ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 15
Appearance
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ራስ ደስታ ዳምጠውቡታጅራ አካባቢ ላይ በትግራይ ተወላጁ በደጃዝማች ተክሉ መሸሻ ተይዘው በፋሺስት ኢጣልያእጅ ወደቁ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ግብጽ እና ሶርያ የአረብ ሪፑብሊ ኅብረትን (United Arab Republic) መሠረቱ። ይሄ የሁለቱ አገሮች ኅብረት ከሦስት ዓመታት በኋላ ቢፈርስም የግብጽ መጠሪያ ስሟ ሆኖ ለብዙ ዓመታት ቆይቷል።.
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ሎንዶን በሕክምና ላይ የነበሩትን የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ፣ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰንን ለመጠየቅ መጥተው የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በዛሬው ዕለት በባኪንግሀም ቤተ መንግሥት ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ የ’ሻይ’ ግብዣ አደረጉላቸው።