Jump to content

እስስት

ከውክፔዲያ
?እስስት

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: እንስሳ
ክፍለስፍን: አምደስጌ
መደብ: ተሳቢ
ክፍለመደብ: የእባብ ክፍለመደብ
ንኡስ ክፍለመደብ: Iguania
አስተኔ: እስስት Camolinde

እስስትእንሽላሊት አይነት ተሳቢ እንስሳ ናት። አንዳንድ የእስስት አይነቶች የቆዳ ቀለማቸውን በመቀያየር ይታወቃሉ። እስስቶች ቀለማቸውን የሚቀይሩበት ምክንያት ሶስት አይነት ሲሆን አንደኛው በአሉበት ስሜት ምክንያት፣ ሁለተኛው በከባቢ ብርሃን፣ እና ሶስተኛው በሙቀት ምክንያት ናቸው። በተለይ የሚገርም ከከባቢ ቀለማት ጋር በመምሰል ለመደብቅ ያለው ችሎታ ነው፤ ከዚህም የተነሣ «እስስታይ» የተባለው አለባበስ በሥራዊቶች ዛሬ ይጠቀማል።

እስስቶች ረጅም፣ እሚያታብቅ ምላስ አላቸው። እኒህ ምላሶቻቸው ከሰውነታቸው ሁለት እጥፍ መለጠጥ ይችላሉ። አይኖቻቸው ለየብቻቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። እስስቶች ብዙ ጊዜ ሚመገቡት ትንኞችን ሲሆን አልፎ አልፎ ትናንሽ እንሽላሊቶችን ይበላሉ።

እስስቶች በአውሮጳአሜሪካአፍሪካ፣ በተለይም በማዳጋስካር ይገኛሉ።