ግመል

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
487px-07. Camel Profile, near Silverton, NSW, 07.07.2007.jpg

ግመል ሙሉ ጣት ሸሆኔ ካላቸው እንስሳ የሚመደብ ለማዳ የቤት እንስሳ ወገን ነው። በዋነኛነት ጀርባው ላይ ባለው በስብ የተሞላ አካል (ሻኛ) ይታወቃል። ይህ ሻኛ የአረቦች ግመል በሚባለው ዝርያ ላይ አንድ ብቻ ሲሆን፣ ሌላው ዝርያ በሰሜን ምስራቅ እስያ የሚገኘው ባክትሪያን ግመል ደግሞ ሁለት ነው። በአብዛኛው ደረቅ በረሀ ለመኖር የሚመቻቸው ሲሆን በብዛት በምዕራብ እስያ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ እስያ ይገኛሉ። የሠው ልጅ የሚያለምዳቸው ለወተት ምርት፣ ለስጋ እንዲሁም አልፎ አልፎ ለመጓጓዣ ስለሚጠቅሙ ነው።