ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 5
Appearance
- ፲፭፻፸፭ ዓ.ም. - የግሪጎሪያዊ ዘመን አቆጣጠር በዛሬው ዕለት በኢጣልያ፤ በፖላንድ ፤ በፖርቱጋል እና በእስፓንያ ከመስከረም ፳፭ ቀን በቀጥታ ወደ ጥቅምት ፭ ቀን በመዝለል ተጀመረ።
- ፲፮፻፺፱ ዓ/ም - በዓፄ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥት ልዑል ሰገድ) ትዕዛዝ፣ ሸሽተው ጣና ሐይቅ ላይ በጨቅላ መንዞ ደሴት የነበሩትን አባታቸውን ዳግማዊ ኢያሱ አድያም ሰገድን ጳውሎስ እና ደርመን የተባሉ ነፍሰ ገዳዮች ሕይወታቸውን ካጠፉ በኋላ አስከሬናቸውን በእሳት አቃጠሉት። ከቃጠሎ የተረፈውን ካህናቱ በታንኳ ወስደው ምጽራሓ ደሴት ላይ ቀበሩት።
- ፲፯፻፩ ዓ/ም - ከ፪ዓመት በፊት በዚህ ዕለት ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱን (ስመ መንግሥት አድያም ሰገድ) የገደሉትን ጳውሎስ እና ደርመንን ንጉሠ ነገሥቱዓፄ ቴዎፍሎስ የስቅላት ሞት ፍርድ ፈረዱባቸው።
- ፲፰፻፰ ዓ.ም. - የፈረንሳይ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ ናፖሌዮን በወተርሉ ጦር ሜዳ ላይ ከተሸነፈ በኋላ በአሸናፊዎቹ በብሪታንያ ቁጥጥር ሥር አትላንቲክ ውቅያኖስ ወደምትገኘው የቅድስት ሔሌና ደሴት ተሰደደ።
- ፲፰፻፴፯ ዓ.ም. - ታዋቂውና ተቀዳሚው የጀርመን ፈላስፋ ፍሬድሪክ ቪልሄልም ኒቺ ተወለደ።
- ፲፱፻፫ ዓ.ም. - ታዋቂው ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንዳዶም ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ ተወለዱ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በፈረንሳይ አገር የናዚ ጀርመን ደጋፊ የነበረው የቪሺ አስተዳደር ጠቅላይ ሚንስቴር የነበሩት ፒዬር ላቫል በሞት ተቀጡ። ላቫል ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከነበሩት ዊሊያም ሆር ጋር በታኅሣሥ ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለፋሽሽት ኢጣልያ በሚያመች መልክ ለመከፋፈል የምስጢራዊ ስምምነት የፈጸሙ ናቸው።
- ፲፱፻፴፱ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወንጀለኛነቱ የሞት ቅጣት የተፈረደበት ኸርማን ጎሪንግ ለቅጣቱ መፈጸሚያ ጥቂት ሰዐታት ሲቀሩ ሳያናይድ መርዝ በመውሰድ ራሱን ገደለ
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. - የቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት መሪ የነበሩት ኒኪታ ክሩስቼቭ ከሥልጣን ተሽረው፣ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት በአሌክሲ ኮሲጊን፤ በኮሙኒስት ፓርቲ ሊቀመንበርነት ደግሞ በሌዮኒድ ብሬዥኔቭ ተተኩ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ ልጅ መቶ-ዓለቃ ልዑል መኮንን መኮንን ትምህርት ላይ ከነበሩበት ከአሜሪካ ወደአገራቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ደርግ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. - የቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚካይል ጎርባቾቭ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፹፮ ዓ.ም. - የደቡብ አፍሪቃ መሪዎች ኔልሰን ማንዴላና ፍሬድሪክ ዊሌም ደክለርክ የዓመቱ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊዎች መሆናቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው የያዘች የሰማይ መንኮራኩር ተኮሰች።