Jump to content

7 ሶበክሆተፕ

ከውክፔዲያ

==

መርካውሬ ሶበክሆተፕ
«መርካውሬ ሶበክሆተፕ» የሚል በአንዱ ሐውልት
«መርካውሬ ሶበክሆተፕ» የሚል በአንዱ ሐውልት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1648-1646 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰዋጅካሬ ሆሪ
ተከታይ መርኸፐሬ ?
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

==


መርካውሬ 7 ሶበክሆተፕላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1648 እስከ 1646 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ የታወቀው ከሦስት ምንጮች ነው፦

  1. ቶሪኖ ቀኖና ሰነድ፣ ከሰዋጅካሬ ሆሪ ቀጥሎ «መርካውሬ ሶበክ[...]» ተዘረዘረ። ሁለት አመት፣ ሦስት ቀን እንደ ነገሠ ይላል።
  2. ካርናክ ዝርዝርም ላይ አንድ «መርካውሬ» ይገኛል፣ ይህ ዝርዝር ግን ቅድመ-ተከተል አይጠብቅም።
  3. ሁለት «መርካውሬ ሶበክሆተፕ» የሚሉ ሐውልቶች በሥነ ቅርስ ከካርናክንና አንድ ጥንዚዛ-ማህተም ተገኝተዋል።

ከመርካውሬ ሶበክሆተፕ ቀጥሎ እነማን በጤቤስ እንደ ገዙ ግልጽ አይደለም፤ ብዙ ስሞች ከቶሪኖ ቀኖና እንደ ጠፉ ይመስላል። ከሥነ ቅርስ የታወቁት ግን መርኸፐሬ እና ሰኸቀንሬ ብቻ ናቸው። እነዚህ ለረጅም ጊዜ እንደ ገዙ አይታስብም። በዚህም ሰዓት በአቢዶስ ዙሪያ አዲሱ የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ይታስባል። የሚቀጠለው የጤቤስ ፈርዖን ጀሁቲ16ኛው ሥርወ መንግሥት ጀማሪ ተብሏል።

በዚሁ ዘመን የሥርወ መንግሥቱ ሥልጣን ከጤቤስ ከተማ በጣም እንዳልራቀ፣ ሂክሶስም ወገኖች በስሜን እንደ ገዙ ይታስባል።

ቀዳሚው
ሰዋጅካሬ ሆሪ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1648-1646 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መርኸፐሬ ?
  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)