Jump to content

ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ

ከውክፔዲያ
(ከማይክል አንጄሎ የተዛወረ)
ማይክል አንጄሎ , በዳኒዬሌ ዳ ቮልቴራ
የማይክል አንጄሎ ሐውልት ጋሌሪያ ዴሊ ኡፊዢ በ ፌሬንዜ

ማይክል አንጄሎ ዲ ሎዶቪኮ ቡናሮቲ ሲሞኒ (6 ማርች 1475 - 18 ፌብሩዋሪ 1564) በተለምዶ ማይክል አንጄሎ እየተባለ ይጠራ የነበረው የእንደገና መወለድ ተብሎ በሚጠራው ዘመን ይኖር የነበረ ኢጣሊያዊ ሰዓሊ ፤ ቀራጭ፤ ህንጻ ሰሪ፤ ገጣሚ፤ እና መሀንዲስ ነበር። ምንም እንኳን ቅንድብን ወደ ላይ ከማስነሳቱ ባሻገር ይጠቀምባቸው የነበረው ስነ ስርአቶች እጅግ በጣም ከፍተኛ ደረጃ በመሆናቸው የእንደገና መወለድ ሰው የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶት ነበር። እሱን በመሳሰሉ ታላላቅ ሰዓሊዎች ለምሳሌ ሊዮናርዶ ዳቪንቺ። ማይክል አንጄሎ በረጅም የእድሜ ዘመኑ በሰራቸው በማናቸውም የስራ ውጤቶቹ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበሩ። ታሪካቸው በደንብ ከተመዘገበላቸው የ16ኛው ክፍለ ዘመን ሰአሊዎችም አንዱ አድርጎታል። እጅግ በጣም ከሚወደዱት ሁለት ስራዎቹ መሀከል ፒየታ = ሐዘን እና ዳዊት የሚባሉትን ሰርቶ የጨረሰው እድሜው ሠላሳ ከመሆኑ በፊት ነበር። ምንም እንኳን ለስዕል የነበረው አመለካከት በጣም ዝቅተኛ ቢሆንም ማይክል አንጄሎ ሁለት ድንቅ የተባሉ ስእሎችን በጄሶ ላይ በመስራት ለምዕራቡ አለም አበርክቷል። ዘፍጥረትን ሲስቲኒ በሚባለው ቤተ ክርስቲያን ጣራ ላይ እና የፍርድ ቀን የተባለውን ደግሞ በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመንበሩ በስተጀርባ በኩል በሮማ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ። ማይክል አንጄሎን ልዩ ከሚያደርገው አንዱ ነገር የመጀመሪያው የምእራብ አለም ሰዓሊ በህይወት ዘመኑ እያለ የህይወት ታሪኩ የተጻፈለትም በመሆኑ ነው። ሁለት የተለያዩ ጸሃፊዎች በህይወት እያለ ታሪኩን ጽፈውታል። አንደኛው ጂዮርጂዮ ቫሳሪ ሲሆን እርሱም ማይክል አንጄሎ እንደገና መወለድ ካፈራቻቸው የኪነ ጥበብ ሰዎች አናት ነው ብሎ ከፍተኛውን ስፍራ ይሰጠዋል። እስከ አሁን ድረስም ይህ አባባል እንደቀጠለ ይገኛል። በህይወት ዘመኑም እያለ የተቀደስው ወይም የተባረከው የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶት ነበር[13]።

የወጣትነት ጊዜው

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሎሬንዞ ዲ ሜዲቺ ሞት በ 8 አፕሪል 1492 ለማይክል አንጄሎ ትልቅ ለውጥ አምጥቶለታል[14]ማይክል አንጄሎ የሜዲቺን አጥር ግቢ ትቶ ወደ አባቱ ቤት ተጓዘ። በሚቀጥሉት ወራትም ከእንጨት (1493) የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ከእንጨት ቀርጾ ለፍሎሬንቲን ቤተ ክርስቲያን ሳንቶ ስፒሪቶ በስጦታ አበረከተ። በአንጻሩም በቤተክርስቲያኑ ሆስፒታል በነበረው ውስጥ የሰውነትን ቅርጽ እና አሰራር በሞቱ ሰዎች አስከሬን በሆስፒታሉ ውስጥ ተለማምዷል። [15] ከ 1493 እና 1494 ግዙፍ የሆነ ዕምነ በረድ ገዝቶ ሄርኩለስን ቀረጸ። ይህ ቅርጽ በሺያጭ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ የደረሰበት ጠፋ 1700.[12][c] በ 20 ጄንዋሪ 1494 በጣም ከፍተኛ በረዶ ከጣለ በኋላ ሎሬንዞ ፒኤሮ ዲ ሚዲቺ የበረዶ ቅርጽ ውድድር አዘጋጀ። ማይክል አንጄሎም ወደ ሜዲቺ ቅጥር ግቢ ለውድድር እንደገና ገባ።

በዚያው አመት የሜዲቺ ቤተሰብ ከፍሎሬንስ ከስልጣን በሳቮናሮላ ተወገዱ። ማይክል አንጄሎ የፖለቲካው ግርግር ከማለቁ በፊት ፍሎሬንስን ትቶ ወደ ቬኒስ ከዚያም ወደ[14] ቦሎኛ አቀና። በቦሎኛ አንድ ውል ተዋዋለ። ውሉም ተጀምሮ ያላለቀ የነበረ አንድ ትንሽ የዶሜኒኮ ሽራይንን ሀውልት ለመጨረስ ነበር። ይህም ቅርጽ የተሰራው ለዶሜኒኮ ማስታወሻ በሆነው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። በ1494 መጨረሻ ግድም በፍሎሬንስ የፖለቲካው ሁኔታ ተረጋጋ ። ቀደም ሲል ከተማዋ በፈረንሳይ ትወረራለች የሚል ፍርሀት ነግሶ ነበር። ነገር ግን ቻርልስ ፰ኛው ሽንፈት ስለገጠመው ፍርሀቱ ተወግዶ ነበር። ማይክል አንጄሎ ወደ ፍሎሬንስ ተመለስ። ነገር ግን ከአዲሱ ሳናቫሮላ መንግስት ምንም አይነት ስራ አላገኘም። ከዚያም ወደ ሚዲቺ በመሄድ ስራ ከዚያ ጀመረ። .[16]

