Jump to content

የኮርያ ጦርነት

ከውክፔዲያ
(ከኮርያ ጦርነት የተዛወረ)
የኮርያ ጦርነት
ቀዝቃዛው ጦርነት ክፍል
ቀን ከሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. እስከ ዛሬ
የተኩስ ማቆም የተፈረመው ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፵፭ ዓ.ም.
ቦታ የኮሪያ ልሳነ ምድር
ውጤት
  • የተኩስ ማቆም ስምምነት ተፈረመ
  • የደቡብ ኮሪያ ወረራ በሰሜን ኮሪያ መክሸፍ
  • የሰሜን ኮሪያ ወረራ በተባበሩት መንግሥታት መክሸፍ
  • የደቡብ ኮሪያ ወረራ በቻይና መክሸፍ
  • የኮሪያ ጦር የለሽ ክልል መቋቋም፣ ሁለቱም ወገኖች 38ኛው ፓራለል አካባቢ ትንሽ መሬት አገኙ
ወገኖች
 የተባበሩት መንግሥታት (ውሳኔ ፹፬)

 ደቡብ ኮሪያ
 አሜሪካ
 የብሪታንያ መንግሥት
 አውስትራሊያ
 ቤልጅግ
 ካናዳ
 ኮሎምቢያ
 ኢትዮጵያ
ፈረንሣይ ፈረንሳይ
 ግሪክ
 ሉክሰምበርግ
 ኔዘርላንድስ
 ኒው ዚላንድ
 ፊሊፒንስ
 ደቡብ አፍሪካ
 ታይላንድ
 ቱርክ
የሕክምና ዕርዳታ፦
 ኖርዌይ
 ስዊድን
 ዴንማርክ
 ኢጣልያ
 ህንድ

ሰሜን ኮሪያና አጋሮች፦

 የኮሪያ ዴሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ
 ቻይና
 ሶቪዬት ሕብረት
የሕክምና ዕርዳታ፦
 ቼኮስሎቫኪያ
ፖላንድ ፖላንድ
ሀንጋሪ ሁንጋሪ
ቡልጋሪያ ቡልጋሪያ
ሮማንያ ሮማንያ

የደረሰው ጉዳት
የሞቱ፦

የቆሰሉ፦

የጠፉ፦

ጠቅላላ፦
የሞቱ፦

የቆሰሉ፦

የጠፉ፦

ጠቅላላ፦


አሜሪካ ሠራዊት በኢንቾን መከላከያ ግድግዳ ሲወጡ

የኮርያ ጦርነትኮርያሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር።

የኮሪያ ዘማቾች ትውስታ

ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም”   “አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም”

በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት  350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡

ለኮሪያ ዘመቻ እንዴት ነው የተመረጡት?

በመሠረቱ የገበሬ ልጅ ነኝ፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ ተብዬ አይደለም ወደ ወታደራዊ ዘመቻ የገባሁት፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት በሕፃንነቴ ከአባቴ ጋር ጫካ ለጫካ ተንከራትቻለሁ፡፡ በ1939 ዓ.ም ወታደርነት ተቀጠርኩ፡፡ የተወለድኩት በ1922 ዓ.ም ነው፡፡ ወታደር በሆንኩ በአምስት ወይ በስድስት ዓመት ኮርያ ዘመትኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር ስዘምት ማንበብና መፃፍ አልችልም ነበር፡፡

አሁንም ድረስ?

አይደለም፡፡ እዚያው ኮርያ እያለሁ ዘመድ ደብዳቤ ፃፈልኝ፡፡ ሃምሳ አለቃ ንጉሤ ወልደሚካኤል የሚባል ጓደኛዬን ፃፍልኝ ስለው ሂድ አልጽፍም አለኝ፡፡ ንዴት ያዘኝና ወንጌሌ ቆስጣ ለሚባሉ አለቃዬ ጋዜጣ ስጡኝና ፊደል ልማርበት አልኳቸው፡፡ ፊደል ጭምር ሰጡኝ፡፡ በዚያው በጓደኞቼ አጋዥነት ተለማምጄ ስሜን መፃፍ ቻልኩ፡፡ በሦስት ወር ደብዳቤ ለቤተሰብ ጽፌ ደብዳቤዬ እንደደረሳቸው ቤተሰቦቼ ሌላ ደብዳቤ ላኩልኝ፡፡ ጥሩ አለቆች ስለነበሩኝም እዚህ ስመለስ ጫካ ወስደው ጥቁር ሰሌዳ በማሸከም ያስተምሩን ነበር፡፡ የማታ ትምህርትም ገብቼ ነበር፡፡ ዘመቻውን ከሦስተኛው ቃኘው ጋር በኮሎኔል ወልደዮሐንስ ሽታ አዝማችነት ነበር የዘመትኩት፡፡

እዚያ ሲደርሱ ከነበረው ምን ያስታውሳሉ?

