ከ«ምጽራይም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.6.5) (ሎሌ መጨመር: nl:Mitsrajim
r2.5.4) (ሎሌ መጨመር: pl:Misraim
መስመር፡ 31፦ መስመር፡ 31፦
[[he:מצרים (דמות מקראית)]]
[[he:מצרים (דמות מקראית)]]
[[nl:Mitsrajim]]
[[nl:Mitsrajim]]
[[pl:Misraim]]
[[pt:Mizraim]]
[[pt:Mizraim]]
[[ru:Мицраим]]
[[ru:Мицраим]]

እትም በ19:06, 12 ሴፕቴምበር 2012

ምጽራይም (ዕብራይስጥמִצְרָיִם /ሚጽራዪም/) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት ከኖህ ልጆች መካከል የካም ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የምጽራይምም ልጆች ሉዲምዐናሚምላህቢምነፍታሌምፈትሩሲምከስሉሂምቀፍቶሪም ናቸው።

የ«ሚጽራዪም» ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ ግብጽ (ምሥር) አገር ነው። እንዲሁም በአረብኛ የአገሩ ስም مصر (ምጽር) ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በአካድኛ መዝገቦች የግብጽ ስም «ሙሱር»፣ «ሙስሪ»፣ በኡጋሪትም ጽላቶች «ምስርም» ተብሏል።

አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶችእስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም (ማሣር ወይም መሥር) ተሠጠ ብለው ጻፉ። በነዚህም ደራስያን ዘንድ የመሥር ዕድሜ እስከ 700 መቶ አመት ድረስ ደረሰ።

ፊንቄ አፈ ታሪክ ደግሞ «ሚሶር» የሚባል ሰው የታዓውቶስ አባት ሲሆን የቢብሎስ ንጉሥ ክሮኖስ ግብጽን ለዚሁ ታዓውቶስ እንደ ሰጠ ይታመን ነበር።

በዕብራይስጥ ስዋሰው «-አዪም» የሚለው ባዕድ መድረሻ የድርብ ቁጥር ምልክት ሲሆን ስሙ 'ሁለት ምድሮች' ይመስላል፤ የዚህም ትርጉም በጥንታዊ ግብጽኛ «-ታ-ውይ» ነው። ከግብጽ መካከለኛ ዘመን መንግሥት ጀምሮ ግብጽ «-ታ-ውይ» (ሁለቱ ምድሮች ወይም «ላይኛው መንግሥት» እና «ታችኛው መንግሥት») ይባል ነበር።

ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ (800 ዓ.ም. አካባቢ) ግን ምጽራይም የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት የመሠረተው ፈርዖን መኔስ እንደ ነበረ ገመተ።

ሌሎች አጻጻፎች

  • ግሪክ ትርጉም፦ Μεστράιμ /መስትራይም/
  • መጽሐፈ ኩፋሌ፦ ሜስጥሮም
  • ኦሪት ዘፍጥረት፣ ልዩ ልዩ ግዕዝ ቅጂዎች፦ ምሴጣሬም፣ ሴጣሬም፤ ሚጣራም፣ ምስጢየረም