ጓጉንቸር

ከውክፔዲያ
?ጓጉንቸር
Fossil range: ትራይሲክ
የዛፍ ጓጉንቸር
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: እንስሳ
ክፍለስፍን: አምደስጌ
መደብ: አምፊቢያን
ክፍለመደብ: ጓጉንቸር Anura
ብላሲየስ ሜሬም, 1820
የጓጉንቸሮች ስብጥር ካርታ
የጓጉንቸሮች ስብጥር ካርታ

ጓጉንቸርአምፊቢያን ዓይነት እንስሳ ስትሆን በውሃ አካባቢ ኑሮዋን ትመራለች። ከእንቁራሪት እና ጉርጥ ይልቅ ሰውነቷ የለሰለሰ ነው። የኋላ እግሮቿም ረዣዥም ስለሆኑ ከመራመድ ይልቅ መዝለል ማለት ይቀናታል።

ጓጉንቸር፣ እንደማንኛውም አምፊቢያን፣ በውሃ ውስጥና እና በደረቅ ምድር ላይ መኖር ትችላለች። የሆኖ ሆኖ ጓጉንቸር ጨው ባለበት ውሃ፣ ለምሳሌ በውቅያኖስ ውስጥ መኖር አትችልም፤ ትሞታለች።

ጓጉንቸርን መግድል ጠንቅ አለው፤ ምክንያቱም ጓጉንቸር በሽታ አስተላላፊ ትንኞችን ስለምትመገብ፣ እርሷ ስትሞት፣ እንደ ወባ አስተላላፊ ያሉ ትንኞች በብዛት መራባት ይችላሉና። ስለሆነም፣ የጓጉንቸር መኖር ጥቅሙ ከፍተኛ ነው።

በዘመናዊ ሥነ ሕይወት ረገድ፣ ክፍለመደቡ ሁሉ «ጓጉንቸር» ተብሏል፤ ከዚህም ውስጥ ብዙ አስተኔዎች በተለመደ «እንቁራሪት» እና ከነርሱም አንዱ አስተኔ «ጉርጥ» ይባላል።

ተረትና ምሳሌ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]