ቴዲ አፍሮ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ቴዲ አፍሮ በሜልቦርንአውስትራሊያ (ጁን 2011 እ.ኤ.አ)

ቴዲ አፍሮ (Teddy Afro) ዕውነተኛ ስሙ: ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ከዘመናችን ወጣት ኢትዮጵያውያን ዘፋኞችና አቀንቃኞች ሁሉ እጅግ ተወዳጅ ነው። ቴዲ ለጃማይካዊው ሬጌ ኮከብ ቦብ ማርሊ የዘፈነለት የሬጌ ሙዚቃው በዓለም ዙሪያ እንዲታወቅ ያደረገው ሲሆን በተለይ ለኃይሌ ገብረ ሥላሴ ና ለሌላኛው የኦሊምፒክ ጀግና ቀነኒሳ በቀለኦሊምፒክስ ካሸነፉ በኋላ ያወጣቸው ወቅታዊ አልቡሞቹ ይበልጥ ታዋቂ አርገውታል። ቴዲ አፍሮን በጣም ታዋቂ ያደረግው 'ያስተሰርያል' የተባለው አልበሙ ሲሆን ስለ ፍቅር ፣ መቻቻል ፣ ህዝብ ስሜት እንዲሁም ስለመንግስታት እና ስለ ተቃዋሚዎች በ ፍቅር ለ ሃገር እድገት መስራት ዘፍኖአል። ዘፈኖቹ ብስል እና ጠንካራ ናቸው። ቴዎድሮስ ካሳሁን ሐምሌ 7 1968 በአዲስ አበባ ተወለደ። {{Template loop detected: መለጠፊያ:Infobox musical artist|en}}

ቴዲ አፍሮ በአሁኑ ሰአት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በመኪና አደጋ ሰው ገድሎ በማምለጥ ወንጀል ተከሶ የነበረ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት 6 ዐመት አና 18000 ብር አንዲከፍል ከተወሰነበት በኋላ በእስር ቤት ውስጥ ለ 1 አመት ከ ወራት ያህል ቆይቷል። ከዚያም በተለያዩ ምክንያቶች (ይቅርታን ይጨምራል) ከ እስር እንዲፈታ ተወስኖለታል።

የፍርዱ ሁኔታ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፍርዱ ብዙውን ህዝብ አላሳመነም። ህዝቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቴዲን መፈታት አስመልክቶ ጩሀቱን አሰምቶአል። የፍርድ ሂደቱ ግልጽ አልነበረም ከ ወንጀል ክስነት ይልቅ የፖለቲካ ትርጉም የያዘ ነበር። እና ሌሎችም ተቃውሞዎች በተለያዩ ጊዜያት ከህዝቡ ተሰምተዋል። ሲገጭ አይቻለሁ ብሎ የመሰከረበት ይርዳው ጤናው ነው። እስከማለት ነበር የህዝቡ ተቃውሞ።

ከእስር በኋላ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተዲ አፍሮ ከ እስር ከተፈታ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ትሪቶቹን አቅርቧል። በቀጣይም ሊያቀርባቸው ያሰባቸው ኮንሰርቶች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

አልበሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]