የመጀመሪያውን ቅኝት ስንወጣ በእኔ መቶ አዛዥነት ነበር፡፡ የመጀመርያው ተኩስ ሞትና መቁሰልም የደረሰው በእኛ ላይ ነው፡፡ የዘመትነው በግንቦት ወር 1945 ዓ.ም ነበር፡፡ የመጀመሪያው ቃኘው የዘመተው በ1943 ዓ.ም ነበር፡፡ አንድ ሞቶብን ሁለት ቆሰሉ፡፡ አንደኛው ቁስለኛ እጁ ተቆረጠ፡፡ የሞተውንና ቁስለኞቹን ይዘን ወደ ወገን ጦር ተቀላቀልን፡፡

ሁለተኛው የጦር ግንባር ከፍተኛው የቲቮ ተራራ ነው፡፡ እዚያ ላይ በመከላከል ላይ ነበርን፡፡ ጓደኛዬ እዚህ ውስጥ አለ (በጦርነቱ የተሰውትን ሃውልት እያሳዩ) በዳኔ ነገዎ ይባላል፡፡ መከላከያ ውስጥ አንድ ላይ ነበርን፡፡ ባንከር አለ፡፡ ድንገት ቢተኮስ እዚያ እንግባ ስለው እምቢ አለ፡፡ እየጐተትኩት እያለሁ ጥይት ተተኮሰ፡፡ እሱን በጣጥሶ ሲጥል እኔን አፈር ከአንገት በታች ቀበረኝ፡፡ ጥይቱ እያበራ ሲመጣ እኔ ዘልዬ ስወድቅ እሱን በጣጠሰው፡፡ ከ45 ደቂቃ ቁፋሮ በኋላ ነው ያወጡኝ፡፡ ከዚያ የጓደኛዬን ሰውነት በዳበሳ ፈልገን በራሱ ሸራ አድርገን ለመቃብር አበቃነው፡፡ ጦርነቱ ባይቆም ያ ሁሉ ሠራዊት ያልቅ ነበር፡፡

ግን አንድም አልተማረከም?

አንድም አልተማረከም፡፡ ዘማቹ ይፋቀራል፡፡ ይከባበራል፡፡ ጓደኛህ ቢሞት እንኳ ሬሳውን ጥለህ አትሄድም፡፡ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም፡፡ አመት ከሰባት ወር እዚያ ቆይቻለሁ፡፡ ጦርነቱም የቆመው እዚያ እያለን ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በየቀጠናው ጥበቃ እናደርግ ነበር፡፡

አሁን በእርቁ ለሰሜን ኮርያ ተሰጠ እንጂ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሰሜን ዘልቀናል፡፡ ብዙ ምሽግ መቆፈራችን ነው አንድም እዚያ ብዙ ያቆየን፡፡ ሀገሩም የራሱን ጦር እስኪያደራጅ መቆየቱ የግድ ነበር፡፡ ነሐሴ 29/1946 ዓ.ም ተመልሰን አዲስ አበባ ገባን፡፡ ሌሎቹ የተማረኩት ምን አልባት በምቾት ብቻ መኖር ስለለመዱ ይመስለኛል፡፡ እኔ ከወገኔ ተለይቼ እጄን የምሰጥበት ምክንያት የለም፡፡ ሄጄ ማን እጅ ነው የምገባው? ጠላት እጅ፡፡ ስም ያለው ሞት መሞት እንጂ ሁለት ሞት አልሞትም፡፡

የመጀመሪያው ቃኘው ሻለቃ ሲሄድ እርስዎ የት ነበሩ?

ሠራዊት ውስጥ ነበርኩ፤ ሐረር የልዑል መኮንን ቤተመንግስት ጥበቃ ላይ ነበርን፡፡ በ1944 ወደ አዲስ አበባ ተዛውረን መጣን፡፡ ከዚያ ተመልምዬ ነው ወደ ኮርያ ለመሄድ የበቃሁት፡፡ እንዴት እንደተመለመልን አላውቅም፡፡ ይኼን የሚያውቁት መልማዮቹ ናቸው፡፡ የታዘዘውን ፈፃሚ ጠንካራ ሞራል ያለው ሠራዊት ተመርጧል፡፡

ከማን ጋር የምትዋጉት? የውጊያ ብቃታቸውስ ምን ይመስላል?

