ኅዳር ፲፬

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ኅዳር ፲፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፬ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፱ነኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፩ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 • ፲፰፻፸፱ ዓ/ም - እቴጌ ጣይቱ ፍልውሃ ፊል-ፊል ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተው ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› ብለው ሠየሙ።
 • ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - በኦጋዴን ክልል በኢትዮጵያ እና በኢጣልያዊ ሶማልያ ያለውን ድንበር እንዲያሠምሩ የተላኩት የብሪታንያ እና የኢትዮጵያ ልዑካን በዚሁ ክልል ውስጥ ለሥራ ይዘጋጁ ነበር። በዚህ ጊዜ ‘ሙስቲ’ በሚባል የኢጣልያ መቶ ዓለቃ የሚታዘዙ ሁለት መቶ ሶማሌያዊ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው፤ ከሺህ በላይ የውሐ ጉድጓዶች የነበሯትን፤ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ያለችውን ወልወልን ከበዋት ተገኙ። በወቅቱ የኦጋዴን ገዥ የነበሩት የፊታውራሪ ሺፈራው ወታደሮችና የኢጣልያን ወገን በሚመራው በሻለቃ ቺማሩታ ወታደሮች ለሁለት ሣምንታት ከተፋጠጡ በኋላ በኢትዮጵያና በፋሽስታዊ ኢጣልያ መካከል ለአምሥት ዓመታት የተከተለው ጦርነት ክብሪት ተጫረ። [1]
 • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቀጥተኛ ትዕዛዝ በአጠቃላይ ፷ (ስድሳ) የቀድሞው የዘውድ ሥርዓት ባለሥልጣናት በአንድ ላይ ያለፍርድ ተገደሉ። እስከዚህ ድርጊት ድረስ ከየካቲት ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ጀምሮ ያለደም ማፍሰስ ሲካሄድ የቆየውና በመስከረም ወር የቀድሞውን የዘውድ ሥርዓት ያለአንዳችም ሽብር ከሥልጣን ያወረደው አብዮት ከዚህ ኢሰብዓዊ አድራጎት በኋላ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ በደም የተጨማለቀ አድርጎታል።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በደርግ እጅ በአንድ ላይ ያለፍርድ ከተገደሉት ፷ ሰዎች መኻል ፦
 • ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ- የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር
 • ልጅ እንዳልካቸው መኮንን- የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር
 • ዓቢይ አበበ (ሌተና ጀኔራል)- የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር
 • አካለወርቅ ሀብተ ወልድ- የቀድሞ የፍርድ ሚኒስትር
 • አስራተ ካሳ (ልዑል ራስ)- የዘውድ ምክር ቤት ሰብሳቢ
 • አበበ ረታ - የዘውድ አማካሪ
 • ታምራት ይገዙ (ኮሎኔል)-የዘውድ አማካሪ
 • መስፍን ስለሺ (ራስ)- የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ
 • ክፍሌ እርገቱ (ደጃዝማች) - አርበኛና አምባሳደር
 • ኢሳያስ ገብረ ሥላሴ (ሌተና ጄኔራል) - የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል) በአጠቃላይ 60 ባለሥልጣናትና
 • እስክንድር ደስታ ኮማንደር - የባሕር ኃይል አዛዥ

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 1. ^ Mockler, Anthony, “Haile Selassie’s War” (2003), p 37-39
 2. ^ http://www.airdisaster.com/special/ethiopian961.shtml
 3. ^ http://www.wto.org/english/thewto_e/countries_e/angola_e.htm