ፍሎሬንስ ባሳለፈው ግማሽ አመት ውስጥ ሁለት ትንንሽ ቅርጾችን ቀርጿል የመጀመሪያው መጥምቁ ዮሀንስ በልጅነቱ እና ሁለተኛው ደግሞ ኩፒድ የተኛው የፍቅር አምላክ የሚባሉ ነበሩ። ኮንዲቪ እንደሚለው ለሎሬንዞ ዲ ፒዬሬ ዲ ሜዲቺ ነበር መጥምቁ ዮሀንስን የቀረጸው። ነገር ግን ሌላኛውን «ተቀብሮ እንደተገኘ አሮጌ አስመስለው» ጥሩ ዋጋ እንዲያወጣልን በማለት ይነግረዋል። ከዚያም እንደተባለው ያደርግርጋል ። ከዚያም ቅርጹ እንደ አሮጌ ተደርጎ በሶስተኛ ሰው አማካኝነት ወደ ሮማ በመላክ ከዚያ ገዢ ተገኝቶ ይሸጣል። ሁለቱም ሎሬንዞ እና ማይክል አንጄሎ ክፉኛ ከተታለሉ በኋላ ራፋኤል ሪያሪዮ ቅርጹን ከሎሬንዞ የገዛው ሰው እንደተባለው አሮጌ እንዳልሆነ አወቀ። ነገር ግን በቅርጹ ጥራት እና ውበት በመማረኩ ቀራጩን ወደ ሮማ እንዲመጣ ጋበዘው። [17] [d] ይህ ያልታሰበና የተቃና እድል ቅርጹን ከወግ አጥባቂዎች ፍሎሬንታውያን ውጭ ገዢ እና ተቀባይ ማግኘቱ ማይክል አንጄሎን ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ሮማ ለመሄድ አበቃው ።

የማይክል አንጄሎ ፒየታ (ሐዘን)፤ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤቴ ማርያምስቅለት በኋላ ታቅፋው ሐዘኗን ለመግለጽ የተቀረጸ ሐውልት በ1499፣ ማይክል አንጄሎ ይህን ሐውልት ሰርቶ ሲጨርስ እድሜው 24 አመት ነበር።

ማይክል አንጄሎ ሮማ በ25 ጁን 1496[18] ገባ እድሜውም 21 ነበር። በ 4 ጁላይ በዚያው አመት ከራፋኤል ሪያሪዮ ጋር በመዋዋል ስራ ጀመረ ። ስራውም ሮማውያን ባከስ የወይን አምላክ ብለው የሚጠሩት ነበር ። ነገር ግን ሀውልቱ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ካርዲናሉ ስላልወደዱት በወቅቱ የባንክ ሰራተኛ የነበረ ጃኮፖ የሚባል ሰው ለግቢው አታክልት ማጌጫ ገዛው ። በኖቬምበር 1497 የፈረንሳይ አምባሳደር ጋር አንድ ውል ተዋዋለ ይህም ውል እጅግ በጣም ውብ እና ድንቅ የሆነው ፒየታ (ሐዘን) የሚባለው ነበር ። ውሉ የተፈረመው በኦገስት ወር በሚቀጥለው አመት ነበር ። በወቅቱ የተሰጠውም አስተያየት በእውነቱ ይህ ተአምር ነው ምንም ቅርጽ ከሌለው እምነ በረድ ድንጋይ ይህን የመሰለ ቅርጽ መውጣቱ ፤ ተፈጥሮ እንኳን እንዲህ ያለውን መስራት አይቻላትም የሚል ነበር ። ማይክል አንጄሎ በሮም ውስጥ ሳንታ ማርያ ዲ ሎሬቶ አካባቢ ይኖር ነበር። እዚህም በሚኖርበት አካባቢ ቪቶሪያ ኮሎና ማርኩዚዬ ፔስካራ እና ገጣሚ ሴት ጋር ፍቅር ይዞት እንደነበር ይነገራል ። ይኖርበት የነበረው ቤት በ1874 ተደምስሷል ቀሪው አንዳንድ ተርፈው የነበሩ እና በአዲሱ ባለቤት ተቀምጠው የነበሩ እቃዎችም እንደገና በ1930 የመደምሰስ እጣ ገጥሟቸዋል። ዛሬ አዲስ የተሰራ የማይክል አንጄሎ ቤት የሚባል በጃኒኮሎ ኮረብታማ ቦታ ላይ ይገኛል ። በዚሁ ዘመን ነበር ማይክል አንጄሎ ላኩን እና ልጆቹ የሚባለውን ሀውልት ቀርጾ የጨረሰው ዛሬ ቅርጹ በቫቲካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሮም ይገኛል[19]