እነዚያ ሰሜን ኮርያ፣ ሶቭየት ሕብረት፣ ቻይናና ተባባሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ብርቱ ስልት አላቸው፡፡ በጨበጣ ውጊያ የወደቀልህ መስሎ መትቶ ይጥልሃል፡፡ የእኛዎቹ በተለይ አሜሪካኖች እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ታንክ፣ መድፍ… ታንክ ላይ የሚጠመደው ጀነራል መድፋቸውማ የተለየ ነው፡፡ ይኼ መድፍ በጣም በርቀት መምታት የሚችል ነው፡፡ እዚህ ሲተኮስ እዚያ ፈንድቶ ርቀቱን ይጨምራል፡፡ አውሮፕላኖችም አሉት - የኛ ወገን፡፡ አንድ ጦር ከተከበበ በአየር ይመታል አካባቢው፡፡ በዚህ መልኩ 70ሺህ ያህል የተቀናቃኝ ጦር ተደምስሷል፡፡ ከእኛ ግን 18 ብቻ ነው የሞተው፤ ተከቦ ከነበረው፡፡

የቋንቋና የባህል ችግር አልገጠማችሁም?

እኛ ከማንም ጋር ግንኙነት የለንም፡፡ ግንኙነት ያለው ከዋናው መምሪያ ነው፡፡ አገናኝ መኮንኖች እዚያ የተባለውን ይነግሩናል እንጂ ከሕዝብ ጋር በፍፁም አንገናኝም፡፡ ስንገናኝም በጥቅሻ ነው፡፡ ያለነው እልም ያለ ገጠር ውስጥ በመሆኑ ከተማ ወጥቶ በእረፍት ጊዜ መዝናናት የሚባል ነገር የለም፡፡ ብንታመም ሻምበላችን ውስጥ ሕክምና አለ፡፡ አንድ ጊዜ ታምሜ ነበር፡፡ እዚያ ታክሜ ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ሌላ ሀኪም ቤት ተላኩ፤ ወዲያውኑ በሄሊኮፕተር ፑዛን ከተማ ሄድኩ፡፡ ለ20 ቀን ያህል ታክሜ ተመልሻለሁ፡፡ ሕክምናቸው በጣም ጥሩ ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከዚያ ሀገር ሴት ጋር በፍቅር መውደቅ ጋብቻ እና የመሳሰሉት አይኖሩም?

ጋብቻ ሳይሆን ከጋብቻ ውጪ ከዚያ ሀገር ሴቶች ልጅ የወለዱ ወታደሮቻችን አሉ፤ ከኮሪያ ሳይሆን ከጃፓን ፍቃድ ስንወጣ ጃፓን ነበር የምንሄደው፡፡ ፍቅር ይዟቸው ሲለያዩ የተላቀሱም አሉ፡፡

እርስዎስ?

እንዲህ አይነት ጣጣ ውስጥ አልገባሁም፡፡ ጃፓን ፍቃድ ሄጃለሁ፡፡ ግን ልጅነትም አለ፡፡ ሀኪም ቤት ውስጥ በተኛሁ ጊዜ ግን አንድ ችግር ገጥሞኛል፡፡

ምን አይነት ችግር?

አንዲት ነጭ አሜከካዊት ሻምበል የሕክምና ባለሙያ ነበረች፡፡ ፑዛን ጋውን ለብሳ መጣች፡፡ አልኮል የፈሰሰበት ሙቅ ውሃ እና ፎጣ ይዛ ገላህን ልጠበው ልሸው አለችኝ፡፡ በፍፁም እንዴት ተደርጐ አልኳት፡፡ በኋላ አሁን ስሙን የረሳሁት አስተርጓሚ ጠራች፡፡ ለምን እምቢ ትላለህ ገላህን ልጠብህ እኮ ነው ያለችህ አለኝ፡፡

ከዚህ ስሄድ እንኳን ላገባ ሴት አላውቅም፡፡ ራሴ መታጠብ ስችል ሴት እንዴት ያጥበኛል አልኩ፡፡ ሳቀብኝና ነግሯት ለኔ ችግር የለውም አለኝ፡፡ በኋላ ስታጥበኝ የሷንም ፍላጐት በማየቴ ሰውነቴ ጋለ፤ ፍላጐቴ ተነሳሳ፡፡ ይኼኔ “ኧረ ባክህ” ብዬ ስነግረው ሳቀና ነገራት፡፡ ችግር የለውም ብላ አንድም የሰውነቴ ክፍል ሳይቀር አገላብጣ አጠበችኝ፡፡ ትንሽ ቆይታ ልብሷን ለውጣ ለእኔም ልብስ ይዛ መጣች፡፡ ይዛኝ ሄደች፡፡ የዚያኑ እለት ግንኙነት አደረግን፡፡

የመጀመሪያዬ እሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደሆነ ጠላኋት፡፡ ተመልሼ ሀኪም ቤት ተኛሁ፡፡ ሳያት ሁሉ እሸፋፈን ነበር፤ ከጥላቻዬ የተነሳ፡፡ ሳልቆይ ለአለቃዬ ለአስተርጓሚው ነገርኩት፡፡ ድኛለሁ ይላል ይውጣ ተባለ፡፡ እሷ አይወጣም ብላ እንደገና ስምንት ቀን አቆየችኝ፡፡ ከአንዴ በላይ አብረን አልወጣንም፤ እምቢ አልኩ፡፡ በዚሁ መንስኤ ለ15 ቀን ታምሜአለሁ፡፡

ሕክምና ሳይጨርሱ ነው ከሻምበሏ ጋር የወጣችሁት?

