ካርል ማርክስ

ከውክፔዲያ
ካርል ማርክስ ተወለደ:ግንቦት 5፣ 1818 እ.ኤ.ኣ ትርየር፣ የፕሩሽያ ግዛት፣ ጀርመን ኮንፌደሬሽን ሞተ:መጋቢት 14፣ 1883 (በ64 አመቱ) ሎንደን፣ ኢንግላንድ የኖረባቸው ስፍራዎች:ጀርመን ፈረንሳይ፣ ቤልጅየም፣ ዩናይትድ ኪንግደም ዜግነት:ጀርመን ያጠናቸው መስኮች: ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ሶሽዮሎጅ ተጽእኖ ያሳረፉበት: ፍሬድሪክ ሄግል፣ ጋብሬል ኮቤት ተጽእኖ ያሳረፈባቸው:ሌኒን፣ አንቶንዮ ግራምሴ፣ ሮዛ ለክዘምበርግ፣ ትሮትስኪ፣ ማኦ፣ ቲቶ፣ ሆርክሄይመር፣ አዶርኖ፣ ማርከስ፣ ተጠቃሽ ስራዎቹ:ካፒታል I (፩፰፮፯), II (፩፰፰፭), III (፩፰፱፬)፣ ኮሚኒስት ማኒፌስቶ (፩፰፬፰)

ካርል ሔንሪክ ማርክስ (ግንቦት 5, 1818መጋቢት 14, 1883) ጀርመናዊ ፈላስፋ እና የፖለቲካ ተመራማሪ ነበር። የካርል ማርክስ ፅሑፎች በገንዘብ( ኢኮኖሚ) እና የኅይል ፖለቲካ ላይ ያተኮሩ ነበር። በማርክስ አስተሳስብ ደመወዝ ተከፋይ ጉልበት ባለበት ሁሉ የመደብ ትግል ይኖራል ብሎ ያምን ነበር። በእርሱ እመነት ይህ የመደብ ትግል በሰራተኞች አሸናፊነትና የበላይነት የሚደመደም ነው።

ከካርል ማርክስ መጻሕፍት ውስጥ ኮሚዩኒስት ማኒፌስቶ የተሰኘው መጽሃፉ በጣም ታዋቂው ሲሆን ከፍሬድሪክ ኤንግልስ ጋር አብሮ በ1840ዓ.ም. የደረሰው ነበር። መጽሐፉ የኮሚዩኒዝምን ሃሳቦችና አላማወች ለማስቀመጥ ይጥራል። እኒህ ሃሳቦቹ በአሁኑ ዘመን ማርክሲዝም በመባል ይታወቃሉ።

በሌላ ጎን ካርል ማርክስ ከደረሳቸው መጻሕፍት ዳስ ካፒታል የሚሰኘው እንደ ዋና ስራው ተደርጎ ይወሰዳል። የዚህ መጽሐፉ ሦስት ክፍሎች ብዙ ጊዜውን እንደወሰዱ ይነገራል። ዳስ ካፒታል እንዴት ካፒታሊዝም እንደሚሰራ ሲገልጽ በዚያው ልክ ካፒታሊዝም የሚፈጥራቸውን ችግሮች አብሮ ያብራራል። የማርክስ ርዕዮተ አለም ለሶሻሊዝም መነሳትና ለሩሲያ አብዮት መንስኤ እንደሆነ በብዙዎች የታመነ ነው።

የማርክስ ታዋቂ ርዕዮት አለም ቁስ አካላዊነት ሲሆን፣ ሃይማኖትሥነ ምግባር እና ማህበረሰባዊ መዋቅሮች በሙሉ መሰረታቸው ኢኮኖሚክስ ነው ብሎ ያምን ነበር።

ብዙ ሰዎች እስካሁን ደረስ የማርክስን ሃሳብ ይከተላሉ፣ እንዲሁም በማሳደግ ሲያዳብሩት ይታያሉ።

ርስት ሁሉ የመንግሥት መሆኑ እንጂ የግል ርስት አለመኖሩ የሚገኝበት ሁናቴ የካርል ማርክስ ፍልስፍና ውጤት ነው። በተጨማሪ ማርክስ የሃይማኖት ወዳጅ ባለመሆኑ መጠን፣ በማርክሲስም-ሌኒኒስም በተገዙት አያሌ አገራት በተለይም ስሜን ኮርያቻይና፣ የቀድሞም አልባኒያ ውስጥ የሃይማኖት ወይም የኅሊና ነጻነት አልተገኘም።

«ስግብግብ ያበደ ካፒታሊስት ሲሆን
ካፒታሊስት ደግሞ ጤነኛ ስግብግብ ነው።»

ካርል ማርክስ