Jump to content

ባይ-ዩዕ

ከውክፔዲያ
የቻይና ሃን ሥርወ መንግሥት ዘመቻዎች በባይ-ዩዕ እና በሥዮንግ-ኑ ላይ 200-100 ዓክልበ. ግድም

ባይ-ዩዕ (ቻይንኛ፦ 百越) ወይም «መቶ ዩዕ» በጥንት (ቢያንስ ከ1200 ዓክልበ.) በደቡብ ቻይና እና ስሜን ቬትናም የተገኙት ብሔሮች ነበሩ።

የዩዕ መንግሥት ሐውልት

ባሕላቸው ያንጊዜ ከቻይና ሰዎች ባሕል በጣም እንደ ተለየ ይታወቃል። ከሩዝ በቀር ብዙ እርሻ አላደረጉም፤ በማደንና በተለይ አሣን በማጥመድ ይኖሩ ነበር፤ እንዲሁም የውሃ ጎሽን ለማዳ አደረጉ። ጎጆቻቸውን በምርኩዞች ላይ ይሠሩ ነበር፣ ጸጉራቸውን ያቋርጡና በቆዳቸው ንቅሳት ያድርጉ ነበር፤ ቻይናዎች ግን ያንጊዜ የኮንግ-ፉጸ ተከታዮች ሆነው ጽጉራቸውን አላቋረጡም፣ ንቅሳት አላደረጉምና ስለዚህ የባይ-ዩዕ ሕዝቦችን እንደ አረመኔዎች ያህል ይቆጥሯቸው ነበር። የዩዕ መንግሥታት ግን ጥራት ያለውን መርከብ እና ሠይፍን በመሥራት አንጋፋዎች ሆኑ፤ አገራቸውም በሉልዕጣንዝሆን ጥርስአውራሪስ ቀንድ፣ ኤሊ ዘጎል፣ ዛጎል ድንጋይብቅበቃጣውስ ዕጅግ ሀብታም ነበረ።

ለቋንቋቸው ትንሽ ናሙና ቢኖረን ከዘመናዊ ቋንቋዎች መካከል የትኛውን እንደ መሠለ ስላለው ጥያቄ አንዳንድ ክርክሮች አሉ። እንደ ዘመናዊ ቬትናምኛ እንዳልመሠለ ግልጽ ነው።