ሕክምናማ ጨርሼ እኮ ነው መታጠቡ የመጣው፡፡

ጥሬ ስጋ ስትበሉ የውጭ ዜጐች አይተው ይሸሹዋችሁ ነበር የሚባለው እውነት ነው?

ይኼንን እኔም እንዳንተው ነው የሰማሁት፡፡ ይህንን አደረገ የተባለው ሻለቃ ተፈራ ወልደትንሣኤ ነው ይባላል፡፡ ከመጀመሪያ ዙር ዘማቾች፡፡ እንደዘመተ መንጉሱ በማቀዝቀዣ ታሽጐ ቁርጥ ሥጋ ይላካል - ለጦሩ ንጉሱ የላኩላችሁን ተመገቡ ተብሎ ምግብ ቤት (ሚንስ ቤት) ይመገባሉ፡፡ የጦሩ አባላት ተመግበው የተረፈውን የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ የምንሰጥበት እቃ አለ፡፡ ያን ሥጋ በላስቲክ ጠቅልሎ ይዟል መሠለኝ፡፡ በልቶ ሲጠግብ ጦርነት ይታዘዛል፡፡

ከውጊያ በኋላ ድል አድርገው ሲጨረሱ በድካምና በረሃብ ቁጭ ይላሉ፡፡ በያዘው ሴንጢ እየቆረጠ ያንን ሥጋ ይበላል፡፡ ይህንን አንዲት ቻይናዊት ፈርታ ተደብቃ አይታዋለች፡፡ ደንግጣ ሰው የሚበሉ እንግዳ ሰዎች መጡ ብላ አስወራች፡፡ ከዚያን ወዲህ ነው እንዲህ መወራት የጀመረው፡፡ ሰው በላ መጣ አሉን፡፡

እርስዎ በስንት የጦር ግንባሮት ተሳትፈዋል?

ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ዮክ ተራራ የጦር ግንባር ነው፡፡ ሁለተኛው ችቦ ነው፡፡ ከነዚህ ውጪ የለም፡፡

በጣም የሚያስታውሱት የኢትዮጵያም ሆነ የሌላ ሀገር ወታደር?

አንድ ግዳጅ ላይ አንድ የመቶ አዛዥ ማንደፍሮ የማነህ ይባላሉ፡፡ ቅኝት ይወጣሉ፡፡ የኛ ሰራዊት ቅኝት ከመውጣቱ በፊት አሜሪካ የማረከቻቸውን የቻይና ወታደሮች አሰልጥና በስለላ ታሰማራ ነበር፡፡ ለእነሱና ለእኛ የተሰጠው ቦታ የተለያየ ነው፡፡ ለመቶ አለቃው ተነግሯል፡፡ ቻይናዎቹ የኛን ይዞታ ይዘው ይጠብቋቸዋል፡፡

የኛዎቹ ሊይዙ ሲሉ ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ የሞቱት ሞቱ፡፡ ቁስለኞችን ውሰዱ ተባልን፡፡ በዚያን ጊዜ እኔ ተመለመልኩና ሂድ ቁስለኛ አምጣ ተብዬ ተላኩኝ፡፡ በሸክም ነው የምናመጣው፤ ያውም ተራራ እና ጨለማ ነው፡፡ ተሸክሜ ሳንጃ ሰክቻለሁ፣ ጠመንጃዬ እንደጎረሰ ነው፡፡ ተሸክሜ ዳገት እየወጣሁ ትንሽ ሲቀረን አንሸራቶኝ ስወድቅ ሰውየውም ወደቀ፡፡ እኔን አጥፍቶ ሊያመልጥ ሲያስብ ቻይናዊው ቀና ብሎ ይቃኛል፣ ቶሎ ብዬ ርምጃ ወሰድኩ፡፡

አሁን ኑሮ እንዴት ነዉ?

የቀበሌ ቤት ተከራይቼ ነው የምኖረው፡፡ እዚህ የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበር በጥበቃ ሰራተኝነት አገለግላለሁ፡፡ ፍላጎት ያለው ያገልግል ሲባል ተቀጠርኩ፡፡ ከምኖርባት ሽሮሜዳ አፍንጮ በር በእግር መንቀሳቀሱን ወድጄዋለሁ፡፡ ደመወዙ ግን  አይወራም አይጠቅምም፡፡

ዘጠኝ ልጆች አሉኝ፡፡ ሦስቱ አግብተዋል፡፡ ሌሎቹ ገና ናቸው፡፡ አንደኛው ልዴ መለሰ ዘነበወርቅ ይባላል ደቡብ ኮርያ ለትምህርት ቢሄድም ከእኔ ጋር እንዳለ ነው የሚቆጠረው፡፡ 249 ብር ነበር የሚከፈለኝ በብዙ ጭቅጭቅ ለቀን እንሄዳለን ስንል ነው መሠለኝ 294 ብር ሆኗል፡፡ የጡረታ አበሉ 310 ብር ነው፡፡ በፊት ደመወዛችን 15 ብር ነበር፡፡ ያውም አምስቱ ብር ተያዥ ነው፡፡ 10 ብር እንቀበላለን፡፡ ሦስት ኪሎ ስንዴም ይሰፈርልናል፡፡ ቤተሰብና ትዳር ስለሌለን ብር ከሃምሳ ሸጠናት ከሰልና ሳሙና እንገዛበት ነበር፡፡

ትዳርስ እንዴት መሠረቱ?

