ታኅሣሥ ፫

ከውክፔዲያ
(ከታኅሣሥ 3 የተዛወረ)

ታኅሣሥ ፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፪ ቀናት ይቀራሉ።

ይቺ ዕለት በኢትዮጵያ ታሪክ ሁነኛ ስፍራ አላት። ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክና የጦሩ ፊታውራሪ፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ ያረፉበት ዕለት ናት፡፡ ዕለቱ ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ሁለቱ ያረፉት በተለያዩ ዓመታት ነው፡፡ ‹‹አባ ዳኘው›› የተባሉት፣ ዳግማዊ ምኒልክ ፳ኛው ምዕት ዓመት በባተ በስድስተኛው ዓመት ላይ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. ሲያርፉ ‹‹አባ መላ›› የተሰኙት ፊታወራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ደግሞ በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈዋል። ዓመታቱ ይለያዩ እንጂ ሁለቱም ያረፉት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፬ ዓ/ም የቀድሞዋ የሕንድ ርዕሰ ከተማ ካልከታ በአዲሷ ደልሂ ተተካች። በዚሁ ዕለት የብሪታንያ ንጉሥ ጆርጅ አምሥተኛ (የዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ አያት) እና ንግሥታቸው የ ሕንድ ንጉሠ ነገሥት እና እቴጌ የሚል ማእረግ ተጨመረላቸው።

፲፱፻፰ ዓ/ም የቻይና ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት አገሪቱን ወደንጉዛት ሥርዐት መመለሳቸውንና እራሳቸውንም ንጉሠ ነገሥት ማድረጋቸውን አወጁ።

፲፱፻፶፮ ዓ/ም ኬንያብሪታንያ ነጻነቷን በመቀዳጀች በአፍሪቃ ሠላሣ አምሥተኛዋ ነጻ አገር ሆነች።

፲፱፻፶፯ ዓ/ም የኬንያ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ጆሞ ኬንያታ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።

፲፱፻፸፪ ዓ/ም የቀድሞዋ ሮዴዢያ ስሟን ቀይራ ዚምባብዌ ተባለች።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፰፻፲ ዓ/ም በኢትዮጵያዘመነ መሣፍንት ሲጀመር ከዙፋናቸው ወርደው አክሱም በስደት ላይ የነበሩት እና “ተፍጻሜተ ነገሥት” የሚባል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ቀዳማዊ ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ አረፉ።

፲፱፻፮ ዓ/ም መጀመሪያ የሸዋ ንጉሥ በኋላም የዘመናዪቱ ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፤ በአድዋ ጦርነት የኢጣሊያን ሠራዊቶች ድል የመቱት ታላቁ መሪ፤ “ዕምዬ ምኒልክ” ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ባደረባቸው ህመም በዛሬው ዕለት አረፉ።

፲፱፻፲፱ ዓ/ም በዳግማዊ ምኒልክ፣ በልጅ ኢያሱ እና በንግሥት ዘውዲቱ ዘመናት የጦር ምኒስትር የነበሩት ፊታውራሪ ሁብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ የሚወዷቸው ዕምዬ ምኒልክ ባረፉበት ዕለት ሞቱ።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]