ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 16
Appearance
- ፲፱፻፲፪ ዓ.ም - የመጨረሻው የኢራን ንጉሠ ነገሥት ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ በዚህ ዕለት ተወለዱ
- ፲፱፻፵ ዓ.ም - የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ሚስትና ስድሳ ሰባተኛዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂላሪ ሮዳም ክሊንተን ተወለዱ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ.ም - በብሪታንያ ብሔራዊ ምርጫ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበሩት በዊንስተን ቸርቺል የሚመራው የኮንሰርቫቲቨ ፖለቲካ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቸርቺልም ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. - የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ቦይንግ 707 አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ ከኒው ዮርክ ከተማ ተነስቶ በፈረንሳይ አገር ፓሪስ ከተማ ድረስ በረረ።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም - ለ ሀያ ስድስት ዓመት በኢራን አልጋ ላይ ከተቀመጡ በኋላ ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ በ፵፰ኛው የልደት በዓላቸው፣ በራሳቸው እጅ ዘውድ ጫኑ። የሚስታቸውን የንግሥት ፋራንም ዘውድ ጫኑላቸው።