በ1957 ዓ.ም በ32 ዓመቴ ነው ያገባሁት፡፡ እናት አባቴ ናቸው የዳሩኝ፡፡ ከሰራዊቱ ወጥቼ በሲቪል ስራ ላይ ነበርኩ - አየር መንገድ ውስጥ፡፡ አባቴን ከሀገር መውጣቴ ካልቀረ አልመለሥም ዳረኝ ስለው እሺ አለ፡፡ አግኝቼልሃለሁና ናና እያት አለኝ፤ ሰሜን ሸዋ ደብረሊባኖስ አካባቢ ነው የቤተሰቦቼ ቤት፤ ሄድኩ፡፡

አይንህ አይኔ፣ አንደበትህ አንደበቴ ነው፤ ማየቴ ምን ጥቅምና ትርፍ አለው፤ አንተ ባየኻት እስማማለሁ አልኩት፡፡ ያየሁአት የሰርጉ እለት ነው፡፡ የሰርጉ እለት ስገባ ሴቶቹ በሀገራችን ባህል መሠረት ተሸፋፍነዋል፡፡ እናት አባቷንም አላውቅም፡፡ ወላጅ አባቷ ማነው አልኩ? እኔ ነኝ አሉ፡፡

እርስዎ ነዎት?  ስል አዎ አሉ፡፡ ያውቁኛል ስል ኧረ ልጄ አላውቅህም አሉኝ፡፡ ዘነበወርቅ በላይነህ እባላለሁ አልኳቸው፡፡ አንተ ነህ ሲሉኝ አዎ … ልጅም ፈቅደውልኛል ሲላቸው አዎ አሉኝ፡፡ በሉ ስለማላውቃት ይስጡኝ አልኳቸው፡፡

ገልጠው ይቺ ነች ልጄ አሉ፡፡ ተሞሽራ ከተቀመጠችበት፡፡ ወ/ሮ አሥራት አለሙ፣ የልጆቼን እናት፣ ባለቤቴን እንደዚህ ነው ያገባኋት፡፡ አገር ቤት ተጋባንና አዲስ አበባ ሽሮሜዳ መኖር ጀመርን፡፡

ማህበራችሁ እንዴት ተመሠረተ?

ማህበሩ የተመሠረተው በ1994 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚያ በፊት በነበሩት መንግስታት ድጋፍ ማጣት ማህበሩ አልተቋቋመም ነበር፡፡ በሁለት ትልልቅ ምክንያቶች ነው የተቋቋመው፡፡ አንደኛው:- ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመኑ ከሰለጠኑት መንግስታት አንፃር ምን ቦታ እንደነበራት ለማሳየት ነው፡፡

ሌላው ሀገራችን የሰጠችንን መወጣታችንንና ታሪክ መስራታችንን ለትውልድ ለማስተላለፍ ነው፡፡

ኮርያ ለመዝመት እንዴት ተመረጡ፣ እድሜዎ ስንት ነው?

እንዴት እንደተመረጥን አናውቀውም፡፡ መኮንኖች ስለሆንን ማን ይሂድ ማን ይቅር የሚለውን የሚያውቁት አለቆቻችን ናቸው፡፡ ሚሊተሪ አካዳሚ ስንገባ ወታደር እንደምንሆን እናውቃለን፡፡ አካዳሚው የንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘበኛ ጦር አካዳሚ ነው፡፡ ቪላ ሳህለሥላሴ ይባላል የሠለጠንበት ቦታ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ ሦስተኛ ኮርሰኞች ነን፡፡ ትምህርታችንን ከሌሎቹ በሰባት ወር ቀድመን ነው የፈፀምነው፡፡ በዚያን ጊዜ የነበረው ከፍተኛ ክፍል ስምንተኛ ስለነበር ከስምንተኛ ክፍል ነው የገባሁት፡፡ የጦር አካዳሚውን ትምህርት እንደጨረስን የኮርያ ዘመቻ ወሬ ተሰማ፡፡ እኛ ሚያዝያ 3 ተመርቀን በማግስቱ ሚያዝያ 4 ጓደኞቻችን ዘመቱ፤ በመጀመሪያ ቃኘው፡፡ እኔ በሁለተኛው ቃኘው የሄድኩት በ1944 ዓ.ም ነው፡፡

ስትሄዱ እንዴት ነበረ ጉዞው?