የዳዊት ሐውልት በማይክል አንጄሎ በ1504 ተፈጸመ እንደገና መወለድ ካፈራቻቸው አንዱ ብርቅ እና ድንቅ ስራ

የዳዊት ሐውልት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማይክል አንጄሎ ወደ ፍሎሬንስ ተመለሰ ከ1499–1501 ነገሮች በሪፐብሊክ አስተዳደሩ በኩል በጣም ተቀያይረዋል። በተለይም ጸረ እንደገና መወለድ ተቃዋሚ የነበረው ቄስ እና የፍሎሬንስ አስተዳዳሪ የነበረው ጂሮላሞ ሳቮናሮላ ( በ1498 ከተገደለ በኋላ ) እና የጎንፋላኖሪ ፒየር ሶዴሪኒ ከተነሳ በኋላ ። በወቅቱ አስተዳዳሪ የነበረው ጊልድ ዉል አንድ ጥያቄ ለማይክል አንጄሎ አቀረበለት ጥያቄውም አንድ ከአርባ አመት በፊት በአጎስቲኖ ዲ ዱቺዮ ተጀምሮ ያላለቀ ቅርጽ ነበር ። ቅርጹም እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ለፍሮንቴናውያን የነጻነት ምልክት የነበረው ጎሊያድን በወንጭፍ መትቶ የገደለውን የዳዊት ሐውልት ነበር ። ቅርጹም ሊቀመጥ የነበረው ፒያዛ ዴላ ሲኞሪያ ሲሆን ይህ ቦታ የሚገኘው ከፓሎዞ ቪኪዮ ፊት ለፊት ነው ። ማይክል አንጄሎም የቀረበለትን ጥያቄ በሚገባ ሁኔታ ከተቀበለ በኋላ የዳዊትን ሀውልት ቅርጽ ከስራዎቹ ሁሉ በጣም ከሚወደዱት አንዱ የሆነውን ጨርሶ በ1504 አስረከበ ። ይህ አስደናቂ ቅርጽ ከአንድ ወጥ እምነበረድ ከካራራ ካብ ከወጣ እምነበረድ የተሰራ ሲሆን ቀደም ሲል በሌላ ሀውልት ቀራጭ ተጀምሮ ያልተጨረሰ ሲሆን ማይክል አንጄሎ ምን ያህል ከፍተኛ ችሎታ እና አስተሳሰብ እንዳለው ያስመሰከረበት ሐውልት ነው ። በዚሁ ዘመን ማይክል አንጄሎ የቅዱሳን ቤተሰብ እና ቅዱስ ዮሀንስ በሌላ ስሙ ዶኒ ቶንዶ ወይም ቅዱስ ቤተሰብ የሚባለውን ስእል ሰርቶ ጨርሷል ። ይህ ስእል የተሰራው ለአንጄሎ ዶኒ እና ማዳሌና ስቱሮዚ ጋብቻ ስጦታ ነው በ17ኛው ክፍለ ዘመንም ትሪቡን ኡፉዚ በሚባል ክፍል ውስጥ ተስቅሎ ይታይ ነበር ። ምናልባትም እመቤተ ማርያም እና ልጇንምመጥምቁ ዮሀንስ ጋር በሌላ ስሙ የማንቼስተር እመቤቴ ማርያም የሚባለውንም ስእል በዚሁ ዘመን ሰርቶ ጨርሷል ። ይህ ስእል በአሁኑ ጊዜ በለንደን ከተማ ብሄራው ጋሌሪ ሙዚየም ውስጥ ይገኛል።

የሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን ጣራ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ማይክል አንጄሎ በሲስቲኒን ቤተክርስቲያን ጣራ ላይ ዘፍጥረትን ሰራ ስራውን ለመጨረስ አራት አመት ፈጅቶበታል (1508–1512)

በ1505 ማይክል አንጄሎ በአዲሱ ጳጳጽ ጁሊዬስ 2ኛው ጋባዥነት ወደ ሮም ተመለሰ ። ከዚያም አንድ ውል ተዋዋለ ውሉም ለጳጳጹ መቀበሪያ ለማሰናዳት ነበር ። ክፍያውም በቀጥታ ከፓፓጹ ነበር ። ማይክል አንጄሎ ይህን ስራ ብዙ ጊዜ እያቋረጠ ሌሎች ስራዎችን ያከናውን ነበር ። በዚህም የተነሳ ማይክል አንጄሎ በዚህ የመቃብር ስራ ላይ 40 አመት ፈጅቷል ። በመቃብሩ መካከል የሚገኘው የሙሴ ሀውልት ማይክል አንጄሎ እንደፈለገው አልተፈጸመም ። ዛሬ ይህ የሙሴ ሀውልትቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያንቪንኮሊ ሮማ ቫቲካን ውስጥ ይገኛል ። በዚያው ዘመን ሌላ ውል ተዋዋለ ውሉም በሲስቲኒ ቤተክርስቲያን ጣራ ላይ ስእል ለመስራት ነበር ። ይህን ስእል ስርቶ ለመጨረስ አራት አመት ፈጅቶበታል (ከ1508 እስከ 1512 ) ማይክል አንጄሎ እንዳለው ብራማንቴ እና ራፋኤል ጳጳጹን አሳምነው ማይክል አንጄሎ ብዙ በማይወደው እና ብዙ ልምድ በሌለው የጄሶ ላይ ስእል ስራ ውል እንዲዋዋል አደረጉት ። ይህንንም ያደረጉት በወቅት በዚያን ዘመን ራፋኤል በጄሶ የስእል ስራ ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ ስለነበር በማይክል አንጄሎ ስቃይ እና ውድቀት ራሳቸውን ትልቅ አድርገው ለማሳየት ነበር ። ነገር ግን ይህን ታሪክ ዘመናዊ የታሪክ ተመራማሪዎች ይህን የሚያሳይ መረጃ ባለማግኘታቸው ታሪኩን አይቀበሉትም ። እንዲያውም ይህ የማይክል አንጄሎ አመለካከት ሊሆን ይችላል ይላሉ ። ማይክል አንጄሎ በመጀመሪያ የተዋዋለው የ12 ቱን ደቀ መዝሙሮች ስእል ለመስራት ነበር ። ነገር ግን ማይክል አንጄሎ በጣም የረቀቀ እና የተወሳሰበ ስእል እንዲሰራ አበክሮ ተከራከረ ለምሳሌ ዘፍጥረትን ያካተተ እንዲሁም የሰውን ልጅ ውድቀት እና በፈጣሪው የተገባለትን ቃል ኪዳን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ነጻ አውጣሀለሁ የሚለውን የኢየሱስ ታሪክ እና እንዲሁም ስለ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት በስፊው እንዲያካትት ነበር ። ስእሉ በአጠቃላይ 300 ሰዎችን ያካተተ ሲሆን መሀሉም ዘጠኝ ክፍሎች አሉት ዘፍጥረትን ያካተቱ በሶስት ምድብ የተከፈሉ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ሲፈጥር ፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥር እና የግዚአብሐርን ቃል እንዴት መጠበቅ እንዳቃታቸው እና አህዛብን የሚወክለው ኖሕ እና ቤተስቡ ናቸው። የቤተክርስቲያኑን ጣራ መጋጠሚያዎች ላይ ደግሞ አስራ ሁለት ወንድ እና ሴት ነቢዮች የጌታችን የመዲሀኒታችን ኢየሱስ መምጣት ሲስብኩ ተስሏል ። ከእነዚህም ሰባት የእስራኤል ነቢያት ሲሆኑ አምስቱ ሴቶች ደግሞ ከሌላው አለም የተወከሉ ነበሩ ። በጣም ከሚወደዱት እና ከሚደነቁት እነዚህ ስእሎች መሀከል የአዳም አፈጣጠር እና ፡ አዳም እና ሔዋንገነት የአትክልት ስፍራ ውስጥ የጥፋት ውሀ ፡ ነቢዮ ኢሳይያስ እና የሲቢል ነቢያት እና እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ ዘረ ሐረግ ናቸው ።

