ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 11
Appearance
- ፲፭፻፲፫ ዓ.ም - የፖርቱጋል ተወላጅ ፈርዲናንድ ማጄላን በደቡብ አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ መርከብ የሚያስተላልፍ በስሙም የሚጠራውን የማጄላን ስትሬይት (Magellan Straits) አገኘ።
- ፲፯፻፺፰ ዓ.ም. - በታዋቂው የብሪታንያ የባህር ኃይል አበጋዝ ሆሬሽዮ ኔልሰን መሪነት ከፈረንሳይና ከእስፓኛ ከተውጣጣ የባሕር ኃይል ጋር የትራፋልጋር ውጊያ (Battle of Trafalgar) እየተባለ በታሪክ በሚታወቀው ጦርነት የብሪታንያ ኃይል ድልን ተቀናጀ። ሆሬሽዮ ኔልሰንም በዚሁ ውጊያ ሞተ።
- ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. - ዳይናማይትን የፈጠረ፤ ፖካርሲ(chemist) ፤ መሐንዲስ እና የጦር መሣሪያ ሠሪ የነበረው እንዲሁም የኖቤል ሽልማትን የመሠረተው የስዊድን ተወላጅ አልፍረድ በርንሃርድ ኖቤልበዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ.ም - የመጀመሪያዋ ሐጽናሚ(Medical Nurse) በመባል ስሟ የሚታወቀው ፍሎሬንስ ናይቲንጌል ከ፴፰ ሐጽናሚያን ጋር ወደ ክራይሚያ ጦርነት ዘመቱ።
- ፲፰፻፸፩ ዓ.ም - ከጨሊዛ(carbon) የተሠራ ክር በመጠቀም ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የመጀመሪያውን የጾፓስ(electric) መብራት ብልቃጥ ሞከረ። ይኼውም መብራት ከመቃጠሉ በፊት ለ ፲፫ ሰዐት ተኩል አበራ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የሮማ ኦሊምፒክ የማራቶን ድል አድራጊው አበበ ቢቂላበቶክዮ ውድድር የራሱን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰከንድ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ድልን ተቀዳጀ። ከዚህ ድል ከሰላሳ ስድስት ቀናት በፊት ትርፍ አንጀቱን በቀዶ ሕክምና አስወግዶ ስለነበረ፣ ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳያገግም በአዲስ ክብረ ወሰን ማሸነፉ በማራቶን ውድድር እስካሁን ድረስ አቻ የለሽ ጀግና አድርጎ አስመስክሮለታል።
- ፲፱፻፹፩ዓ.ም - የቀድሞው የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርቆስና ሚስታቸው ኢሜልዳ ማርቆስ በማጭበርበር ወንጀል ኒው ዮርክ ተከሰሱ።