ወደ ለገሃር ማክ በሚባል ወታደራዊ መኪና ሄድን - ከጃንሜዳ፡፡ ከዚያ በባቡር ወደ ጅቡቲ፤ ከዚያም በመርከብ ደቡብ ኮርያ፡፡  ደቡባዊ የወደብ ከተማ የሆነችው ፑዛን ከሃያ ሁለት ቀን የባህር ላይ ጉዞ በኋላ ገባን፡፡ ከዚያም እንደገና በመኪና ተሳፍረን እዚያው አካባቢ ከአየር ፀባዩ እና ከጦር መሣሪያው ጋር ተለማመድን፡፡ በሌላ ባቡር ሁለት ቀን ተጉዘን ገባን፡፡ እንደገና በአሜሪካ መኪና ተጭነን ግንባር ደረስን፡፡ ያኔ ኮርያ ስደርስ የ21 ዓመት ከሰባት ወር ልጅ ነበርኩ፡፡

ሚስት ሳያገቡ ነበር የሄዱት?

ኡ…እንኳን ላገባ የሴት ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ እንደዛሬው ልጆች አልነበርንም፡፡

እዚያስ አንዷን ደቡብ ኮርያዊት የመተዋወቅ ነገር?

የሄድነው ለጦርነት ነው እንጂ ለሽርሽር አይደለም፡፡ ከነሱ ጋር የምንገናኘው በሦስት ወር አንድ ጊዜ ከጦር ግንባር እረፍት ለማድረግ ስንመለስ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አቅራቢያችን ወዳሉ ከተሞች እንሄዳለን፤ ጃፓንም ድረስ፡፡ በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ተጠቃቅሶ መግባባትና መጫወት አይቀርም፡፡ ጦርነት ውስጥ ሆነህ እጮኛ ለመያዝ ሚስት ለማግባት መመኘቱ ጥሩ ነው፡፡ እድሉ ግን ይገኛል ወይ ነው ጥያቄው፡፡ መቀባበጡ ግን እድሜአችን ስለነበር አልቀረም፡፡

እንዴት ትግባቡ ነበር?

በጫወታ ለመግባባት እኮ ምልክት ይበቃል፡፡ ለእረፍት ስንመለስ ጦር ሜዳ መኖራችንንም እንረሳዋለን፡፡ ምክንያቱም ዘመናዊ አቅርቦት ነበር፡፡ ከመከላከያ መስመር እንኳ ከቻልክ በየአምስቱ ቀን ሻወር አለ፡፡ እዚያ እየታጠብክ የለበስከውን ጥለህ አዲስ ልብስ ትለብሳለህ፡፡

ተግባብቶ ትዳር የያዘ ወይ ፍቅረኛ የነበረውና የወለደ አልነበረም?

ይኖራል፡፡ ከኛ በላይ ያሉት ይኖራሉ፡፡ እኛ የመቶ አዛዦች ነን፡፡ ከፍተኛ መኮንኖችና አዛዦቻችን ማለት ነው፡፡ ጠና ያሉ ናቸው፡፡ አራት አምስት ልጅ ከወለዱ በኋላ የዘመቱ ይገኙባቸዋል፡፡ ያላየሁትን አልመሠክርም ሲያደርጉ አላየሁም፡፡ እኛ ብንቀብጥ ብንቀብጥ ከጓደኞቼ ጋር ነው፡፡ ከአዛዦቼ ጋር ሆኜ ደግሞ መቅበጥም አልችልም፡፡

የባህልና የቋንቋ ግጭትስ?

ትክክለኛውን ለመናገር ከነሱ ጋር የባህል ልውውጥ የለንም፡፡ ምክንያቱም በሄድንበት ቦታ ሁሉ የሚቀርብልን ምግብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንድ አይነት ምግብ ነው፤ የጦር ግንባር መዘርዘረ ምግብ፡፡ ወደ ሕዝብ የሚያቀርብ የለንም፡፡ በጦሩ ወረዳም ሕዝቡ የለም፡፡

ጥሬ ሥጋ በመብላታችሁ “ሰው በሎች” ብለው ሲሸሿችሁ ነበር የሚባለውስ?

ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በነበርኩበት ጊዜ ይኼ አልተፈፀመም፡፡ ወሬውን ሰምቼዋለሁ፡፡ በዐይኔ ያየሁት ነገር የለም፡፡ በዘመትኩበት ጊዜ እንዲህ አልተደረገም፡፡ ኮርያዎች ከዚያ በፊት ጥሬ ሥጋ አልበሉ ይሆናል፡፡ ተቀቅሎ የሚበላ ጥሬ ሥጋ ግን ይቀርብልሃል፡፡ ሃበሾች ያ ደስ ብሏቸው በልተው ሊሆን ይችላል፡፡

ለምንድነው አንድም ሰው ያልተማረከው?

