ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 18
Appearance
- ፲፱፻፴፬ ዓ/ም የፋሺስት ኢጣልያን የመጨረሻውን ይዞታ ጎንደርን ለማስለቀቅ አባቶቻችን አርበኞች ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በከተማዋ ዙሪያ ውጊያቸውን ጀመሩ። በዚሁ ዕለት ጄኔራል ናሲ ከነሠራዊቱ እጁን ሰጥቶ የአገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በፋሲለደስ ግንብ ላይ ተውለበለበ። በታሪክ መዝገብ የድል ቀን ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፬፻፴፫ዓ/ም ቢባልም ኢትዮጵያ ከፋሺስቶች የተላቀቀችበት ዕለት ግን ኅዳር ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ/ም ነው።
- ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በከፊል በናዚ ጀርመን ቁጥጥር ስር፤ በከፊል ደግሞ በጀርመን ደጋፊው የቪሺ አስተዳደር ስር የነበረችው የፈረንሳይ የባሕር ኃይል ቱሎን ወደብ ላይ የተሰበሰቡትን መርከቦቿን፣ በናዚዎች ቁጥጥር ስር እንዳይውሉ አሰመጧቸው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጃዋሃርላል ኔህሩ አሜሪካ እና የሶቪዬት ሕብረት የኑክሊዬር መሣሪያዎችን መፈተሻቸውን እንዲያቆሙና እንዲያውም ያላቸውን የኑክሊዬር መሣሪያዎች እንዲያጠፉ አቤቱታቸውን አቀረቡ።