ፍሎሬንስ በሚዲቺ ፓፓጽ ስር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የማይክል አንጄሎ ሙሴራሔል እና ሊህያ መካከል


በ 1513 ጳጳጽ ጁሊየስ 2ኛው ሞቱ ። እሳቸውን የተካው ጳጳጽ ሌዮ ኤክስ ይባላል ። ማይክል አንጄሎ ክሜዲቺ ጋር አንድ ውል ተዋዋለ ውሉም በፍሎሬንስ የሚገኘውን የባሴሊካን ሳን ሎሬንዞ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊቱን አፍርሶ የተለያዩ ቅርጾች እና ሐውልቶች ጨምሮ በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ነበር ። ማይክል አንጄሎም በሀሳቡ ወዲያውኑ ተስማማ ። ከዚያም ለሶስት አመታት ለስራው የሚያስፈልገውን የስእል ንድፍ እና ለሐውልቶቹም የሚያስፈልገውን ንድፍ እና እቅድ አውጥቶ በአካባቢውም ለሐውልቶቹ ቅርጾች የሚያስፈልግውን የእምነ በረድ ካብ በፒዬትርራሳንታ ቁፋሮ ማካሄድ ካስጀመረ በኋላ በገንዘብ እጦት ምክንያት ስራው ተቋረጠ ። ማይክል አንጄሎ በህይወት ዘመኑ በጣም የተማረረበት የስራ ውል ነበር። ቤተ ክርስቲያኑም ምንም ለውጥ ሳይደረግለት እስከ ዛሬ ድረስ አለ ። ሜዲችም ቀደም ብለው በሰረዙት የስራ ውል ሳያፍሩ ማይክል አንጄሎን ሌላ ስራ እንዲሰራላቸው ጠየቁት ። በዚህ ጊዜ ደግሞ ለቤተሰባቸው የሚሆን የመቃብር ቤት በባሴሊካ ሳን ሎሬንዞ እንዲሰራላቸው። ይህ ስራ ከ 1520 እስከ 1530 ማይክል አንጄሎ ብዙ ጊዜ ሰርቶበታል ነገር ግን ስራው እስከ አሁን አልተፈጸመም ። ነገር ግን ማይክል አንጄሎ ምን ያህል ሐውልትን የመቅረጽ እና የምህንድስና ችሎታ እንዳለው የሚያሳይ ትልቅ ማስረጃ ነው ። ማይክል አንጄሎ ሐውልቶቹን እና የህንጻውን የውስጥ ፕላን በማውጣት ምን ያህል ከፍተኛ እና ድንቅ የሆነ ችሎታ እንዳለው አስመስክሯል ። እንደዘበት ብዙ ያስገረመው መቃብር የሁለቱ የማይታዩ ሜዲቺ በወጣትነታቸው የሞቱ የሎሬንዞ ll ማግኒፊኮ ልጅ እና የልጅ ልጅ እና እራሱ ሎሬንዞ ማግኒፊኮ የተቀበሩበት ያልተጨረሰ እና ብዙ የማያምር ባንድ ጎኑ በኩል ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር የሚዋሰን ነው ። በመጀመሪያ እንደታቀደው እመሬት ላይ የቆመ ቅርጽ የለውም ።

የማይክል አንጄሎ የፍርድ ቀን . ቅዱስ ባርቶሎሜ ከ12ቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር አንዱ የነበረ ቆዳው እንደ እንሰሳ ተገፍፎ ተዘቅዝቆ በስቅላት የተገደለ የተገፈፈበትን ቢላዋ እና ቆዳውን ይዞ በቆዳው ላይ ያለው ፊት የማይክል አንጄሎ ነው።

በ 1527 የፍሎሬንስ ዜጎች በሮም አስተዳደር በመደገፍ ሜዲቺን ከስልጣን አስወግደው ሪፐብሊካን ስልጣን ላይ ወጡ። ከተማውን በመክበብ የትርምስ ጊዜ ሆነ ። ማይክል አንጄሎም የሚወዳትን ፍሎሬንስ በመርዳት ከ1528 እስከ 1529 በወታዳራዊ ተቋሞች ውስጥ በመስራት አገልግሏል ። በ 1530 የከተማዋ በሜዲቺ አስተዳደር ውስጥ ወደቀ ። ሜዲቺም ስልጣን ላይ ወጡ በሙሉ ስምምነት ከጨካኝ እና ጨቋኝ ከሆነው ዱካል ሜዲቺ ጋር ። ማይክል አንጄሎ ፍሎሬንስን በ 1530 ለቆ ወጣ ። የሜዲቺንም ቤተ ክርስቲያን እንዲጨርስ ስራውን ለሌላ ስው ስጥቶ ። ከአመታት በኋላም የማይክል አንጄሎ አስከሬን ከሮም ወደ ባሴሊካ ዲ ሳንታ ክሮሼ ለቀብር መቶ ነበር። ነገር ግን በማይክል አንጄሎ ኑዛዜ መሰረት እጅግ በጣም በሚወዳት ቱስካኒ የመጨረሻ ማረፊያው ሆነ