አለመማረክ የጀግንነትና የጉብዝና ጉዳይ አይደለም፡፡ አለመማረክ የአመራር ውጤት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የት እንዳለ የት እንደወደቀ ዝርዝር ቁጥጥር በምታደርግበት ጊዜ የቆሰለውን፣ የወደቀውን ሰው ታውቃለህ፡፡

አንድ ሰው ከጓደኞቹ መሃል ሲጠፋ የት እንደወደቀ ትፈልጋለህ፡፡ ይኼ ለእኛ መሠረታዊ ትምህርታችን ነው፡፡ አጥቅተህም ቦታ ከያዝክ በኋላ ሰዎችህን ትቆጣጠራለህ፡፡ እዚያ ስታጣው የት እንደደረሰ ትፈልገዋለህ፡፡ አንድም ቀን አልሸሸንም፡፡ ምናልባት ሽሽት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰዎችን ለመቆጣጠር ሲያቅትህ ነፍስህን ብቻ ለማውጣት ስትሸሽ ያን ጊዜ ሰዎችህ ሊማረኩ ይችላሉ፡፡

በስንት ውጊያዎች ተሳትፈዋል?

ሻለቃው በተዋጋባቸው ውጊያዎች ሁሉ ተሳትፌአለሁ፡፡ አምስት ዋና ዋና ውጊያዎች ነበሩ፡፡ ከዚያ በተረፈ የሽምቅ፣ የደፈጣ ውጊያዎች አሉ፡፡ በነዚህ ሁሉ ተካፍያለሁ፡፡ ስለዚህ መቁጠር ያስቸግራል፡፡

ውጊያ ላይም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ትዝ የሚልዎት ሰው ካለ?

የሰማሁትን ሳይሆን ያየሁትን ልንገርህ፡፡ በነበርኩበት ግንባር እንደ ጥላዬ ወንድም አገኘሁ ያሉትን አስታውሳለሁ፡፡ እንደ ሞገሥ አልዩ ያሉትንም አስታውሳለሁ፡፡ በጦር ሜዳ ውስጥ ገብተው ሙያ እየሰሩ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ጓደኛዬ በቀለ ገብረ ኪዳን ደግሞ አብረን ቅኝት ወጣን፡፡ ሁላችም በያለንበት ተከበብን፡፡ በኋላ እንደምንም አድርገን ከዚያ ሰብረን ወጣን፡፡ ጠላት በሚሸሽበት ጊዜ እሱ ከጎኔ ወድቋል፡፡ እሱን አንስቼ አንድ ቦታ ላይ አስቀምጬ ረርዳታ ጠየኩ፡፡ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ መማረክ የሚመጣው እንዲህ አይነቱ ቦታ ላይ ነበር፡፡ ያን ጊዜ እንኳን አልተማረክንም፤ ሦስት አራት ቦታ ላይ ተከበን በነበርንበት ጊዜ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ጓደኛዬ ከፊቴ ቀድሞ ይኼዳል፡፡ ቁርስ ሰዓት ላይ ነው እኔ ከኋላ ነኝ፡፡ ቁርሳችንን በልተን ስንመጣ ከኋላ ተተኮሰብን፡፡ ጥይቱ ልክ እሱ ላይ ያርፋል፡፡ ሲፈነዳ በጭሱ ተሸፈነ፡፡ ሞተ ብዬ ሳስብ ጭሱ ፈገግ ሲል ቆሞ አየሁት፡፡ ሮጬ ስሄድ ሰውነቱ በሙሉ ደም ነው፡፡ “ሞገሴ” ስለው “እ…” አለኝ፡፡ “ደህና ነህ?” ስለው “ደህና ነኝ አንተስ?” አለኝ፡፡ “ደህና ነኝ ይኸ የምን ደም ነው?” ስለው ደሙን አይቶ ወደቀ፡፡ ያ ትንሽ አስደነገጠኝ፡፡ ሳልነግረው ብደግፈው ሮኖ ምናልባት አይወድቅም ነበር፡፡ ወዲያው አምቡላንስ ጠየቅን፡፡ ታክሞ ዳነ፡፡ መለሰ ዘርይሁን ደግሞ ነበር፡፡ ኮርያኖች መከላከያ መሥመራችንን በሽቦ ያጥራሉ፡፡ በጠላት መድፍ ተደብድቦ የሳሳ አለ፡፡

