Jump to content

ኢያሪኮ

ከውክፔዲያ
ኢያሪኮ ['Jericho'] በዌስት ባንክ ፍልስጥኤም

ኢያሪኮ (ዕብራይስጥ፦ /ይሪሖ/፣ አረብኛ፦ /ኣሪኃ/) አሁን በፍልስጥኤም ዌስት ባንክ የሚገኝ ከተማ ነው። 20 ሺህ ኗሪዎች አሉበት።

ሥነ ቅርስ ሊቃውንት ዘንድ ኢያሪኮ ከሁሉ አስቀድሞ የተሠፈረው ቦታ ሲሆን በቅደመ-ታሪክ እንደ ተሠራ ይላሉ። ኪታብ አል-ማጃል የተባለው ጽሑፍ እንደሚለው ግን ኢያሪኮ የተሠራው የይስሐቅ ዕድሜ 64 ዓመት ሲሆን (ወይም እንደ የመዛግብት ዋሻ 67 ዓመት ሲሆን) ነበር፣ ከኬብሮንኢየሩሳሌምደማስቆ በኋላ ተሠራ ማለት ነው። በነዚህ ጽሁፎች ዘንድ፣ ፯ የከነዓን ነገሥታት -- እነርሱም የኬጥያውያን፣ የአሞራውያን፣ የኢያቡሳውያን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርጌሳውያን፣ የኤዊያውያንና የፌርዛውያን ነጉሶች -- ኢያሪኮን ሠሩትና በግድግዳ ከበቡት።

መጽሐፈ ኢያሱብሉይ ኪዳን ምዕራፍ ፮ የኢያሪኮ ውግያ ይተረካል።