የመጨረሻ ስራው በሮማ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጄሶ ላይ የፍርድ ቀን የተባለው የግርግዳ ላይ ስእሉ የተሰራው በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን ከመንበሩ በስተ ጀርባ በኩል ነው። ይህ ውል የተፈጸመው ከጳጳጽ ክሌሜንቴ 8ኛው ጋር ነበር። ነገር ግን ጳጳጹ ውሉን በተዋዋሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ፓውሎስ 3ኛው የዚህ ስራ ተቆጣጣሪ ነበሩ ማይክል አንጄሎም ስራውን ጀምሮ እስኪፈጽም ድረስ። ማይክል አንጄሎ በዚህ ስራ ላይ ከ 1534 እስከ 1541 ለሰባት አመት ሰርቷል። ስራው በጣም ግዙፍ እና ከመንበሩ በስተጀርባ ያለውን ገድግዳ ሙሉ በሙሉ ከጭፍ እስከ ጫፍ ያካተተ ነበር። የመጨረሻው የፍርድ ቀን የሚባለው ስእል የጌታችን የመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደ ምድር ከጻድቃን ጋር ለፍርድ ቀን እንዴት እንደሚመጣ ለማሳየት የተሰራ ስእል ነው። ስእሉ ተስርቶ እንዳለቀ የብዙዎቹ ስእሎች ራቁታቸውን መሆን ጳጳጹ በሚጸልዩበት ቤተ ክርስቲያን በጣም ነውር እና አሳፋሪ ከምንሰራው ስራ ጋር የማይሄድ ነው በማለት ጳጳጽ ካራፋ እና ሞንሲኞር ሴሪኒኒ (የማንቱአ አምባሳደር) ስእሉ እንዲጠፋ ወይም ሀፍረተ ስጋቸው እንዲሸፈን ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ ተቃወሙ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩት ፓፓጽ ስእሉ አይጠፋም ወይም አይቀየርም ሲሉ ክፉኛ ተከራከሩ።

ማይክል አንጄሎ የቅዱስ ጴትሮስን ቤተ ክርስቲያን አናት ግማሽ ክብ ንድፍ አውጥቶ ስራው ተጀመረ ስራው ከመፈጸሙ በፊት ማይክል አንጄሎ አረፈ (ሞተ)በ 18 ፌብሩዋሪ 1564)

ማይክል አንጄሎ ከሞተ በኋላ ግን ሀፍረተ ስጋቸውን ለመሸፈን ተስማሙ። ከዚያም የማይክል አንጄሎ ተማሪ ከነበረው ዳኒኤሌ ዳ ቮልቴራ ጋር ውል በመዋዋል ሀፍረተ ስጋቸውን በጨርቅ መሸፈን ተያያዙት። በ 1993 ስእሎቹ እድሳት ሲደረግላችው ወግ አጥባቂዎች በጣም በመከራከር ቀደም ሲል ዳኒኤሌ ሸፍኗቸው የነበሩትን ስእሎች ቀድሞ ማይክል አንጄሎ እንደሰራቸው ማስመለስ ችለዋል። አንዳንዶቹንም ለታሪክ በማለት ጨርቅ እንደለበሱ ትተዋቸዋል። የማይክል አንጄሎ ስራዎች አሳፋሪ በሚል በሌላ ሰአሊ በመበላሸታቸው ዋናውን የማይክል አንጄሎ ዋና ስራ በማንም ያልተነካውን በማርቼሎ ቬኑስቲ የተሰራውን በካፖዲሞንቴ ሙዚየም ውስጥ ኔፕልስ ማየት ይቻላል። ሳንሱር ሁልጊዜ ማይክል አንጄሎን ይከታተለው ነበር ይባላል። ማይክል አንጄሎ በአንድ ወቅት የሚያሳፍር ስራ ፈጣሪ የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር። ብዙ የማይወደደው የአሳማ ነገር በመባል የሚታወቀው የጸረ እንደገና መወለድ እንቅስቃሴ በዘመኑ የነበሩትን ቅርጽ እና ስእሎች በሙሉ ሀፍረተ ስጋ መሸፈን የተጀመረው በማይክል አንጄሎ ስራዎች ነው። ማስረጃ ለመስጠት ያህል የክርስቶስ ዴላ ሚንሬቫ ቤተክርስቲያን ሳንታ ማሪያ ሶፕራ ሚንሬቫ ሮም በጨርቅ እንዲሸፈኑ ተደርጓል እስከ ዛሬ ድረስ። ሌላው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐውልት በልጅነቱ እራቁቱን የብሩጌስ ማዶና ። በቤልጂየም የሚገኘው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመን ሀውልቱ በጨርቅ ተሸፍኖ ይኖር ነበር። በለንደን በካስት ኮርትስ (ቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም ) ውስጥ የዳዊት ሀውልት ቅጂ ከበስተጀርባው ቅጠል በሳጥን ውስጥ ተደርጎ ይኖራል ምክንያቱም የንጉሱ ቤተሰቦች ሊያዩት ከመጡ እራቁቱን እንዳያዩት ለመሸፈን ተብሎ ነው። በ1546 ማይክል አንጄሎ የቅዱስ ፔጥሮስ ቤተክርስቲያን መሀንዲስ ሆኖ ተቀጠረ ። ከዚያም የቤተ ክርስቲያኑን አናት ግማሽ ክብ ንድፍ አውጥቶ ስራው ተጀመረ በዚያን ጊዜም ከፍተኛ ስጋት ነበር። ስጋቱም ስራው ከመጠናቀቁ በፊት ማይክል አንጄሎ ይሞታል የሚል ፍርሀት ነበር። ነገር ግን ግማሽ ስራው እንደተገባደደ ስራውን እንደሚፈጽሙት አረጋገጡ።

የመጨረሻው ንድፍ መገኘት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዲሴምበር 7 2007 የማይክል አንጄሎ በቀይ ቾክ የተሰራ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሴሊካ ንድፍ ተገኘ። በ 1564 ከመሞቱ በፊት። የተገኘውም በቫቲካን ግምጃ ቤት ውስጥ ነው። በጣም የሚያስገርም ነገር ነበር። ማይክል አንጄሎ ጥሩ ያልሆኑ የሚላቸውን ስራዎቹን በሙሉ በእሳት አቃጥሏቸዋል። የተገኘው ንድፍ ከቋሚዎቹ የአንዱ ሲሆን የቅዱስ ጴጥሮ ኩፖላ ድረም በመባል ይታወቃል። [20]

