ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 5
Appearance
- ፲፫፻፵፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው መነኩሴ አባ ኤውስጣቴዎስ በስደት በሚኖሩበት አርመን አገር ላይ ሞቱ።
- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም -አጼ ልብነ ድንግል በነገሡ በ፴፪ ዓመታቸው ሐሙስ ዕለት ደብረ ዳሞ ላይ አረፉ። የንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን፣ ዘውድና ዙፋናቸው በዚሁ ዕለት ወደልጃቸው የ፲፰ ዓመቱ አጼ ገላውዴዎስ (ስመ መንግሥት፣ አፅራር ሰገድ) ተላለፈ።
- ፲፮፻፪ ዓ/ም - የእንግሊዝ መርከበኛ ሄንሪ ሀድሰን (በዛሬዋ ኒው ዮርክ ከተማ) በስሙ የተሠየመውን የሀድሰን ወንዝን አገኘ።
- ፲፰፻፭ ዓ/ም - የናፖሌዎን ወራሪ ሠራዊት እንዳይማርከው የሩሲያ ሰራዊት የመስኮብን ከተማ አቃጠለ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም በወንጀላዊ ልብ ወለድ ጽሑፎቿ “አቻ የላት” የምትባለው እንግሊዛዊቷ ደራሲ አጋታ ክሪስቲ (Agatha Christie)፣ ቶርኪ (Torquay) በምትባል ከተማ ተወለደች። (ክሪስቲ በ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሞተች)
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ ታንክ የተባለው የጦር መሣሪያ አገልግሎት ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራና ኢትዮጵያ በ«ኅብረታዊ መንግሥት» እንዲዋሃዱ አጸደቀ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - በሁለት ትላልቅ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ድርጅቶች የመሪዎች መፈንቅል ተፈጸመ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት ስድስት ዓመት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ ሥራቸውን ለቀቁ። አቶ ግርማን የሚተኳቸው ምክትላቸው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይሆናሉ ይባላል። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አማረ አምሳሉም ሥራቸውን ለቀቁ