋል። በዘመነ መሳፍት ማግስት በ1769ዓ.ም እንደጥንቱ እንደገና በርበር ተራራው ላይ ተሠርቷል፡፡ በተጨማሪ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ የዚህ የጥንቱ መጽሕፍት ግልባጭ እንዲጻፍና፣ እንድጠነክር ተደረገ፡፡ በደጊሞተ ላይ በጠፋው ቤተክርስቲያን ቦታ አዲስ ቤተክርስቲያን በ1870ዓ.ም እንዲሰራ እንዳደረጉ የንጉሱ ዜና መዋዕል ያትታል[5]። አፄ ምንሊክ በነበሩበት ዘመን ቤተክርስቲያኑ ድረስ የተጓዙ ሲሆን፣ በዚያ ዘመን ይገኝ የነበረው የወርቅና የብር ቅርሳቅርስ እንዲሁም የነገስታት ተክሊል አሁን ተመዝብሮ ጠፍቷል[6]

  1. ^ መጽሐፈ ታሪክ ዘሀገረ ገሞ
  2. ^ Caquot André. Note sur Berber Māryām. In: Annales d'Ethiopie. Volume 1, année 1955. pp. 109-116, internet
  3. ^ Caquot André. Note sur Berber Māryām. In: Annales d'Ethiopie. Volume 1, année 1955. pp. 109-116, internet
  4. ^ Paul T. Baxter, Encyclopaedia Aethiopica", volume 1, edited by Otto Harrassowitz Verlag, (2003)
  5. ^ Caquot André. Note sur Berber Māryām. In: Annales d'Ethiopie. Volume 1, année 1955. pp. 109-116, internet
  6. ^ http://www.eotc-mkidusan.org/English/SaintsAndHolly/index_February19_2009.ht