ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 10
Appearance
- ፲፯፻፺፰ ዓ/ም - የሱዌዝ ቦይን የገነባው መሐንዲስ እና የፈረንሳይ ወኪል ፈርዲናንድ ደ ለሴፕስ በዚህ ዕለት ተወለደ
- ፲፰፻፴፬ ዓ/ም - በሸዋ ንጉዛት ከተማ አንጎለላ ላይ ሣህለ ሥላሴ ንጉሠ ሸዋ ከብሪታንያ መንግሥት ጋር "የወዳጅነትና የመነገድ አንድነት" ውል ተፈራረሙ።
- ፲፰፻፶፯ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት አብርሃም ሊንከን በጌቲስበርግ ፔንሲልቫኒያ የወታደሮች መቃብር በመረቁበት ጊዜ በታሪክ የ”ጌቲስበርግ ንግግር” አሰሙ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞ ባለ-ሥልጣናትን በሙስና እና የአስተዳደር ጉድለት ወንጀል በሕግ ለመመርመር የተሠየሙትን ሁለት ልዩ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ሕጋዊ የሚያደርገው አዋጅ ቁጥር ፯ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፸ ዓ/ም - የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ምናኽም ቤጊን ግብዣ በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ “ክኔሰት” ንግግር አደርጉ። ሳዳትም ይኼን ታሪካዊ ድርጊት በመፈጸም የመጀመሪያው አረባዊ መሪ ናቸው።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም- በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (US Congress)፣ የሕግ ሸንጎ በሞኒካ ሌዊንስኪ የአመንዝራ ኃጢአት በፈጸሙት በፕሬዚደንት ዊሊያም ጀፈርሰን ክሊንተን ላይ የክሱ ዝርዝር እና ምስክሮች መሰማት ጀመረ።