የሕንጻ ስራዎቹ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማይክል አንጄሎ በሌሎች ሰዎች ተጀምረው ባላለቁ በብዙ ስራዎች ላይ ተሳትፏል። በጉልህ ከሚታዩት ለምሳሌ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሴሊካ እና ካምፒዶጊሊዮ ፕላናቸውን ያወጣው ማይክል አንጄሎ ነው። የሮማን ካፒቶል ሂልም ንድፍ ያወጣው ማይክል አንጄሎ ነበር። ቅርጹም ሮምቦይድ ነበር ከአራት ማእዘን ይልቅ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት በቦታው ጥበት የተነሳ የተመልካቹን አይን ለማታለል ነው። ሌላው የህንጻ ስራዎቹ በፍሎሬንስ ሳን ሎሬንዞ እና የሎውሬንቲን ቤተ መጻህፍት እና ለውትድርና የሚያገለግሉ ምሽጎች እና ማማዎች ናቸው። በሮም ከሰራቸው ደግሞ የቅዱስ ጴትሮስ ቤተ ክርስቲያንፓላዞ ፋርኔሴሳን ጆቫኒ ዴዪ ፊዮሬንቴኒ ፤ ዘ ስፎዛ ቤተክርስቲያን (ካፔላ ስፎርዛ) በ ባሴሊካ ዲ ሳንታ ማሪያ ማጆሬፖርታ ፒያ እና ሳንታ ማሪያ ዴጂሊ አንጄሊ ናቸው።

የማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ መቃብር ፡ በ ስንታ ክሮሼ ዲ ፌሬንዜ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፍሎረንስ

የላውሬንቲን ቤተ መጻህፍት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ 1530 ማይክል አንጄሎ የላውሬንቲን መጽህፍት ቤት በፍሎሬንስ ንድፍ አወጣ። መጻህፍት ቤቱ ከሴንት ሎሬንዞ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተያያዘ ነው። በዚህ ስራው ላይ ፒላስተርስ የሚባል አዲስ ዘዴዎችን በመጠቀም። ሌላው ከስር ከስተው ወደ ላይ እየወፈሩ የሚሄዱ ዘዴዎችን በመጠቀም ። ደረጃዎችን ደግሞ አራት ማእዘን እና ግማሽ ክብ አድርጎ በመፍጠር ነበር።

የሜዲቺ ቤተ ክርስቲያን

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማይክል አንጄሎ የሜዲቺን ቤተክርስቲያን ንድፍ አወጣ። በሜዲቺ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተለያዩ ሐውልቶች አሉ ለተለያዩ የሜዲቺ ቤተሰቦች የተሰሩ። ማይክል አንጄሎ ስራውን በሙሉ አልጨረሰውም። የሱ ሰራተኞች የነበሩ በኋላ ጨርሰውታል። ሎሬንዞ ዘ ማግንፊሰንት የተቀበረው ከመግቢያው ፊት ለፊት ነው። የእመቤቴ ማርያም እና ልጇ እንዲሁም የሜዲቺ አለቃ የሆኑት የቅዱስ ኮስማስ እና ዳሚያን ከመቃብሩ በላይ በሐውልት ተቀርጸዋል። የእመቤቴ ማርያም እና ልጇ ሐውልትም የተቀረጸው በማይክል አንጄሎ ነው።

ማይክል አንጄሎ ብዙ ጊዜ እብሪት ለሌሎች ያሳይ ነበር እና በራሱም ብዙ አይደሰትም ነበር። ኪነ ጥበብ ከባህል እና ከውስጥ የሚመነጭ ስሜት እንደሆን ይናገር ነበር። በወቅቱ ተፎካካሪው ከነበረው ከሌዎናርዶ ዳቬንቺ በተቃራኒው። ማይክል አንጄሎ ተፈጥሮን እንደ ጠላት ነበር የሚያየው ስለዚህም መሸነፍ አለበት ይል ነበር። የሚሰራቸው ስራዎች በሙሉ እያንዳንዳቸው በየራሳቸው መንገድ አስደናቂ እና አስገራሚ ነበሩ በዘመኑ ከሚታዩት ሐውልቶች ። ማይክል አንጄሎ የሐውልት ቀራጭ ስራ የሚፈለገውን ቅርጽ ከ እምነበረዱ ውስጥ ማላቀቅ ነው ይል ነበር። ማይክል አንጄሎ እያንዳንዱ እምነበረድ በውስጡ ቅርጽ አለ ብሎ ይል ነበር የቀራጭም ስራ የማያስፈልገውን ቅርጹን የሸፈነውን እና የቅርጹ አካል ያልሆነውን እምነበረድ ከላዩ ላይ በመዶሻ እና በመሮ መቅረፍ ወይም ማለያየት ነው ይል ነበር። በወቅቱ ይነገር ከነበረው አፈ ታሪክ የማይክል አንጄሎ ችሎታ በተለይም ሐውልት በመቅረጽ ላይ በወቅቱ በጣም የተወደደ ነበር። ሎሬንዞ ደ ሚዲቺ በማይክል አንጄሎ ትንሽ ገንዘብ ሊሰራ ፈለገ።