ያ ጠላት እንዲያጠቃ መከላከያ ነው ቀድሞውኑ፡፡ ያንን ለማሳጠር ጠይቀን የኮርያ ሰርቪስ ቡድን የሚባል አለ፡፡ እሾሃም ሽቦውን ያጥራሉ፡፡ ብረቱን ለመትከል ድምፅ ሲያሰሙ ያንን የሰማ ጠላት ከባድ መሣርያ ይተኩሳል፡፡ ሲመጣ መሃከላቸው ያርፋል፡፡ ብዙዎቹ ቆሰሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሞቱ፡፡ አንድ ወታደር እርዱኝ ብሎ ጮኸ፤ ቆስሎ፡፡ በኃይል ጮኸ፡፡ ወታደሮቻችን ያለ ትዕዛዝ ከዚያ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ መለሰ ዘርይሁን ግን አላስችል ብሎት ከሁለት ሦስት ወታደሮች ጋር ዘሎ ይወጣና ሁሉም ቁስለኞች ተሸክመው የቆሰሉትን ወደ መስመር ሲመልሱ፣ ሁለተኛውን ሰው ሲታደግ ሌላ ፈንጂ መጣና ሁለቱንም አብሮ ገደላቸው፡፡ በደም የተሳሰረ ወዳጅነት የምንለው አሁን ያ ነው፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን ኮርያዊ ነው፡፡ የሁለቱ ደም ተቀላሏልና በደም የተሳሰረ ወዳጅነት እንላለን፡፡

የአሁን ኑሮዎ እንዴት ነው?

ጃንሆይ የሰጡን አንድ ነገር ነው፡፡ ወደ ኮርያ ስንሄድ አንድ ሰንደቅ ዓላማ ሰጥተውናል፡፡ ይኼን ሰንደቅ ዓላማ መመርያ አድርጋችሁ እንድትዘምቱ፣ በተሰማራችሁበት ቦታ ጀግንነት ሠርታችሁ በደረታችሁ ላይ ልዩ ምልክት አድርጋችሁ በኩራት ስትመለሱ በአደራ የሰጠናችሁን አርማ መልሳችሁ እንድታስረክቡን ነው ያሉት፡፡ ያንን መልሰን አስረክበናቸዋል፡፡ ጃንሆይ ስለወታደርነት የተናገሩት አንደ ነገር አለ፡፡ “ወታደርና ጊዜው” የሚለው የክብር ዘበኛ የመጀመርያው የወታደር ጋዜጣ አለ፡፡ እዚያ ላይ ያሰፈሩት ምንድነው.. “የጦር ሰው ፖለቲካን መልመድ ወላዋይነትን ያስከትላል፡፡ ሲታዘዝም ለምን ማለት ሃፍረት ነው” ብለዋል፡፡ የሄድነው ታዘን ነው፡፡ ስንመለስ ይህን አድርጉልን አላለንም፤ እሳቸውም አላደረጉልንም፡፡ ኮንጎም ዘምቻለሁ፡፡ ከዚያ ስመለስ ትንሽ ፍራንክ ተጠራቅማ ጠብቃኝ ነበር፡፡ በዚያች ፍራንክ ቦታ ገዛሁኝ፡፡ በቦታዋ በደርግ ጊዜ ቤት ሰራሁባት፤ ሳትወረስ ጠብቃኝ ነበር፡፡ ከሰራሁም በኋላ አልተወረሰችም፡፡ ትንንሽ ትንንሽ ቤቶች ሠርቻለሁ፡፡ ያንን እያከራየሁ ስለምኖር በጣም ጥሩ ኑሮ ነው የምኖረው፤ ከጓደኞቼ አንፃር ስመለከተው፡፡

እንዴት ገዙ?

ልጆቼ ይረዱኛል፡፡ የመኪና ዋጋም የዋጋ ግሽበቱም እንዲህ አልነበረም፤ እኔ መኪና ስገዛ፡፡ ሦስት ወንድ ሦስት ሴት ልጆች አሉኝ፡፡ ኢንጂነሮች፣ የሕግ ባለሙያዎች ወዘተ ናቸው፡፡ በባህላችን ልጅ አይቆጠርም፡፡

የደቡብ ኮርያ መንግስት ለማህበራችሁ ስላደረገው ድጋፍ ቢያብራሩልኝ?

የተለየ ነገር አላደረገም፡፡ ነገር ግን ለኮርያ ዘማች ልጆች የነፃ ትምህርት እድል ሰጥቷል፡፡ ለዘማቹ ያደረገው የጎላ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ኮርያኖች መጀመርያ በተሰለፍንበት የጦር ግንባር አካባቢ ለምቶ ከተማ ካደረጉ በኋላ፣ በተለይ ቹንቾን በተባለ አካባቢ የማህበራችንን ሕንፃና ሐውልት በከንቲባ አርከበ እቁባይ ጊዜ ሠርቶልናል፡፡

ሌላው የኮርያ ወርልድ ቪዥን፤  በሰባት ሚሊዮን ብር መዝናኛ ማዕከል ለመሥራት ቃል ገብተዋል፡፡ ምስጋናውን ከቻልክ በኮርያንኛ አስተላልፍልን፡፡ ሕንፃውን ቶሎ እንዲጀምሩ አስታውስልን፡፡