ኅዳር ፲፫
Appearance
ኅዳር ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በዳላስ፣ ቴክሳስ ሠላሳ አምሥተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጠመንጃ ጥይት ተገድለው ሞቱ። በሚጓዙበት ተሽከርካሪ ውስጥ አብረዋቸው የነበሩትም የቴክሳስ ገዥ ጆን ኮናሊ በጥይት ተመተው ቆስለው ነበር። በዚህም ታሪካዊ ድርጊት የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ ተይዞ በቁጥጥር ሥር ሆነ። የዚያኑ ዕለት ምክትል ፕሬዚደንቱ ሊንደን ቢ ጆንሰን ሠላሳ ስድስተኛው ፕሬዚደንት ሆነው የመሀላ ሥርዐታቸውን በመፈጸም ስልጣኑን ተቀበሉ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በእስፓኝ አምባ ገነኑ ፕሬዚደንት ፍራንሲስኮ ፍራንኮ በሞቱ በሁለተኛው ቀን ቀዳማዊ ሁዋን ካርሎስ የአገሪቷ ንጉሥ ተባሉ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በናይጄሪያ በወቅቱ ሊካሄድ በታቀደው ከ”ወይዘሪት ዓለም” የቁንጅና ውድድር ጋር በተያያዘ ጉርምርምታ መነሻነት “ThisDay” በተባለ የናይጄሪያ ጋዜጣ ላይ የወጣው ‘ሐይማኖት ነክ’ አንቀጽ ባስከተለው ሽብር ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ውድድሩም በዚሁ ሽብር ምክንያት ወደ ለንደን ተዛወረ።[1]
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በዩክራይን የተካሄደውን የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሕዝቡ ትልቅ ጭብርብርነት ተፈጽሟል በሚል መነሻነት፣ በብዙ አሥራት ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ የዕጩዋቸውን፣ የቪክቶር ዩሽቼንኮን ስም እየጠሩ የኪዬቭን ከተማ አጥለቀለቋት። ይሄውም የተቃውሞ ሰልፍ “የብርቱካን አብዮት” (Orange Revolution) ተብሎ የተሰየመውን ቅስቀሳ የተጀመረበት ዕለት ነው።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - በጀርመን ፌዴራላዊ ሪፑብሊክ፣ አንጌላ መርክል የአገሪቷ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መንግሥት (Chancellor) በመሆን የመሀላ ስርዐት ፈጽመው ሥልጣን ተቀበሉ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአገራቸውን የነጻነት ትግል በመምራት፤ ከነጻነትም በኋላ በፕሬዚድንትነት ያገለገሉት ፈረንሳዊ ጄነራል ሻርል ደ ጎል
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በተለይም ሄልሲንኪ ላይ በ፲፱፻፵፭ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር በአምሥት እና በአሥር ኪሎሜትር እንዲሁም በማራቶን የሩጫ ውድድሮች አሸናፊነቱ ስመ ጥሩነትን ያተረፈው የቼክ አትሌት ኤሚል ዛቶፔክ (“የቼኩ ባቡር”)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974