ዱዱ
Appearance
ዱዱ ከ2010 እስከ 2001 ዓክልበ. ግድም የአካድ ንጉሥ ነበረ።
በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከሻርካሊሻሪ ቀጥሎ አራት ተወዳዳሪዎች እነርሱም ኢሉሉ፣ ኢርጊጊ፣ ኢሚ፣ እና ናኑም ለ፫ ዓመት ይወዳደሩ ነበር። ከዚያ ዱዱ ለ፳፩ ዓመት እንደ ነገሠ ይዘግባል። ሆኖም እንደ ቀዳሚዎቹ ሳይሆን ለእርሱ ዘመን አንዳችም «የዓመት ስም» አልተረፈልንም። እንግዲህ እንደዚህ ረጅም ጊዜ መግዛቱ አጠያያቂ ነው።
በዚህ ዘመን ጉታውያን አብዛኛውን መስጴጦምያን ወርረው የዱዱ ግዛት ከአካድ ከተማ እንዳልራቀ ከጥቂት ቅርሶች ሊታወቅ ይቻላል። እንዲሁም ወደ ደቡብ በተገኙት በአካድ ቀድሞ ተገዥ አገራት በኤላም፣ ኡማና ጊርሱ ላይ እንደ ዘመተ ይመስላል።[1]
ዝርዝሩም እንዳለው የዱዱ ልጅ ሹዱሩል በዙፋኑ ላይ ተከተለው።
ቀዳሚው ኢሉሉና ሦስት ሌሎች |
የአካድ ንጉሥ 2010-2001 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሹዱሩል |
- ^ Gwendolyn Leick, 2002, Who's Who in the Ancient Near East, p. 49.