ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አሜሪካ)
Appearance
(ከዲሞክራቲክ ፓርቲ (አሜሪካ) የተዛወረ)
ዲሞክራቲክ ፓርቲ (እንግሊዝኛ: Democratic Party) በአሁኑ ጊዜ ካሉት የአሜሪካ ሁለት (ማለትም ሪፐብሊካንን ጨምሮ) ዋና ዋና ፓርቲዎች አንዱ ነው። ይህ የፖለቲካ ፓርቲ በዓለማችን ረዥሙን እድሜ ካስቆጠሩት ፓርቲዎች አንዱ ሲሆን በአሜሪካም ቢሆን ለረጅም ዘመን ተከታታይ አለመፍረስን ያሳየ ነው። በ2004 እ.አ.አ. 72 ሚሊዮን የሚደርሱ የተመዘገቡ ድምፅ ሰጭዎች ነበሩት።[1] በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሆኑት ባራክ ኦባማ በፓርቲው ታሪክ የፕሬዝዳንትነትን ማዕረግ ያገኙ 14ኛው ዲሞክራት ሲሆኑ 15ኛው ፕሬዝዳንት ናቸው።
- 7ኛው አንድሪው ጃክሰን
- 8ኛው ማርቲን ቫንቡረን
- 11ኛው ጄምስ ፖልክ
- 14ኛው ፍራንክሊን ፒርስ
- 15ኛው ጄምስ ቡካነን
- 22ኛው እና 24ኛው ግሮቨር ክሊቭላንድ
- 28ኛው ውድሮው ዊልሰን
- 32ኛው ፍራንክሊን ሮዘቨልት
- 33ኛው ሃሪ ትሩማን
- 35ኛው ጆን ኤፍ ኬኔዲ
- 36ኛው ሊንደን ጆንሰን
- 39ኛው ጂሚ ካርተር
- 42ኛው ቢል ክሊንተን
- 44ኛው ባራክ ኦባማ