Jump to content

ፓይታጎረስ

ከውክፔዲያ
የፓይታጎረስ ሃውልት በቫቲካን

ፓይታጎረስጥንቱ ግሪክ ስሙ የገነነ ሐሳቢ እና ፈላስፋ ነበር፤ የተወለደው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ580 ዓክልበ. ሲሆን የሞተውም በ500 ዓክልበ. ነው። በአሁኑ ዘመን ታዋቂነቱ የሚመነጨው የፓይታጎረስ እርጉጥ ( ) የተባለውን የሂሳብ ቀመር በማግኘቱ ነው። በኖረበት ዘመን ፓይታጎሪያንስ የተሰኙ ቁጥር አምላኪ ቡድኖችን በመመስረቱ ይጠቀሳል። ፓይታጎረስ፣ በጥንቱ ዘመን ከነበረው የገነነ ስም አንጻር በፈላስፋው ፕላቶ አስተሳሰቦች ላይ ተፅእኖ በመፈጠር፣ በቀሪው የምዕራቡ አለም ስልጣኔ ላይ የማይደበዝዝ አሻራውን ትቶ አልፏል።

ፓይታጎረስ ሳሞስ በምትባል የግሪክ ደሴት የተወለደ ሲሆን፣ ከነበረበት የጊዜ ርቀት አኳያ የኅይወት ታሪኩ እምብዛም አይታወቅም። ባጠቃላይ መልኩ፣ ፓይታጎረስ በህጻንነቱ ጥሩ አስተዳደግ እንደነበረው፣ በኋላ ግን ከነበረው መንግስት ጋር በትምህርት አሰጣጥ አለመስማማቱ፣ ስለሆነም የራሱ ቡድን (ፓይታጎሪያንስ) መስርቶ ትምህርት እንዳስተማረ እንዲሁም የእርሱ ግሩፖች ስጋ እንደማይበሉና በጣም ጽኑ የሆኑ ደንቦችን ይከተሉ እንደነበር ይጠቀሳል። እያንዳንዱ የግሩፑ አባላት በፓይታጎረስ በራሱ ትምህርት ይሰጣችቸው ነበር።

በአንድ አንድ ታሪክ አጥኝወች ዘንድ ፍልስፍና የሚለውን ቃል ይህ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተጠቀመ ይገለጻል። በፓይታጎረስ ፍልስፍና መሰረት ተጨባጩ አለም ከሒሳብ ህጎች የተሰራና ቁጥሮች ደግሞ እውነተኛወቹ የውኑ አለም መሰረቶች ናቸው የሚል ነው። ይህ አስተሳሰብ በውነቱ ለዘመናዊው አለም ሳይንስ መሰረት የጣለ ነው። ፓይታጎረስ በፍልስፍና ብቻ ሳይሆን በሙዚቃ ጥናት እና በሥነ ፈለክ ጥናቶች ላይ ሰፊ የሆነ አስተዋጾን አበርክቷል። ብዙወቹ የፓይታጎራስ ግኝቶች ከሁለት ሺህ በላይ ዘመናት በኋላ አሁን ድረስ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

ፓይታጎረስ እርጉጥበምስል ሲተነተን

የቁጥር ሃይማኖት ለፓይታጎሪያኖች በጣም ወሳኝ ነበር። ሲምሉም በ "1+2+3+4" ነበር (ውጤቱ 10 መሆኑን እናስተውል)። በፓይታጎሪያኖች አስተሳሰብ ነፍስ ለዘለዓለም የማይጠፋ ነገር ነው። እንስሳትም ሆነ እጽዋት ነፍስ እንዳላቸው በኒህ ወገኖች የታመነ ነበር። ፓይታጎረስ እራሱ 4 ጊዜ በህይወት እንደኖረ ያምን ነበር። እየተደበደብ ባለ የውሻ ሰቆቃ ድምጽ ውስጥ የሞተ ጓደኛውን ድምጽ ያዳምጥ እንደነበር ተመዝግቦ ይገኛል። በተረፈ ፓይታጎረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሰው የሚገኙተን ነቢያት ህዝቅኤልንና ዳንኤልባቢሎን አገር ጎብኝቶ እንደነበር ይጠቀሳል።