Jump to content
ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 17
- ፲፰፻፲፭ ዓ/ም -ቺሌ የሰውን ልጅ መሸጥ መለወጥ (ባርነት) ሕገ ወጥ አደረገች።
- ፲፱፻ ዓ/ም - በሶርያዊው ሃቢብ ይድሊቢ በኩል ኢትዮጵያ በገባው ማተሚያ መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ በሕትመት “ጎህ”” የተባለ ጋዜጣ በዚህ ዕለት ታትሞ ወጣ።
- ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - በሊቢያ እና በግብጽ መኻል ለአራት ቀናት የተካሄደው የድንበር ጦርነት በ አልጄሪያው ፕሬዚደንት ሁዋሪ ቡመዲየን ሽምግልና ቆመ።
- ፳፻ ዓ/ም - የአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ባራክ ኦባማ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎች በተሰበሰቡበት የበርሊን መናፈሻ ላይ ንግግር አደረጉ። በዚህ ንግግር ላይ ለ አውሮፓውያን እና አሜሪካኖች በበፊተኛው ትውልድ በአንድነት ኮሙኒዝምን እንዳሸነፉ፤ አሁን ደግሞ ሽብርተኝነትን በአንድነት እንዲዋጉ ጥሪያቸውን አቀረቡ።