Jump to content

ኤላም (የሴም ልጅ)

ከውክፔዲያ

ኤላም (עֵילָם) በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት (የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ) 10፡22 መሠረት ከኖኅ ልጆች መካከል የሴም በኩር ልጅ ነበረ።

«ኤላም» ማለት በብሉይ ኪዳን ደግሞ ጥንታዊት ሀገር ኤላምና ሕዝቧ ያመለከተ ነው። እኚህ ሕዝብ ከኤላም ሴም ኖኅ እንደ ተወለዱ ይታመናል። የአሁኑ ሊቃውንት ኤላምኛሴማዊ ቋንቋዎች መካከል አለመገኘቱ ቢያወቁም፤ በኦሪት ዘፍጥረት አስተያየት የሰው ልጅ ልሳናት ሁሉ በባቢሎን ግንብ ስለ ተደበለቁ የቋንቋ አለመዛመድ ጥያቄ ምንም አያስቸግርም።

የኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምርአብርሃም ዘመን ጦርነት በከነዓን አገር እንዳዋጀ በዘፍጥረት 14 ይጠቀሳል።

ትንቢተ እሳይያስ (11:11, 21:2, 22:6) እና በትንቢተ ኤርምያስ (25:25) ኤላም ሀገር ትጠቀሳለች። በትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 49 መጨረሻ (49፡36-39) በይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ መጀመርያ አመት (606 ዓክልበ.) ለነቢዩ ኤርምያስ የመጣው ስለ ኤላም የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል።

መጽሐፈ ኩፋሌ 9፡16 መሠረት ከጤግሮስ ወንዝ ምስራቅ በፈርናኬም ጎን ከነሕንደኬ ለኤላም ርስት ዕጣ ደረሰ። በተጨማሪ ኤርትራ (በግዮን ወንዝና በቀይ ባሕር መካከል ያለው) የኤላም ርስት ሆነ።

በተጨማሪም በኩፋሌ. 8፡34 የኤላም ልጅ ሱስን ልጅ ራሱአያ አርፋክስድን እንዳገባች ይላል። ሱስን (ሹሻን) የኤላም ጥንታዊ ዋን ከተማ ስም ነበረ።