የሊብያን ሲይብል በኒው ዮርክ ከተማ በሜትሮፖሊታን የኪነ ጥበብ ሙዚየም

ማይክል አንጄሎንም የፍቅር አምላክ የሚባለውን ሐውልት እንዲሰራ እና አሮጌ እንዲያስመስለው ጠየቀው። ሎሬንዞ ለማይክል አንጄሎ ለፍቅር አምላክ ለሚባለው ቅርጽ 30 ዱካት ከፈለው። ነገር ግን ሎሬንዞ ቅርጹን አሮጌ ቅርጽ ለሚሸጡ ሰዎች በ 200 ዱካት ሸጠው። ቅርጹን የገዛው ካርዲናል ራፋኤል ሪያሪዮ ቅርጹ አሮጌ መሆኑን በጣም ስለተጠራጠረ የቅርጹን ታሪክ የሚያጠናለት ሰው ቀጠረ። ሰውየውም ማይክል አንጄሎን ካገኘው በኋላ የፍቅር አምላክ የሚባልውን ሐውልት በወረቀት ላይ ንድፉን እንዲሰራ እና እንዲያሳየው ጠየቀው ማይክል አንጄሎም ስርቶ አሳየው። በዚህን ጊዜ ሰውየው ከአንተ የፍቅር አምላክ የሚባለውን ቅርጽ በ 30 ዱካትስ ገዝቶ በ200 ዱካትስ እንደሸጠው ነገረው። ማይክል አንጄሎም ቅርጹን እሱ እንደቀረጸው ተናዘዘ ነገር ግን ይህን ያህል መታለሉን አላወቀም ነበር። እውነቱ ከወጣ በኋላ ካርዲናሉ ቅርጹን የገዛው ማይክል አንጄሎ በእርግጥም ልዩ ችሎታ እንዳለው ካረገገጠ በኋላ ባከስ ወይም የወይን አምላክ የሚባለውን እንዲሰራለት ውል ተዋዋሉ። ሌላው ሰለ ማይክል አንጄሎ የሚነገረው ታሪክ ሙሴ የሚባለውን ሐውልት ሰርቶ ሲጨርስ ይቀርጽበት በነበረው መዶሻ የሙሴን ሀውልት ጉልበቱን በመዶሻው በመምታት “ለምን አታናግረኝም” ብሎ እንደመታው ይነገራል። በግል ህይወቱ ማይክል አንጄሎ በጣም ቁጥብ ነበር ። ተማሪው ለነበረው"አስካኒዮ ኮንዲቪ “ምንም ሀብታም ብሆን የኖርኩት ግን እንደ አንድ ድሀ ነው ብሎት ነበር።[21 ] ኮንዲቪ እንዳለው ለምግብ እና ለመጠጥ ብዙም ግድ አልነበረውም። የሚበላው ሲርበው ብቻ እንጂ በምግብ ለመደስት ብሎ በልቶ አያውቅም። [21] ወደ አልጋውም ሲሄድ እስከ ልብሱ እና ጫማው ይተኛ ነበር።[21] ይህ ጸባዩ በብዙዎች ዘንድ የተወደደ አልነበረም። ይህ ጸባዩ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ እንዳይሆን አድርጎታል። ታሪኩን የጻፈው ፓኦሎ ጂኦቪዮ እንዳለው “ተፈጥሮው በጣም አስቸጋሪ እና ግልጽ ያልሆነ ነው። የቤት ውስጥ አያያዙም ባህሪውም ቆሻሻ ነበር። በዚህም የተነሳ ብዙ ተከታይ አልነበረውም ይላል። [22] ማይክል አንጄሎ ግን ግድ አልነበረውም። በተፈጥሮው ከሰው ጋር ብዙ መገናኘት ስለማይወድ። ብዙዎችም ጉደኛው እና አስገራሚው ይሉት ነበር። ማይክል አንጄሎ እራሱን ከሰዎች አግልሎ ነበር ህይወቱን የኖረው። [23]

የማይክል አንጄሎ መሰረታዊ የኪነ ጥበብ ስራ መስረት ያደረገው የወንድን ጡንቻማ አካል በ መውደድ ላይ ነው። ወደዚህም የተሳበው ተፈጥሮን በጣም ስለሚወድ እና ስሜታዊ ስለነበር ነው። በከፊል የእንደገና መወለድ አገላለጽ እና አምልኮ ነበር። የማይክል አንጄሎም የስራ ውጤቶች ተፈጥሮን መውደዱን በግልጽ የሚያንጸባርቁ ነበሩ [24] የሚቀርጻቸውም ቅርጾች ፍቅርን እና ተፈጥሮን የሚገልጹት በኒዮፕላቶኒያን እና በእርቃነ ስጋ ላይ ያተኮረ ነበር። ለምሳሌ ቺቺኖ ዴዪ ብራቺ በተዋወቁ በአመቱ በ 1543 ከዚህ አለም በመለየቱ አርባ ስምንት የሀዘን እንጉርጉሮ ግጥም ጽፎለታል። አንዳንድ ሰዎች ይህን በመመልከት ግንኙነታቸው ከጓደኝነት በላይ ነበር ይላሉ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ የፕላቶኒያን ፍቅር መግለጫ መንገድ ነበር ይሉታል። በወቅቱ ሀፍረት የሌለበት ግጥም ለሚወዱት ሰው መግጠም እውነተኛ የፍቅር መግለጫ ነበር ይላሉ።

