ጎጃም ክፍለ ሀገር
ይህ መጣጥፍ የውክፔዲያ የአቀማመጥ ልምዶችን እንዲከተል መስተካከል ይፈልጋል። |
ጎጃም በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግሥት የነበረው ከፍለ-ሃገር ነው። ጎጃም ውስጥ ኣሉ ከሚባሉት ከተሞች እንደ ባሕር ዳር ፡ ደብረ ማርቆስ ፡ፍኖተ ሰላም ፡ቡሬ ፡ኮሶበር ፡ ዳንግላ ፡ቻግኒ ፡ ኣዴት ፡ መራዊ ፡ ሞጣ፡ ቢቸና፡ ደጀን ይገኙበታል ፡፡
ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች መፈጠሪያ እንዲሁም የዓባይ እና የጣና ባለቤት ናት ፡፡
ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ ር) (1902- 1996 )ኣ.ም ኣቤ ጉበኛ (1925 - 1972 )ኣ.ም ዮፍታሄ ንጉሤ(1897-1937 ) ኣ.ም የመሳሰሉ የጥበብ ሰወችን ኣፍርታለች ፡፡ ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። በተለይ የአዴት ጤፍ በባህር ዳር ጎንደር ደሴ እና መቀሌ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት የታወቀ እና ተወዳጅም ነው። እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሞጣ ዙሪያ ወይንውሀ እና ጎንቻ ሲሶ ግንደወይን ዙሪያ የሚመረተው ጤፍ የአዲስ አበባን ህዝብ ገትሮ እንደያዘ ይነገራል።[[ቡሬ]] ዙሪያ የሚበቅለው በርበሬ በቆሎ ደግሞ የመላው የኢቲዮጵያን ህዝብ ገትሮ እንደያዘም ይነገርለታል፡፡ በነገራችን ላይ ቡሬ ዙሪያ ይህንን ብቻ አይደለም የሚያበቅል እንደ ጤፍ፣ሽንብራ፣ቦለቄ፣ዳጉሳ፣መጥቀስ ሆነብን እንጂ የማይበቅል ነገር የለም፡፡በዋናነትም ከ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ [[ገዳም ልጃሞር]] ቀበሌ ይህንን በማምረት ይጠቀሳል፡፡ ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል። ጎጃም የአባይ እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።ጎጃም በኣሁኑ ጊዜ ማለትም ኣገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከኣራት ኣስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥወስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።
ምዕራብ ጐጃም ዞን §የዞኑ ዋና ከተማ፡- ፍኖተ ሰላም
§የወረዳዎች ብዛት፡- 16
§የከተማ አስተዳደሮች ብዛት፡- 6
oባህር ዳር oፍኖተ ሰላም oመርዓዊ oቡሬ oደንበ ጫ o አዴት
§የቀበሌዎች ብዛት፡- 370
oየገጠር፡-328
oየከተማ፡-42
§በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 2714017
ወንድ 1 364 143
ሴት 1 349 874
የወረዳው ስም የወረዳው ዋና ከተማ
1 ሜጫ መርዓዊ
2ደምበጫ ደምበጫ
3ቡሬ ዙሪያ ቡሬ
4ወንበርማ ሺንዲ
5ጃቢ ጣህናን ፍኖተ ሠላም
6ባህር ዳር ዙሪያ ባህር ዳር
7ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት
8ሰከላ ግሽ ዓባይ
9ቋሪት ገበዘ ማርያም
10ሰሜን አቸፈር ቢን
11ደቡብ አቸፈር ዱር ቤቴ
12ይልማና ዴንሳ አዴት
13ጐንጅ ቆለላ አዲስ አለም
አዊ ዞን §የዞኑ ዋና ከተማ፡- እንጅባራ §የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት-122 ኪ.ሜ
§የወረዳዎች ብዛት፡- 7
§የከተማ አስተዳደሮች ብዛት፡- 3
oዳንግላ
oእንጅባራ
oቻግኒ
§የቀበሌዎች ብዛት፡- 201
oየገጠር፡- 180
oየከተማ፡- 21
§በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 1058 289
oወንድ916015
oሴት142274
የወረዳው ስም የወረዳው ዋና ከተማ
1አንካሻ ጓጉሣ አገው ግምጃ ቤት
2ባንጃ ሽኩዳድ እንጅባራ
3ጓጉሣ ሽኩዳድ ቲሊሊ
4ፋግታ ለኮማ አዲስ ቅዳም
5ዳንግላ ዳንግላ
6ጃዊ ፈንድቃ
7ጓንጓ ቻግኒ
ምስራቅ ጐጃም ዞን
§የዞኑ ዋና ከተማ፡- ደብረ ማርቆስ
§የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት፡-
249 ኪ.ሜ
§የወረዳዎች ብዛት፡- 16
§የከተማ አስተዳደሮች ብዛት ፡- 4
oደብረ ማርቆ oሞጣ
oቢቸና
oደጀን
§የቀበሌዎች ብዛት፡- 424
oየገጠር፡- 388
oየከተማ፡- 36
§በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 2 152 671
ወንድ1 066 09 ሴት1 086 577
የወረዳው ስም የወረዳው ዋና ከተማ
1ባሶሊበን የጁቤ
2ማቻከል አማኑኤል
3እነማይ ቢቸና
4ደባይጥላት ግን ቁይ
5ደጀን ዙሪያ ደጀን
6እናርጅና እናውጋ ደብረ ወርቅ
7ሁለት እጁ እነሴ ሞጣ
8 ቢቡኝ
ድጓፅዮን
9አዋበል ሉማሜ
10እነብሴ ሳር ምድር መርጡ ለማሪያም
11ጐዛምን ደብረ ማርቆስ
12 ስናን ረቡዕ ገበያ
13አነደድ አምበር
14ሸበል በረንታ የዕድ ውኃ
15ጐንቻሲሶ እነብሴ ግንደ ወይን
16ደብረ ኤልያስ ደብረ ኤልያስ
17 ሰዴ
ሰዴ
1. http://www.amhara.gov.et/web/communcation-affairs-office/information-desk?p_p_id=56_INSTANCE_o5RZ&p_p_lifecycle=0&p_p_state=normal&p_p_mode=view&p_p_col_id=column-2&p_p_col_count=1&page=8
2. «Bibliography of Ethiopian Writers» ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ - ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር (pdf)
#ስዩም ይዘንጋው ድንቁ (talk) 14:27, 23 ጁላይ 2019 (UTC)