Jump to content

የኮሞዲቲ ገበያ

ከውክፔዲያ
(ከኮሞዲቲ ንግድ የተዛወረ)

በገበያ የሚነገዱ ኮሞዲቲዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እንደምን ሰንብታችዋል የተከበራችሁ አንባብያን።
በዚህ ገፅ ላይ ስለ ኮሞዲቲ ገበያ በተመለከተ እንዴት በዓለም የንግድ መለዋወጫ ቦታዎች ላይ፤ በይበልጥም በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ፡ እንዲሁም በእስያ እና በአውስትራልያ ያሉትን ፣ የቅባት እና የጥራጥሬ እህሎች፣የእንሥሳ ፤ የከብትና የዶሮ ስጋዎች፣ የከብት ምግብና የአትክልት ማዳበሪያ ሸቀጦች፣ በኢኮኖሚ የአደጉ አገሮችን የገንዘብ ምንዛሪ አለዋወጥ ዘዴ ፣ የነዳጅ ዘይትንና የድፍድፍ ዘይትን አገዛዝ ስልቶች ለማሳወቅ በአጭሩ ለመተንተን የተዘጋጀ የዊኪ ገጽ ነው።

(ይህ ገጽ በመታደስ እና በመስተካከል ሁኔታ ላይ ነው።)



እነዚህ ከበታች የተዘረዘሩት፤ በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ በየጊዜውና አንዳንዴም በየቀኑ ለመገዛትና ለመሸጥ በብዛት ተፈላጊነት ያላቸው ሲሆኑ ፤ በእንግሊዘኛው አጠራር - አክቲቭ ሙቨርስ ኤንድ ሼከርስ በመባል ታውቀው በተጨማሪም ገበያውን ለሚያውቅና ለማያውቅ ሰው ፤ በዙ ትርፍን እና የብዛት ኪሳራንም የሚሰጡ ናቸው።

የሶፍት ኮሞዲቲ ምድቦች የእርሻ ተክሎች የቅባት እህሎች የከብት ስጋ መደብ የብረት ማዕድኖች የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት የአገሮች ገንዘብ ምንዛሪ
ቡና  ኮፊ
ኮኮዋ ካካዋ
የብርቱካን ጭማቂ
(ፍሮዘን ኦሬንጅ ጁስ)

ስኳር #11
ስኳር #14
በቆሎ - ኮርን 
ስንዴ - ዊት
አጃ - ኦትስ
ሩዝ - ራፍ ራይስ የካንሳስ ቀይ ስንዴ
ሶይ ቢን
ሶይ ቢን ዘይት
ሶይ ቢን ምግብ ለከብቶች
ካኖላ
የቀንድ ከብት
(ላይቭ ካትል)

የሚደልቡ ጥጆች
(ፊደር ካትል)

አሳማ- ፖርክ
የአሳማ ስጋ
ፖርክ ቤሊ
(ለቤከን የሚሆን የአሳማ ስጋ)
ወርቅ-ጎልድ
ብር-ሲልቨር
ፕላቲንየም
አሉሚንየም
መዳብ -ኮፐር
ፓላዲየም
ክሩድ ዘይት

ሂቲንግ ዘይት
ኤን ዋይ ኤች አር ቦብ
ናችዩራል ጋዝ
የአሜሪካን ዶላር
የእንግሊዝ ፓውንድ
የአውሮፓውያን ኢዩሮ
የጃፓን የን

የስዊዘርላንድ ፍራንክ
የካናዳ ዶላር
የአውስትራልያን ዶላር
የኒው ዚላንድ ዶላር
የሜክሲኮ ፔሶ

የአሜሪካን ዶላር ኢንዴክስ
(የዶላር ገበያ መመዘኛ ኮታ)



የኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ መሸጫና መግዣ መተመኛዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

(ይህ ገጽ በመታደስ እና በመስተካከል ሁኔታ ላይ ነው።)

በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ ሻጭም ሆነ ገዢ የሚዋዋልበትና የመነጋገጃው ዘዴ ከሌላው ገበያ አይነት ለየት የሚያደርገው ውሉ በኮንትራት ነው። ይህም ማለት መጀመሪያ ለመገበያየት በኮምፒውተር ላይ ፤ አካውንት መክፈት ያስፈልጋል። በአካውንት መክፈቻ ጊዜ የኢንቬስትመንት ባንኩ የሚጠይቀው የመነሻ መጠን አለ። ብዙ ጊዜ ከአምስት ሺህ ዶላር በላይ ነው። ይህ መጠን ለአንድ ኮንትራት በቂ ነው። ለምሳሌ አንድ ኮንትራክት እንደየ ኮሞዲቲው አይነት እስከ ሦስት ሺህ እና ከዚያም በላይ ይደርሳል። በአንድ ቀን ጥዋት ውስጥ ሁሉም ለማጣት ወይንም ሁለት እጥፍ አድርጎ ለማርፈድ ይቻላል። ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ የኢንቬስትመንቱ ባንክ ደላላ በቅድሚያ ስለገበያው ሁኔታ ማወቃችሁን ማረጋገጥ የሚፈልገው። ዋናው መሠረቱ ከሚገዛው የኮሞዲቲ ኮንትራት እኩል ስለ ገበያው አካሄድ ሁኔታ ማወቅ ያስፈልጋል። በኮሞዲቲው ዋጋ ላይ የትንሽ ሳንቲሞች ልዩነት በኮንትራቱ ይዘት ላይ ቶሎ ለውጥን ያሳያል። ከመቶዎች ዶላር እስከ ሺህ በላይ በአንድ ኮንትራክት ውስጥ።

አብዛኛው ኮሞዲቲ የሚገዛና የሚሸጥ ሰው ፤ ትርፉንም ሆነ ኪሳራውን በቶሎ አውቆ ወይ መሸጥ ወይም መቆየት ይችላል። መጀመሪያ አካውንቱ ውስጥ ካለው ገንዘብ ላይ ኮሞዲቲውን በኮንትራት ይገዛል። ኮንትራቱም የሚለው የዚህ አይነት ኮሞዲቲ ኮንትራክት በዚህ ወር ላይ የሚያልቀውን በዝህ ያክል ዋጋ ገዝቷል ፤ ወይም የዚህ አይነት ኮሞዲቲ በዚህ ወር ላይ ኮንትራቱ የሚያልቀውን በዚህ ያክል ዋጋ ይሸጣል ነው የሚለው። እና ገዢው ወይም ሻጩ ሰው የኮንትራቱ ጊዜ ሳያልቅ በፊት ትርፉን ወይም ኪሳራውን ተገንዝቦ ከኮንትራቱ መውጣት ይገባዋል። ካለበለዚያ ኮንትራቱ ካለቀ በኋላ እዳ ውስጥ ገብቶም ቢሆን መግዛትና ወዳ ቤቱ ለማስጫን በኮንትራቱ ይገደዳል። ነገር ግን በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ ፤ አብዛኛው የገበያ ተዋናኝ ፤ ማለትም ከዘጠና በመቶው በላይ ፤ የኮንትራቱ ቀን እስከሚደርስ ሳይጠብቅ ኪሳራውን አምኖ ወይንም እጥፍ ትርፉን ወስዶ ከኮንትራክቱ ውስጥ ይወጣል። ከዚያም ወደ ሌላ ኮሞዲቲ በመሄድ ግዥ እና ሽያጩን ያካሄዳል። (በዚህ አርስት ላይ በተለያይ ጊዜ ጨማምሬ ለመፃፍ እሞክራለሁ። በቶሎ ይሚገባ ሊሆን አይችልም ፤ ቢሆንም ብዙ የማወቅ ልምምድ ያስፈልገዋል ካለበለዚያ ውጤቱ በጣም አክሳሪ ነው የሚሆነው።)

የእህልና የዘር ተክሎች
የቅባት እህሎች
የሶፍት ኮሞዲቲ
የከብት ስጋ
የብረት ማዕድኖች
የብረት ማዕድኖች የብረት ማዕድናት በሁለት ይከፈላሉ። እነሱም ፕሪሽየስ ሜታል መደብ እና ቤዝ ሜታል መደብ ናቸው።
የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት
ክሩድ ዘይት ክሩድ ዘይት በሁለት ዓይነት ልዩነት መደብ የተደረገበት ዋንኛው ምክንያት ክሩድ ዘይቱ በውፍረትና በሠልፈር ፐርሰንት መጠን የተለየ ስለሆነ ነው።
የአገሮች ገንዘብ ምንዛሪ
ንግድና ኢኮኖሚ
የአሜሪካን ዶላር ኢንዴክስ ሌሎች የትላልቅ ካምፓኒ ኢንዴክሶች መመልከት የገበያን ሁኔታ በቅድሚያ ለመገንዘብ ይረዳል።