የሊብያን ሲይብል , በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን

በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የሞያ ፍቅር ከዛሬው የሞያ ፍቅር በጣም የበለጠ ነበር። [26] በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ወሮ በላዎችም ይህንን አጋጣሚ ገንዘብ ለማግኛ ተጠቅመውበታል። ፌቦ ዲ ፖጂዮ በ 1532 ማይክል አንጄሎ የጻፈለትን የፍቅር ደብዳቤ ይዞ ይዞር ነበር። ቀደም ሲል ጌራርዶ ፔሪኒ በ 1522 ያለ ሀፍረት ዘርፎታል። ማይክል አንጄሎ ራሱን ከሰው ያገል ነበር። አንድ የጓደኛው ሰራተኛ የነበረ ኒኮላ ኳራቴሲ የሚባል ሰው ልጁን ከማይክል አንጄሎ ጋር ተማሪ ሆኖ እንዲሰራ ሲጠይቀው አልጋም ላይ ጥሩ ነው ብሎት ነበር። ማይክል አንጄሎ ግን ወዲያውኑ ግብረ ሰዶም ለእሳት ይዳርጋል ብሎ መልስ ሰጥቶታል። ከፍተኛው የፍቅር ደብዳቤ ተጽፎ የተገኘው ለቶማሶ ዴዪ ካቫሌሪ ነው ( 1509–1587) በወቅቱ እድሜው 23 አመት ሲሆነው ነው ከማይክል አንጄሎ ጋር የተገናኙት በ1532 ማይክል አንጄሎ 57 አመቱ ነበር ። ካቫሌሪ በእድሜ ከገፉ ሰዎች ጋር ይውል ነበር። ፍቅራችሁን እመልሳለሁ እያለም ይምል ነበር። እንዳንተ የወደድኩት ሰው የለም እያለም ይናገር ነበር። ጓደኝነትህንም ከማንም በላይ እፈልገዋለሁ እያለም ይናገር ነበር። ካቫሌሪም ማይክል አንጄሎ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ጓደኝነታቸው የጸና ነበር። ማይክል አንጄሎም ከሶስት መቶ በላይ ግጥሞች እና እንጉርጉሮ ጽፎለታል። አንዳንዶች እንደሚሉት ግን ይህ ፍጹም ንጹህ የሆነ ወንድማዊ የፕላቶኒያን ፍቅር መግለጫ ነው ይላሉ። እንዲያውም ማይክል አንጄሎ ካቫሌሪ ልጅ ቢኖረው ወስዶ ለማሳደግ ይፈልግ ነበር።[27] ነገር ግን በወቅቱ ፍቅራቸው በግልጽ የሚታይ ነበር። ማይክል አንጄሎ ለግጥም እና ለቪቶሪያ ኮሎና ለምትባል ሴት ከፍተኛ ፍቅር ነበረው። የተገናኙት ሮም ውስጥ በ 1536 ወይም በ 1538 ነበር። ሲገናኙም ቪቶሪያ በ አርባዎቹ አመታት ውስጥ ነበረች። እስከሞተችበት ጊዜም ድረስ ግጥም ይጻጻፉ ነበር። ግንኙነታቸው ምን እንደነበር ለመገመት አስቸጋሪ ነበር። ኮንዲቪ ግን የመነኩሴ ንጹህ ፍቅር ነው ይል ነበር። [28] ነገር ግን በግጥሞቹ እና በሰራቸው ስራዎቹ አስተሳሰቡን መገመት እንችላለን[29]

ኢግኑዶ በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን

ይህን ይመልከቱ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

The asteroid 3001 Michelangelo and a crater on the planet Mercury were named after Michelangelo.[1] The character Michelangelo from Teenage Mutant Ninja Turtles was named after Michelangelo.

The 1965 film The Agony and the Ecstasy features the story of Michelangelo and his travails in painting the Sistine Chapel. He is portrayed in the film by Charlton Heston.

የግርጌ ማስታወሻ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
a. Michelangelo's father marks the date as 6 March 1474 in the Florentine manner ab Incarnatione. However, in the Roman manner, ab Nativitate, it is 1475.
b. Sources disagree as to how old Michelangelo was when he departed for school. De Tolnay writes that it was at ten years old while Sedgwick notes in her translation of Condivi that Michelangelo was seven.
c. The Strozzi family acquired the sculpture Hercules. Filippo Strozzi sold it to Francis I in 1529. In 1594, Henry IV installed it in the Jardin d'Estang at Fontainebleau where it disappeared in 1713 when the Jardin d'Estange was destroyed.
d. Vasari makes no mention of this episode and Paolo Giovio's Life of Michelangelo indicates that Michelangelo tried to pass the statue off as an antique himself.

ማመሳከሪያዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
Notes
  1. ^ Gallant, R., 1986. National Geographic Picture Atlas of Our Universe. National Geographic Society, 2nd edition. ISBN 0-87044-644-4

በበለጠ ለማንበብ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • Ackerman, James (1986). The Architecture of Michelangelo. University of Chicago Press. ISBN 978-0226002408. 
  • Clément, Charles (1892). Michelangelo. Harvard University, Digitized 25 June 2007: S. Low, Marston, Searle, & Rivington, ltd.: London. http://books.google.com/books?id=G-sDAAAAYAAJ&printsec=frontcover&dq=michelangelo&as_brr=1#PPA1,M1. 
  • Condivi, Ascanio; Alice Sedgewick (1553). The Life of Michelangelo. Pennsylvania State University Press. ISBN 0-271-01853-4. 
  • Baldini, Umberto; Liberto Perugi (1982). The Sculpture of Michelangelo. Rizzoli. ISBN 0-8478-0447-x. http://books.google.com/books?id=pCEWAQAAIAAJ. 
  • Einem, Herbert von (1973). Michelangelo. Trans. Ronald Taylor. London: Methuen.
  • Gilbert, Creighton (1994). Michelangelo On and Off the Sistine Ceiling. New York: George Braziller.
  • Hibbard, Howard (1974). Michelangelo. New York: Harper & Row.
  • Hirst, Michael and Jill Dunkerton. (1994) The Young Michelangelo: The Artist in Rome 1496–1501. London: National Gallery Publications.
  • Liebert, Robert (1983). Michelangelo: A Psychoanalytic Study of his Life and Images. New Haven and London: Yale University Press. ISBN 0-300-02793-1. 
  • Pietrangeli, Carlo, et al. (1994). The Sistine Chapel: A Glorious Restoration. New York: Harry N. Abrams
  • Sala, Charles (1996). Michelangelo: Sculptor, Painter, Architect. Editions Pierre Terrail. ISBN 978-2879390697. 
  • Saslow, James M. (1991). The Poetry of Michelangelo: An Annotated Translation. New Haven and London: Yale University Press.
  • Rolland, Romain (2009). Michelangelo. BiblioLife. ISBN 1110003536. 
  • Seymour, Charles, Jr. (1972). Michelangelo: The Sistine Chapel Ceiling. New York: W. W. Norton.
  • Stone, Irving (1987). The Agony and the Ecstasy. Signet. ISBN 0-451-17135-7. 
  • Summers, David (1981). Michelangelo and the Language of Art. Princeton University Press.
  • Tolnay, Charles (1947). The Youth of Michelangelo. Princeton, NJ: Princeton University Press. 
  • Tolnay, Charles de. (1964). The Art and Thought of Michelangelo. 5 vols. New York: Pantheon Books.
  • መለጠፊያ:Citebook
  • Wilde, Johannes (1978). Michelangelo: Six Lectures. Oxford: Clarendon Press.

ወደ ውጭ የሚያገናኙ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]